Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: イムラーン家章   節:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُواْ نَصِيبٗا مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ يُدۡعَوۡنَ إِلَىٰ كِتَٰبِ ٱللَّهِ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٞ مِّنۡهُمۡ وَهُم مُّعۡرِضُونَ
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፍ (ትምህርት) ድረሻን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን? ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ይጠራሉ:: ከዚያ ከእነርሱ ገሚሶቹ (ከፊሎቹ) እውነቱን ወደ ጎን የተው ሆነው ይሸሻሉ::
アラビア語 クルアーン注釈:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَالُواْ لَن تَمَسَّنَا ٱلنَّارُ إِلَّآ أَيَّامٗا مَّعۡدُودَٰتٖۖ وَغَرَّهُمۡ فِي دِينِهِم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
24. ይህም እነርሱ «የገሀነም እሳት የተቆጠሩ ቀናትን ብቻ እንጂ አትነካንም።» በማለታቸው ነው:: በሀይማኖታቸዉም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
فَكَيۡفَ إِذَا جَمَعۡنَٰهُمۡ لِيَوۡمٖ لَّا رَيۡبَ فِيهِ وَوُفِّيَتۡ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا كَسَبَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
25. በእርሱ መምጣት ጥርጥር የሌለበት በሆነው ቀን በሰበሰብናቸውና ነፍስ ሁሉ የሰራችውን ስራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም ቅንጣትንም አይበደሉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلۡمُلۡكِ تُؤۡتِي ٱلۡمُلۡكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلۡمُلۡكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُۖ بِيَدِكَ ٱلۡخَيۡرُۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «የንግስና ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግስናን ትሰጣለህ:: ከምትሻዉም ሰው ንግስናን ትገፋለህ:: የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ:: የምትሻውንም ሰው ደግሞ ታዋርዳለህ:: መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ብቻ ነው:: አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።
アラビア語 クルアーン注釈:
تُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَتُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۖ وَتُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَتُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّۖ وَتَرۡزُقُ مَن تَشَآءُ بِغَيۡرِ حِسَابٖ
27. «ሌሊቱን በቀን ውስጥ ታስገባለህ:: ቀኑንም በሌሊት ውስጥ ታስገባለህ:: ሕያውንም ከሙት ታወጣለህ:: ሙታንንም ከሕያው ታወጣለህ፤ ለምትሻውም ሁሉ መጠን የለሽ ሲሳይ ትሰጣለህ።» በል።
アラビア語 クルアーン注釈:
لَّا يَتَّخِذِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ فَلَيۡسَ مِنَ ٱللَّهِ فِي شَيۡءٍ إِلَّآ أَن تَتَّقُواْ مِنۡهُمۡ تُقَىٰةٗۗ وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفۡسَهُۥۗ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ
28. አማኞች ከሓዲያንን ከአማኞች ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ። ይህንን የሚሰራ ከአላህ ሀይማኖት በምንም ውስጥ አይደለም:: ከእነርሱ መጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ:: አላህ ከእርሱው ያስጠነቅቃችኋል:: መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነውና።
アラビア語 クルアーン注釈:
قُلۡ إِن تُخۡفُواْ مَا فِي صُدُورِكُمۡ أَوۡ تُبۡدُوهُ يَعۡلَمۡهُ ٱللَّهُۗ وَيَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ብትደብቁት ወይም ብትገልጹት አላህ ያውቀዋል:: በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በል።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: イムラーン家章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる