Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: フード章   節:
وَيَصۡنَعُ ٱلۡفُلۡكَ وَكُلَّمَا مَرَّ عَلَيۡهِ مَلَأٞ مِّن قَوۡمِهِۦ سَخِرُواْ مِنۡهُۚ قَالَ إِن تَسۡخَرُواْ مِنَّا فَإِنَّا نَسۡخَرُ مِنكُمۡ كَمَا تَسۡخَرُونَ
38. ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር በእርሱ ላይ እየተሳለቁበት መርከቢቱን ይሠራል። አላቸውም: «በእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን በእናንተ እንሳለቅባችኋለን።
アラビア語 クルアーン注釈:
فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيۡهِ عَذَابٞ مُّقِيمٌ
39. «የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ወደ ፊት ታውቃላችሁ።» አላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ قُلۡنَا ٱحۡمِلۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ وَمَنۡ ءَامَنَۚ وَمَآ ءَامَنَ مَعَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٞ
40. ትዕዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በመርከቧ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን።» አልነው:: ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም ነበር::
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ وَقَالَ ٱرۡكَبُواْ فِيهَا بِسۡمِ ٱللَّهِ مَجۡر۪ىٰهَا وَمُرۡسَىٰهَآۚ إِنَّ رَبِّي لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ
41. «‹መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው።› እያላችሁ በእርሷ ተሳፈሩ:: ጌታዬ መሓሪና አዛኝ ነውና።» አላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَهِيَ تَجۡرِي بِهِمۡ فِي مَوۡجٖ كَٱلۡجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ٱبۡنَهُۥ وَكَانَ فِي مَعۡزِلٖ يَٰبُنَيَّ ٱرۡكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
42. እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ እነርሱን ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት።) ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር። ከከሓዲያንም አትሁን።» ሲል ጠራው።
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ سَـَٔاوِيٓ إِلَىٰ جَبَلٖ يَعۡصِمُنِي مِنَ ٱلۡمَآءِۚ قَالَ لَا عَاصِمَ ٱلۡيَوۡمَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَۚ وَحَالَ بَيۡنَهُمَا ٱلۡمَوۡجُ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُغۡرَقِينَ
43. ልጁም «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ።» አለ:: አባቱም «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም:: እርሱ ብቻ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር።» አለው:: ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ:: ልጁም ከሰማጮች ሆነ::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَقِيلَ يَٰٓأَرۡضُ ٱبۡلَعِي مَآءَكِ وَيَٰسَمَآءُ أَقۡلِعِي وَغِيضَ ٱلۡمَآءُ وَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ وَٱسۡتَوَتۡ عَلَى ٱلۡجُودِيِّۖ وَقِيلَ بُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
44. ተባለም «ምድር ሆይ! ዉሃሽን ዋጪ:: ሰማይ ሆይ! ዝናብሽን ያዢ።» ውሃዉም ሠረገ:: ቅጣቱም ተፈጸመ:: ጁዲይ በሚባለም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች:: «ለከሓዲያን ጥፋት ተገባቸው (ጥፉ)።» ተባለ።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَنَادَىٰ نُوحٞ رَّبَّهُۥ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ٱبۡنِي مِنۡ أَهۡلِي وَإِنَّ وَعۡدَكَ ٱلۡحَقُّ وَأَنتَ أَحۡكَمُ ٱلۡحَٰكِمِينَ
45. ኑህም ጌታውን- «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ አንዱ ነው:: ቃል ኪዳንህም እውነት ነው:: አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነህ።» በማለት ጠየቀ (ተጣራ)::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: フード章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる