Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 蟻章   節:
فَلَمَّا جَآءَ سُلَيۡمَٰنَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٖ فَمَآ ءَاتَىٰنِۦَ ٱللَّهُ خَيۡرٞ مِّمَّآ ءَاتَىٰكُمۚ بَلۡ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمۡ تَفۡرَحُونَ
36. መልዕክተኛው ሱለይማንን በመጣውም ጊዜ አለ፡- «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን? አላህም የሰጠን ከሰጣችሁ የበለጠ ነው:: ይልቁንም እናንተ በገጸበረከታችሁ ትደሰታላችሁ።
アラビア語 クルアーン注釈:
ٱرۡجِعۡ إِلَيۡهِمۡ فَلَنَأۡتِيَنَّهُم بِجُنُودٖ لَّا قِبَلَ لَهُم بِهَا وَلَنُخۡرِجَنَّهُم مِّنۡهَآ أَذِلَّةٗ وَهُمۡ صَٰغِرُونَ
37. «ወደ እነርሱ ተመለስ:: ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን:: ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ሆነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን።» አለ።
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ أَيُّكُمۡ يَأۡتِينِي بِعَرۡشِهَا قَبۡلَ أَن يَأۡتُونِي مُسۡلِمِينَ
38. «እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ሆነው ወደ እኔ ሳይመጡ በፊት ዙፋኗን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው?» አለ::
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ عِفۡرِيتٞ مِّنَ ٱلۡجِنِّ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبۡلَ أَن تَقُومَ مِن مَّقَامِكَۖ وَإِنِّي عَلَيۡهِ لَقَوِيٌّ أَمِينٞ
39. ከጋኔን ሃይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ:: እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ።» አለ።
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ ٱلَّذِي عِندَهُۥ عِلۡمٞ مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبۡلَ أَن يَرۡتَدَّ إِلَيۡكَ طَرۡفُكَۚ فَلَمَّا رَءَاهُ مُسۡتَقِرًّا عِندَهُۥ قَالَ هَٰذَا مِن فَضۡلِ رَبِّي لِيَبۡلُوَنِيٓ ءَأَشۡكُرُ أَمۡ أَكۡفُرُۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشۡكُرُ لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيّٞ كَرِيمٞ
40. ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው «የተገለጸው ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ።» አለ:: እንደዚሁም አደረገ:: እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየዉም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው። የማመሰግን ወይም የምክድ መሆኔን ሊሞክረኝ ቸረልኝ:: አላህን ያመሰገነ ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ነው:: አላህን የካደም ሰው ሁሉ ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ፤ ቸር ነው።» አለ::
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ نَكِّرُواْ لَهَا عَرۡشَهَا نَنظُرۡ أَتَهۡتَدِيٓ أَمۡ تَكُونُ مِنَ ٱلَّذِينَ لَا يَهۡتَدُونَ
41. «ዙፋኗን ለእርሷ አሳስቱ ታውቀው እንደሆነ ወይም ከእነዚያ ከማያውቁት ትሆን እንደሆነ እናያለን።» አላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
فَلَمَّا جَآءَتۡ قِيلَ أَهَٰكَذَا عَرۡشُكِۖ قَالَتۡ كَأَنَّهُۥ هُوَۚ وَأُوتِينَا ٱلۡعِلۡمَ مِن قَبۡلِهَا وَكُنَّا مُسۡلِمِينَ
42. በመጣችም ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን?» ተባለች «እርሱ ልክ እርሱን ነው የመሰለኝ።» አለች። ሱለይማንም አለ: «ከእርሷ በፊትም እውቀትን ተሰጠን:: ሙስሊሞችም ነበርን።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَصَدَّهَا مَا كَانَت تَّعۡبُدُ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ إِنَّهَا كَانَتۡ مِن قَوۡمٖ كَٰفِرِينَ
43. «ከአላህ ሌላ ትገዛው የነበረችውንም ከለከላት:: እርሷ ከከሓዲያን ሕዝቦች ነበረችና።»
アラビア語 クルアーン注釈:
قِيلَ لَهَا ٱدۡخُلِي ٱلصَّرۡحَۖ فَلَمَّا رَأَتۡهُ حَسِبَتۡهُ لُجَّةٗ وَكَشَفَتۡ عَن سَاقَيۡهَاۚ قَالَ إِنَّهُۥ صَرۡحٞ مُّمَرَّدٞ مِّن قَوَارِيرَۗ قَالَتۡ رَبِّ إِنِّي ظَلَمۡتُ نَفۡسِي وَأَسۡلَمۡتُ مَعَ سُلَيۡمَٰنَ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
44. «ሕንጻውን ግቢ።» ተባለች:: ባየችዉም ጊዜ ባህር ነው ብላ ጠረጠረችው:: ከባቶቿም ገለጠች:: «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ህንጻ ነው።» አሏት:: «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩኝ።» አለች።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 蟻章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる