Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់   អាយ៉ាត់:
۞ إِلَيۡهِ يُرَدُّ عِلۡمُ ٱلسَّاعَةِۚ وَمَا تَخۡرُجُ مِن ثَمَرَٰتٖ مِّنۡ أَكۡمَامِهَا وَمَا تَحۡمِلُ مِنۡ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلۡمِهِۦۚ وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ أَيۡنَ شُرَكَآءِي قَالُوٓاْ ءَاذَنَّٰكَ مَا مِنَّا مِن شَهِيدٖ
ጊዜይቱን ማወቅ ወደእርሱ ይመለሳል ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም፤ ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፣ አትወልድምም በዕውቀቱ ቢኾን እንጅ፡፡ «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም «ከእኛ ውስጥ (ባላንጣ አልለ ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አስታወቅንህ» ይላሉ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَدۡعُونَ مِن قَبۡلُۖ وَظَنُّواْ مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٖ
ያም በፊት ይግገዙት የነበሩት (ጣዖት) ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ ለእነርሱም ምንም መሸሻ የሌላቸው መኾኑን ያረጋግጣሉ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّا يَسۡـَٔمُ ٱلۡإِنسَٰنُ مِن دُعَآءِ ٱلۡخَيۡرِ وَإِن مَّسَّهُ ٱلشَّرُّ فَيَـُٔوسٞ قَنُوطٞ
ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም፡፡ ክፉም ቢያገኘው ወዲያውኑ በጣም ተስፋ ቆራጭ ተበሳጭ ይኾናል፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَئِنۡ أَذَقۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنَّا مِنۢ بَعۡدِ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُ لَيَقُولَنَّ هَٰذَا لِي وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّجِعۡتُ إِلَىٰ رَبِّيٓ إِنَّ لِي عِندَهُۥ لَلۡحُسۡنَىٰۚ فَلَنُنَبِّئَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِمَا عَمِلُواْ وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ
ካገኘችውም መከራ በኋላ ከእኛ የኾነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ (በሥራዬ የተገባኝ) ነው፤ ሳዓቲቱም መጪ ናት ብዬ አላስብም። ወደ ጌታዬ ብመለስ (እንኳን) ለእኔ በርሱ ዘንድ መልካሚቱ ገነት በእርግጥ አለችልኝ" ይላል። እነዚህም የካዱትን ስራዎቻቸውን በእርግጥ እንነግራቸዋለን። ከበረታውም ስቃይም በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ فَذُو دُعَآءٍ عَرِيضٖ
በሰውም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ (ከማመስገን) ይዞራል፡፡ በጎኑም ይርቃል፡፡ መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይኾናል፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كَانَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ ثُمَّ كَفَرۡتُم بِهِۦ مَنۡ أَضَلُّ مِمَّنۡ هُوَ فِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ
በላቸው «ንገሩኝ (ቁርኣኑ) ከአላህ ዘንድ ቢኾን ከዚያም በእርሱ ብትክዱ (ከውነት) በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከኾነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
سَنُرِيهِمۡ ءَايَٰتِنَا فِي ٱلۡأٓفَاقِ وَفِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمۡ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّۗ أَوَلَمۡ يَكۡفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ
እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَآ إِنَّهُمۡ فِي مِرۡيَةٖ مِّن لِّقَآءِ رَبِّهِمۡۗ أَلَآ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءٖ مُّحِيطُۢ
ንቁ! እነርሱ ከጌታቸው መገናኘት በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ንቁ! እርሱ በነገሩ ሁሉ (ዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

បានបកប្រែដោយលោកម៉ូហាំម៉ាត់ សទុីក និងលោកអាស់សានី ហាប៊ុីប។ ត្រូវបានអភិវឌ្ឍន៍ដោយការត្រួតពិនិត្យពីមជ្ឍមណ្ឌលបកប្រែរ៉ូវ៉ាទ ការបកប្រែដើមអាចចូលមើលបានក្នុងគោលបំណងផ្តល់យោបល់ វាយតម្លៃ និងអភិវឌ្ឍន៍បន្ត។

បិទ