Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 戦利品章   節:
وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ أَنتُمۡ قَلِيلٞ مُّسۡتَضۡعَفُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ تَخَافُونَ أَن يَتَخَطَّفَكُمُ ٱلنَّاسُ فَـَٔاوَىٰكُمۡ وَأَيَّدَكُم بِنَصۡرِهِۦ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
26. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በምድር ላይ የተናቃችሁ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳላችሁ ሰዎች ሊነጥቋችሁ የምትፈሩ ስትሆኑ ያስጠጋችሁን፤ በእርዳታዉም ያበረታችሁን፤ ከመልካሞች ሲሳዮችም ታመሰግኑ ዘንድ የሰጣችሁን አላህን አስታውሱ::
アラビア語 クルアーン注釈:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَخُونُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ وَتَخُونُوٓاْ أَمَٰنَٰتِكُمۡ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
27. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን አትካዱ:: አደራዎቻችሁንም እያወቃችሁ አትካዱ::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَأَوۡلَٰدُكُمۡ فِتۡنَةٞ وَأَنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ
28. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለፈተና ብቻ መሆናቸውንና አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለ መሆኑን ዕወቁ።
アラビア語 クルアーン注釈:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَتَّقُواْ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّكُمۡ فُرۡقَانٗا وَيُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۗ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ
29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያ ብርሃንን ያደርግላችኋል:: ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከናንተ ላይ ያብስላችኋል:: እናንተንም ይምርላችኃል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَإِذۡ يَمۡكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيُثۡبِتُوكَ أَوۡ يَقۡتُلُوكَ أَوۡ يُخۡرِجُوكَۚ وَيَمۡكُرُونَ وَيَمۡكُرُ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلۡمَٰكِرِينَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያስወጡህ ባንተ ላይ ባሴሩብህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ያሴራሉም:: አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል:: አላህ ግን ከሴረኞቹ ሁሉ በላይ ነውና::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا قَالُواْ قَدۡ سَمِعۡنَا لَوۡ نَشَآءُ لَقُلۡنَا مِثۡلَ هَٰذَآ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
31. አናቅጻችን በነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜም: «በእርግጥ ሰምተናል። በሻን ኖሮ የዚህን አባባል ተመሳሳይ ባልን ነበር:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَإِذۡ قَالُواْ ٱللَّهُمَّ إِن كَانَ هَٰذَا هُوَ ٱلۡحَقَّ مِنۡ عِندِكَ فَأَمۡطِرۡ عَلَيۡنَا حِجَارَةٗ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ أَوِ ٱئۡتِنَا بِعَذَابٍ أَلِيمٖ
32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ የተወረደ እውነት እንደሆነ በእኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን።» ባሉጊዜ (የሆነውን አስታውስ)።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمۡ وَأَنتَ فِيهِمۡۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ مُعَذِّبَهُمۡ وَهُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ
33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በመካከላቸው እያለህ አላህ የሚቀጣቸው አይደለም። እነርሱም ምሕረትን የሚለምኑት ሲሆኑ አላህ የሚቀጣቸው አይደለም።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 戦利品章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる