クルアーンの対訳 - الترجمة الأمهرية - زين * - 対訳の目次


対訳 章: 相談章   節:

ሱረቱ አሽ ሹራ

حمٓ
1. ሓ፤ሚይም፤
アラビア語 クルアーン注釈:
عٓسٓقٓ
2. ዐይን፤ ሲን፤ ቃፍ::
アラビア語 クルアーン注釈:
كَذَٰلِكَ يُوحِيٓ إِلَيۡكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكَ ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እንዳለው አሸናፊውና ጥበበኛው አላህ ወደ አንተ ያወርዳል:: ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ህዝቦችም አውርዷል::
アラビア語 クルアーン注釈:
لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡعَظِيمُ
4. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرۡنَ مِن فَوۡقِهِنَّۚ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَيَسۡتَغۡفِرُونَ لِمَن فِي ٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
5. ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያጠራሉ:: በምድር ላለው ፍጡርም ምህረትን ይለምናሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: መሀሪውና አዛኙ አላህ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ ٱللَّهُ حَفِيظٌ عَلَيۡهِمۡ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٖ
6. እነዚያም ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድርገው የያዙ ሁሉ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው:: አንተም በእነርሱ ላይ ሀላፊ አይደለህም::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَكَذَٰلِكَ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ قُرۡءَانًا عَرَبِيّٗا لِّتُنذِرَ أُمَّ ٱلۡقُرَىٰ وَمَنۡ حَوۡلَهَا وَتُنذِرَ يَوۡمَ ٱلۡجَمۡعِ لَا رَيۡبَ فِيهِۚ فَرِيقٞ فِي ٱلۡجَنَّةِ وَفَرِيقٞ فِي ٱلسَّعِيرِ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን የመካን ሰዎችና በአካባቢዋ ያሉትን ህዝቦች ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ በዐረበኛ ቋንቋ የሆነን ቁርኣንን ወደ አንተ አወረድን:: ከእነርሱም ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም ደግሞ በእሳት ውስጥ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَهُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَلَٰكِن يُدۡخِلُ مَن يَشَآءُ فِي رَحۡمَتِهِۦۚ وَٱلظَّٰلِمُونَ مَا لَهُم مِّن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٍ
8. አላህ በፈለገ ኖሮ ሰዎችን በአንድ ሃይማኖት ላይ የሆኑ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር:: ግን የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዮች ሁሉ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَۖ فَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡوَلِيُّ وَهُوَ يُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
9. ከእርሱ ሌላ ረዳቶች ያዙን? (እነርሱ ረዳቶች አይደሉም) ትክክለኛ ረዳት አላህ ብቻ ነው:: እርሱ ሙታንን ህያው ያደርጋል:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَا ٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِيهِ مِن شَيۡءٖ فَحُكۡمُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبِّي عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُ وَإِلَيۡهِ أُنِيبُ
10. (ሰዎች ሆይ!) «ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ (አላህ) ጌታዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመካሁ:: ወደ እርሱም ብቻ እመለሳለሁ» በላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
فَاطِرُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ جَعَلَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجٗا وَمِنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ أَزۡوَٰجٗا يَذۡرَؤُكُمۡ فِيهِۚ لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ
11. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው አላህ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንሰሳዎችም አይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: በዚህ ድርጊቱም ያባዛችኋል:: የሚመስለው ምንም ነገር የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
لَهُۥ مَقَالِيدُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ
12. የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መክፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: ሲሳይን ለሚፈልገው ሰው ያሰፋል:: ለሚፈልገዉም ያጠባል:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحٗا وَٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ وَمَا وَصَّيۡنَا بِهِۦٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓۖ أَنۡ أَقِيمُواْ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُواْ فِيهِۚ كَبُرَ عَلَى ٱلۡمُشۡرِكِينَ مَا تَدۡعُوهُمۡ إِلَيۡهِۚ ٱللَّهُ يَجۡتَبِيٓ إِلَيۡهِ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِيٓ إِلَيۡهِ مَن يُنِيبُ
13. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑህን ያዘዘበትን ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም ኢብራሂምን፤ ሙሳንና ዒሳንም በእርሱ ያዘዝንበት የሆነውን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም ላይ አትለያዩ በማለት ደነገገላችሁ::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ አጋሪዎች ያ ወደ እርሱ የምትጠራቸው ነገር (ኢስላም) ከበዳቸው:: አላህ የሚፈልገውን ሰው ወደ እርሱ እምነት ይመርጣል:: የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَا تَفَرَّقُوٓاْ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُ بَغۡيَۢا بَيۡنَهُمۡۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى لَّقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُورِثُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሃይማኖት ሰዎች እውቀት ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ባለ ወሰን አላፊነት እንጂ በሌላ አልተለያዩም:: እስከተወሰነ ጊዜ በማቆየት ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል አሁኑኑ በተፈረደ ነበር:: እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፍን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ ባወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
فَلِذَٰلِكَ فَٱدۡعُۖ وَٱسۡتَقِمۡ كَمَآ أُمِرۡتَۖ وَلَا تَتَّبِعۡ أَهۡوَآءَهُمۡۖ وَقُلۡ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٖۖ وَأُمِرۡتُ لِأَعۡدِلَ بَيۡنَكُمُۖ ٱللَّهُ رَبُّنَا وَرَبُّكُمۡۖ لَنَآ أَعۡمَٰلُنَا وَلَكُمۡ أَعۡمَٰلُكُمۡۖ لَا حُجَّةَ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمُۖ ٱللَّهُ يَجۡمَعُ بَيۡنَنَاۖ وَإِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እዚህ መንገድም ጋኔንንና ሰዎችን ጥራ:: ልክ እንደታዘዝከዉም ቀጥ በል:: ዝንባሌያቸውን አትከተል:: «ከመጽሐፍም አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ:: በመካከላችሁ በፍርድ ላስተካክልም ታዘዝኩ:: አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው:: ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም እንዲሁ ስራዎቻችሁ አሏችሁ:: በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም:: አላህ በመካከላችን ይሰበስባል:: መመለሻው ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱلَّذِينَ يُحَآجُّونَ فِي ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا ٱسۡتُجِيبَ لَهُۥ حُجَّتُهُمۡ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمۡ وَعَلَيۡهِمۡ غَضَبٞ وَلَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٌ
16. እነዚያም በአላህ ሃይማኖት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ሰዎች ማስረጃዎቻቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ (ዉድቅ) ናቸው:: በእነርሱም ላይ የአላህ ቁጣ አለባቸው (ወደቀባቸው):: ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አለባቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
ٱللَّهُ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ وَٱلۡمِيزَانَۗ وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٞ
17. አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው:: ሚዛንንም ልክ እንደዚሁ ያወረደ ነው:: ሰዓቲቱ ምን አልባት ቅርብ ብትሆንስ ምን አሳወቀህ?
アラビア語 クルアーン注釈:
يَسۡتَعۡجِلُ بِهَا ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِهَاۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مُشۡفِقُونَ مِنۡهَا وَيَعۡلَمُونَ أَنَّهَا ٱلۡحَقُّۗ أَلَآ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُمَارُونَ فِي ٱلسَّاعَةِ لَفِي ضَلَٰلِۭ بَعِيدٍ
18. እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ግን ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው:: እርሷ እውነት መሆኗንም በትክክል ያውቃሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከእውነት በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
ٱللَّهُ لَطِيفُۢ بِعِبَادِهِۦ يَرۡزُقُ مَن يَشَآءُۖ وَهُوَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡعَزِيزُ
19. አላህ ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው:: ለሚፈልገው ሰውም ሁሉ በሰፊው ሲሳይን ይሰጣል:: እርሱም ብርቱዉ እና አሸናፊው ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
مَن كَانَ يُرِيدُ حَرۡثَ ٱلۡأٓخِرَةِ نَزِدۡ لَهُۥ فِي حَرۡثِهِۦۖ وَمَن كَانَ يُرِيدُ حَرۡثَ ٱلدُّنۡيَا نُؤۡتِهِۦ مِنۡهَا وَمَا لَهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِن نَّصِيبٍ
20. በስራው የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ለእርሱ በአዝመራው ላይ ሌላን እንጨምርለታለን:: የቅርቢቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ግን በእርሷ የተወሰነለትን ብቻ እንሰጠዋለን:: ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَٰٓؤُاْ شَرَعُواْ لَهُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا لَمۡ يَأۡذَنۢ بِهِ ٱللَّهُۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةُ ٱلۡفَصۡلِ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
21. ከሓዲያን ከአላህ ያልተፈቀደውን ሃይማኖት የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው ወዲያውኑ በተፈረደ ነበር:: በደለኞችም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
تَرَى ٱلظَّٰلِمِينَ مُشۡفِقِينَ مِمَّا كَسَبُواْ وَهُوَ وَاقِعُۢ بِهِمۡۗ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فِي رَوۡضَاتِ ٱلۡجَنَّاتِۖ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمۡۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَضۡلُ ٱلۡكَبِيرُ
22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደለኞችን በሰሩት ስራ ዋጋ በትንሳኤ ቀን ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ:: እርሱም በእነርሱ ላይ የማይቀር ወዳቂ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራን የሰሩ ሁሉ በገነት ጨፌዎች ዉስጥ ናቸው:: ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ታላቅ ችሮታ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
ذَٰلِكَ ٱلَّذِي يُبَشِّرُ ٱللَّهُ عِبَادَهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِۗ قُل لَّآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًا إِلَّا ٱلۡمَوَدَّةَ فِي ٱلۡقُرۡبَىٰۗ وَمَن يَقۡتَرِفۡ حَسَنَةٗ نَّزِدۡ لَهُۥ فِيهَا حُسۡنًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ شَكُورٌ
23. (ይህ ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩት ባሮቹን የሚያበስርበት ነው::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልዕክቴን በማድረሴ ላይ የዝምድና ውዴታየን እንጂ ሌላ ዋጋ አልጠይቃችሁም በላቸው:: መልካም ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ ለእርሱ በእርሷ ላይ መልካምን ነገርን እንጨምርለታለን:: አላህ መሀሪ እና አመስጋኝ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗاۖ فَإِن يَشَإِ ٱللَّهُ يَخۡتِمۡ عَلَىٰ قَلۡبِكَۗ وَيَمۡحُ ٱللَّهُ ٱلۡبَٰطِلَ وَيُحِقُّ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢፈልግ በልብህ ላይ ያትማል:: አላህ ውሸትን ያብሳል:: እውነትንም በቃላቱ ያረጋግጣል:: እርሱ በይፋ የተነገሩት ቀርቶ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَهُوَ ٱلَّذِي يَقۡبَلُ ٱلتَّوۡبَةَ عَنۡ عِبَادِهِۦ وَيَعۡفُواْ عَنِ ٱلسَّيِّـَٔاتِ وَيَعۡلَمُ مَا تَفۡعَلُونَ
25. እርሱም አላህ ያ ሁልጊዜም ከባሮቹ ንስሀን የሚቀበል ኃጢአቶችንም ይቅር የሚል የምትሰሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ጌታ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَيَسۡتَجِيبُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضۡلِهِۦۚ وَٱلۡكَٰفِرُونَ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞ
26. እነዚያም በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልመናቸውን ይቀበላል:: ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል:: ከሓዲያንም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ وَلَوۡ بَسَطَ ٱللَّهُ ٱلرِّزۡقَ لِعِبَادِهِۦ لَبَغَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَٰكِن يُنَزِّلُ بِقَدَرٖ مَّا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرُۢ بَصِيرٞ
27. አላህም ለባሮቹ ሁሉ ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ ሁሉም ወሰን ባለፉ ነበር:: ግን የሚፈልገውን በልክ ያወርዳል:: እርሱ በባሮቹ ውስጠ አዋቂ፤ ተመልካች ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَهُوَ ٱلَّذِي يُنَزِّلُ ٱلۡغَيۡثَ مِنۢ بَعۡدِ مَا قَنَطُواْ وَيَنشُرُ رَحۡمَتَهُۥۚ وَهُوَ ٱلۡوَلِيُّ ٱلۡحَمِيدُ
28. አላህ ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናብን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው:: እርሱም ረዳቱና ምስጉኑ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ خَلۡقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَثَّ فِيهِمَا مِن دَآبَّةٖۚ وَهُوَ عَلَىٰ جَمۡعِهِمۡ إِذَا يَشَآءُ قَدِيرٞ
29. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን ፍጡር መፍጠሩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ከፊሎቹ ናቸው:: እርሱም በሚፈልግ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَآ أَصَٰبَكُم مِّن مُّصِيبَةٖ فَبِمَا كَسَبَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَيَعۡفُواْ عَن كَثِيرٖ
30. (ሰዎች ሆይ!) ማንኛዉም መከራ (ያገኛችሁ ነገር) እጆቻችሁ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ብቻ ነው:: ብዙውንም ይቅር ይላል::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ
31. (ሰዎች ሆይ!) እናንተ በምድር ውስጥ የምትሳኑን (አምላጮች) አይደላችሁም:: ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት ምንም የላችሁም::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلۡجَوَارِ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ
32. በባህር ላይ እንደ ጋራዎች ሆነው ተንሻላዮቹ መርከቦችም ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
إِن يَشَأۡ يُسۡكِنِ ٱلرِّيحَ فَيَظۡلَلۡنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهۡرِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٍ
33. ቢፈልግ ንፋሱን የረጋ ያደርገዋል:: ከዚያም መርከቦች በባህሩ ጀርባ ላይ የረጉ ይሆናሉ:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ፤ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ በእርግጥም ብዙ ተዓምራት አሉ::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَوۡ يُوبِقۡهُنَّ بِمَا كَسَبُواْ وَيَعۡفُ عَن كَثِيرٖ
34. ወይም ተሳፋሪዎች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት እነርሱን በባህሩ በማስመጥ ያጠፋቸዋል:: ከብዙ ጥፋቶችም ይቅርታ ያደርጋል።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٖ
35. ከእነርሱ መካከል እነዚያን በአናቅጻችን የሚከራከሩትን ሰዎች ለማወቅ (ያጠፋቸዋል):: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም መሸሻ የላቸዉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
فَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَيۡءٖ فَمَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ
36. (ሰዎች ሆይ!) የተሰጣችሁት ነገር ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: በአላህ ዘንድ ያለው ምንዳ ግን ለእነዚያ በትክክል በእሱ ላመኑትና በጌታቸው ላይ ብቻ ለሚመኩት ሁሉ በላጭና ሁልጊዜ ነዋሪ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُواْ هُمۡ يَغۡفِرُونَ
37. ለእነዚያም ታላላቅ ሃጢያቶችንና ዝሙትን የሚርቁ፤ በተቆጡም ጊዜ የሚምሩ ለሆኑት፤
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱلَّذِينَ ٱسۡتَجَابُواْ لِرَبِّهِمۡ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَمۡرُهُمۡ شُورَىٰ بَيۡنَهُمۡ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ
38. ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፤ ሶላትንም ላዘወተሩት፤ በነገራቸው ላይም በመካከላቸው መመካከር ልምዳቸው ለሆነው፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ለሚለግሱት፤
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَابَهُمُ ٱلۡبَغۡيُ هُمۡ يَنتَصِرُونَ
39. ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ በመሰሉ የሚመልሱ ለሆኑት (በላጭና ነዋሪ ነው)::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَجَزَٰٓؤُاْ سَيِّئَةٖ سَيِّئَةٞ مِّثۡلُهَاۖ فَمَنۡ عَفَا وَأَصۡلَحَ فَأَجۡرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ
40. የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋጋው ተመሳሳዩ መጥፎ ነው:: ይቅር ያለና ያሳመረ ሰው ደግሞ ምንዳው በአላህ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ በደለኞችን አይወድምና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَمَنِ ٱنتَصَرَ بَعۡدَ ظُلۡمِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ مَا عَلَيۡهِم مِّن سَبِيلٍ
41. እነዚያ ከተበደሉ በኋላ በመሰሉ የተበቀሉ በእነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸዉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَظۡلِمُونَ ٱلنَّاسَ وَيَبۡغُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
42. የወቀሳ መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት እና በምድር ውስጥም ያለ ህግ ወሰንን በሚያልፉት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَمَن صَبَرَ وَغَفَرَ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ
43. የታገሰና ምህረት ያደረገ፤ ይህ ተግባር በእጅጉን ተፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن وَلِيّٖ مِّنۢ بَعۡدِهِۦۗ وَتَرَى ٱلظَّٰلِمِينَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَ يَقُولُونَ هَلۡ إِلَىٰ مَرَدّٖ مِّن سَبِيلٖ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሚያጠመውን ሰው ከእርሱ ማጥመም በኋላ ለእርሱ ምንም ወዳጅ የለዉም:: በደለኞችም ቅጣትን ባዩ ጊዜ «ለመመለስ መንገድ አለን?» የሚሉ ሲሆኑ ታያቸዋለህ::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَتَرَىٰهُمۡ يُعۡرَضُونَ عَلَيۡهَا خَٰشِعِينَ مِنَ ٱلذُّلِّ يَنظُرُونَ مِن طَرۡفٍ خَفِيّٖۗ وَقَالَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّ ٱلۡخَٰسِرِينَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِيهِمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ أَلَآ إِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ فِي عَذَابٖ مُّقِيمٖ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ሆነው በዓይን ስርቆት ወደ እሳት እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀርቡ ሁነው ታያቸዋለህ:: እነዚያም በአላህ ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሳኤ ቀን የከሰሩት ናቸው» ይላሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: በደለኞች በእርግጥ ዘወታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَا كَانَ لَهُم مِّنۡ أَوۡلِيَآءَ يَنصُرُونَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِۗ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن سَبِيلٍ
46. ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ረዳቶች ምንም አልነበሯቸዉም:: አላህ የሚያጠመው ሰው ሁሉ ለእርሱ ወደ እውነት የሚመለስበት ምንም መንገድ የለዉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
ٱسۡتَجِيبُواْ لِرَبِّكُم مِّن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَ يَوۡمٞ لَّا مَرَدَّ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِۚ مَا لَكُم مِّن مَّلۡجَإٖ يَوۡمَئِذٖ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٖ
47. ያ ከአላህ ከመጣ መላሽ የሌለለው ቀን ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ:: በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያም ሆነ መቃወም የላችሁም።
アラビア語 クルアーン注釈:
فَإِنۡ أَعۡرَضُواْ فَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ حَفِيظًاۖ إِنۡ عَلَيۡكَ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُۗ وَإِنَّآ إِذَآ أَذَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِنَّا رَحۡمَةٗ فَرِحَ بِهَاۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ فَإِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ كَفُورٞ
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም::) በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድረገን አላክንህምና:: ባንተ ላይ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብህም:: እኛም ሰውን ከእኛ የሆነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በእርሷ ይደሰታል:: እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው ደግሞ ተስፋ ይቆርጣሉ:: ሰው በጣም ውለታን ከሓዲ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
لِّلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ يَهَبُ لِمَن يَشَآءُ إِنَٰثٗا وَيَهَبُ لِمَن يَشَآءُ ٱلذُّكُورَ
49. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ለሚፈልገው ሴቶችን ልጆች ይሰጣል:: ለሚፈልገዉም ወንዶችን ይሰጣል::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَوۡ يُزَوِّجُهُمۡ ذُكۡرَانٗا وَإِنَٰثٗاۖ وَيَجۡعَلُ مَن يَشَآءُ عَقِيمًاۚ إِنَّهُۥ عَلِيمٞ قَدِيرٞ
50. ወይም ወንዶችንና ሴቶችን አድርጎ ያጠናዳቸዋል:: የሚፈልገውንም መካን ያደርገዋል:: እርሱ ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحۡيًا أَوۡ مِن وَرَآيِٕ حِجَابٍ أَوۡ يُرۡسِلَ رَسُولٗا فَيُوحِيَ بِإِذۡنِهِۦ مَا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ عَلِيٌّ حَكِيمٞ
51. ሰውን አላህ በራዕይ ወይም ከግርዶሹ ወዲያ ወይም መልዕከተኛን በመላክና በፈቃዱ የሚፈልገውን ነገር የሚያወርድለት ቢሆን እንጂ በገሀድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም:: እርሱ የበላይና ጥበበኛ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَكَذَٰلِكَ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ رُوحٗا مِّنۡ أَمۡرِنَاۚ مَا كُنتَ تَدۡرِي مَا ٱلۡكِتَٰبُ وَلَا ٱلۡإِيمَٰنُ وَلَٰكِن جَعَلۡنَٰهُ نُورٗا نَّهۡدِي بِهِۦ مَن نَّشَآءُ مِنۡ عِبَادِنَاۚ وَإِنَّكَ لَتَهۡدِيٓ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን ሂወት የሆነውን (ቁርአን) አወረድነው:: መጽሐፉም ሆነ እምነቱ ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም:: ግን ቁርኣንን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው:: አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ::
アラビア語 クルアーン注釈:
صِرَٰطِ ٱللَّهِ ٱلَّذِي لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِلَى ٱللَّهِ تَصِيرُ ٱلۡأُمُورُ
53. ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ሆነው ወደ አላህ መንገድ (ትመራለህ):: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 相談章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - الترجمة الأمهرية - زين - 対訳の目次

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

閉じる