Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 勝利章   節:

አል ፈትህ

إِنَّا فَتَحۡنَا لَكَ فَتۡحٗا مُّبِينٗا
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ላንተ (መካን) በመክፈት ግልጽ የሆነን ድል ለገስንህ።
アラビア語 クルアーン注釈:
لِّيَغۡفِرَ لَكَ ٱللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنۢبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَيَهۡدِيَكَ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا
2. አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን ኃጢአትክን ሊምርህ፤ ፀጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላና ቀጥተኛዉን መንገድ ሊመራህ፤
アラビア語 クルアーン注釈:
وَيَنصُرَكَ ٱللَّهُ نَصۡرًا عَزِيزًا
3. አላህም ብርቱን እርዳታ ሊረዳህ መካን ከፈተልህ::
アラビア語 クルアーン注釈:
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لِيَزۡدَادُوٓاْ إِيمَٰنٗا مَّعَ إِيمَٰنِهِمۡۗ وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا
4. አላህ ያ በአማኞች ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው:: አላህ የሰማይና የምድር ስራዊት ሁሉ የሱ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
لِّيُدۡخِلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَيُكَفِّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عِندَ ٱللَّهِ فَوۡزًا عَظِيمٗا
5. ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናትን በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ሊያስገባቸው፤ ከነርሱም ሐጢያቶቻቸዉን ሊያብስላቸው (መካን ከፈተልህ):: ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ መታደል ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَيُعَذِّبَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡمُشۡرِكِينَ وَٱلۡمُشۡرِكَٰتِ ٱلظَّآنِّينَ بِٱللَّهِ ظَنَّ ٱلسَّوۡءِۚ عَلَيۡهِمۡ دَآئِرَةُ ٱلسَّوۡءِۖ وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَلَعَنَهُمۡ وَأَعَدَّ لَهُمۡ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرٗا
6. በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ወንድ ተጣራጣሪ አስመሳዮችንና ሴት አስመሳዮችን ወንድ አጋሪዎችና ሴት አጋሪዎችን ያሰቃይም ዘንድ (በትግል አዘዘ):: በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው:: በእነርሱ ላይ አላህ ተቆጣባቸው ረገማቸዉም:: ለእነርሱ ገሀነምን አዘጋጀላቸው:: ገሀነም መመለሻነቷም ከፋች::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا
7. ለአላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ شَٰهِدٗا وَمُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا
8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መስካሪ፤ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእርግጥ ላክንህ::
アラビア語 クルアーン注釈:
لِّتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُۚ وَتُسَبِّحُوهُ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلًا
9. በአላህ ልታምኑ። በመልዕክተኛዉም ልታምኑ፤ ልትረዱትና ልታከብሩት፤ አላህንም በጠዋትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱት (ላክንህ)።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 勝利章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる