Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: ユーヌス章   節:
وَإِذَآ أَذَقۡنَا ٱلنَّاسَ رَحۡمَةٗ مِّنۢ بَعۡدِ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُمۡ إِذَا لَهُم مَّكۡرٞ فِيٓ ءَايَاتِنَاۚ قُلِ ٱللَّهُ أَسۡرَعُ مَكۡرًاۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكۡتُبُونَ مَا تَمۡكُرُونَ
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን ምቾትን ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነርሱ በተዓምራቶቻችን በማላገጥ ተንኮል ይኖራቸዋል:: «አላህ ቅጣቱ ፈጣን ነው።» በላቸው። መልዕክተኞቻችን የምታሴሩትን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይጽፋሉ።
アラビア語 クルアーン注釈:
هُوَ ٱلَّذِي يُسَيِّرُكُمۡ فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا كُنتُمۡ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَجَرَيۡنَ بِهِم بِرِيحٖ طَيِّبَةٖ وَفَرِحُواْ بِهَا جَآءَتۡهَا رِيحٌ عَاصِفٞ وَجَآءَهُمُ ٱلۡمَوۡجُ مِن كُلِّ مَكَانٖ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُمۡ أُحِيطَ بِهِمۡ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ لَئِنۡ أَنجَيۡتَنَا مِنۡ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
22. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው:: በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በእርሷ የተደሰቱ ሆነው መርከቦቹ በተንሻለሉ ጊዜ ሀይለኛ ነፋስ ትመጣባቸዋለች:: ከየስፍራዉም ማዕበል ይመጣባቸዋል:: እነርሱም ለጥፋት የተከበቡ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ያን ጊዜ አላህን «ከዚህች ጭንቀት ብታድነን ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ እምነታቸውን ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርገው ይለምኑታል::
アラビア語 クルアーン注釈:
فَلَمَّآ أَنجَىٰهُمۡ إِذَا هُمۡ يَبۡغُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۗ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغۡيُكُمۡ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمۖ مَّتَٰعَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ ثُمَّ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُكُمۡ فَنُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
23. በአዳናቸዉም ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ። እናንተ ሰዎች ሆይ ወሰን ማለፋችሁ ጥፋቱ በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ የቅርቢቱ ህይወት መጠቀሚያ ነው:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኛ ነው:: ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን::
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّمَا مَثَلُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَآءٍ أَنزَلۡنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخۡتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلۡأَرۡضِ مِمَّا يَأۡكُلُ ٱلنَّاسُ وَٱلۡأَنۡعَٰمُ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذَتِ ٱلۡأَرۡضُ زُخۡرُفَهَا وَٱزَّيَّنَتۡ وَظَنَّ أَهۡلُهَآ أَنَّهُمۡ قَٰدِرُونَ عَلَيۡهَآ أَتَىٰهَآ أَمۡرُنَا لَيۡلًا أَوۡ نَهَارٗا فَجَعَلۡنَٰهَا حَصِيدٗا كَأَن لَّمۡ تَغۡنَ بِٱلۡأَمۡسِۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
24. . የቅርቢቱ ህይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት እንደፋፋ ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋን በእርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መሆናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትዕዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱللَّهُ يَدۡعُوٓاْ إِلَىٰ دَارِ ٱلسَّلَٰمِ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
25. አላህ (ሁል ጊዜም) ወደ ሰላም አገር ይጠራል:: የሚፈልገዉን ሰዉም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: ユーヌス章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる