Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: យូនូស   អាយ៉ាត់:
أَلَآ إِنَّ أَوۡلِيَآءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
62. አስተውሉ! የአላህ ወዳጆች ፍርሀት የለባቸዉም። አይተክዙምም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ
63. እነርሱም እነዚያ ያመኑትና አላህን የሚፈሩት ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَهُمُ ٱلۡبُشۡرَىٰ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ لَا تَبۡدِيلَ لِكَلِمَٰتِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
64. ለእነርሱ በቅርቢቱ ህይወትም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብስራት አለላቸው:: የአላህ ቃል አይለወጥም:: ይህ እርሱ ታላቅ እድል (ስኬታማነት) ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا يَحۡزُنكَ قَوۡلُهُمۡۘ إِنَّ ٱلۡعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًاۚ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: ኃይል በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና:: እርሱም ሰሚውና ሁሉን አዋቂው ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَمَا يَتَّبِعُ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُرَكَآءَۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ
66. አስተውሉ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَسۡمَعُونَ
67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተአምራት አሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۖ هُوَ ٱلۡغَنِيُّۖ لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ إِنۡ عِندَكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭ بِهَٰذَآۚ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
68. «አላህ ልጅን ወለደ።» አሉ። ከሚሉት ሁሉ ጥራት ተገባው:: እርሱ በራሱ ተብቃቂ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እናንተ ዘንድ በዚህ በምትሉት ምንም አስረጂ የላችሁም:: በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ لَا يُفۡلِحُونَ
69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች ፈጽሞ አይድኑም።» በላቸው
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَتَٰعٞ فِي ٱلدُّنۡيَا ثُمَّ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ ثُمَّ نُذِيقُهُمُ ٱلۡعَذَابَ ٱلشَّدِيدَ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ
70. እነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ጥቂት ጊዜ ይጠቀሙና ከዚያም መመለሻቸው ወደ እኛ ነው:: ከዚያም ይክዱ በነበሩበት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: យូនូស
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ