Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: 家畜章   節:
وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ مَلَكٗا لَّجَعَلۡنَٰهُ رَجُلٗا وَلَلَبَسۡنَا عَلَيۡهِم مَّا يَلۡبِسُونَ
9. መልዕክተኛውን ከመላዕክት መካከል ባደረግነው ኖሮ ወንድ ሰው አድርገን በመላክ በእነርሱ ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት በነበሩ መልዕክተኞችም ላይ ተላግጧል:: እናም በእነዚያ ባላገጡት ላይ ያላገጡበት ውጤት በእነርሱ ላይ ተፈጽሟል::
アラビア語 クルアーン注釈:
قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ ٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ከሓዲያንን) «በምድር ላይ ሂዱና የእነዚያን የአስተባባዮችን መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
قُل لِّمَن مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قُل لِّلَّهِۚ كَتَبَ عَلَىٰ نَفۡسِهِ ٱلرَّحۡمَةَۚ لَيَجۡمَعَنَّكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِۚ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው?» በላቸውም: «የአላህ ብቻ ነው። አላህ በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: በዚያ ጥርጥር በሌለበት በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ማለት እነርሱው ናቸው። እናም አያምኑም።
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ وَلَهُۥ مَا سَكَنَ فِي ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
13. «በሌሊትም ሆነ በቀን ጸጥ ያለው ሁሉ የእርሱው ነው:: እርሱም ሰሚውና አዋቂው ነው።»
アラビア語 クルアーン注釈:
قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيّٗا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَهُوَ يُطۡعِمُ وَلَا يُطۡعَمُۗ قُلۡ إِنِّيٓ أُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ أَوَّلَ مَنۡ أَسۡلَمَۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ እርሱ ፍጡርን የሚመግብና ለራሱ የማይመገብ አምላክ ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው። «እኔ መጀመሪያ ትዕዛዝን ከተቀበለ ሰው እንድሆን ታዘዝኩ:: ‹ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን።› ተብያለሁ።» በላቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
قُلۡ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ በጌታዬ ላይ ባምጽ የዚያን የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው።
アラビア語 クルアーン注釈:
مَّن يُصۡرَفۡ عَنۡهُ يَوۡمَئِذٖ فَقَدۡ رَحِمَهُۥۚ وَذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡمُبِينُ
16. በዚያ ቀን ከእርሱ ላይ ቅጣት የሚመለስለት ሰው ሁሉ በእርግጥ አላህ አዘነለት:: ይህም ግልጽ ስኬት ነው።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَإِن يَمۡسَسۡكَ ٱللَّهُ بِضُرّٖ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَۖ وَإِن يَمۡسَسۡكَ بِخَيۡرٖ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ችግር ቢያደርስብህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ማንም አስወጋጅ የለም:: በጎ ነገርን ቢሰጥህም እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ
18. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: እርሱ ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 家畜章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる