Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ៊ូទ   អាយ៉ាត់:
وَيَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مَالًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۚ وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْۚ إِنَّهُم مُّلَٰقُواْ رَبِّهِمۡ وَلَٰكِنِّيٓ أَرَىٰكُمۡ قَوۡمٗا تَجۡهَلُونَ
29. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ የተላክሁበትን በማድረስ ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም:: እኔም እነዚያን በአላህ ያመኑትን ከአጠገቤ አባራሪ አይደለሁም:: እነርሱ ከጌታቸው ጋር የሚገናኙ ናቸውና:: ግን እኔም የምትሳሳቱ ህዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَٰقَوۡمِ مَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِن طَرَدتُّهُمۡۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
30. «ህዝቦቼ ሆይ! ባባርራቸው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማን ነው? አትገሰጹምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ وَلَآ أَقُولُ إِنِّي مَلَكٞ وَلَآ أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزۡدَرِيٓ أَعۡيُنُكُمۡ لَن يُؤۡتِيَهُمُ ٱللَّهُ خَيۡرًاۖ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا فِيٓ أَنفُسِهِمۡ إِنِّيٓ إِذٗا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
31. «ለናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አሉ:: ሩቅንም አውቃለሁ አልላችሁም:: እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም:: ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን እምነትን አይሰጣቸዉም አልልም:: አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር አዋቂ ነው:: እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና።» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالُواْ يَٰنُوحُ قَدۡ جَٰدَلۡتَنَا فَأَكۡثَرۡتَ جِدَٰلَنَا فَأۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
32. «ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን:: እኛን መከራከርህንም አበዛህ:: ከእውነተኞቹም ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው እስቲ።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ إِنَّمَا يَأۡتِيكُم بِهِ ٱللَّهُ إِن شَآءَ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ
33. አላቸውም: «እርሱን የሚያመጣባችሁ አላህ የፈለገ ከሆነ ብቻ ነው። እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا يَنفَعُكُمۡ نُصۡحِيٓ إِنۡ أَرَدتُّ أَنۡ أَنصَحَ لَكُمۡ إِن كَانَ ٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغۡوِيَكُمۡۚ هُوَ رَبُّكُمۡ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
34. «እናንተም አላህ ሊያጠማችሁ ፈልጎ ከሆነ ልመክራችሁ ብፈልግም ምክሬ አይጠቅማችሁም:: እርሱ ጌታችሁ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ።» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ إِنِ ٱفۡتَرَيۡتُهُۥ فَعَلَيَّ إِجۡرَامِي وَأَنَا۠ بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُجۡرِمُونَ
35. ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? (ሙሐመድ ሆይ) «ብቀጥፈው ኃጢአቴ ቅጣቱ በእኔ ላይ ነው:: እኔም ከምታጠፉት ጥፋት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأُوحِيَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُۥ لَن يُؤۡمِنَ مِن قَوۡمِكَ إِلَّا مَن قَدۡ ءَامَنَ فَلَا تَبۡتَئِسۡ بِمَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ
36. ወደ ኑህም (እንዲህ በሚል) ተወረደ: «እነሆ ከህዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር ወደፊት ሌሎች አያምኑም:: ይሠሩትም በነበሩት ክህደት አትዘን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ
37. «በጥበቃችንና በትዕዛዛችን ሆነህ መርከቢቱን ሥራ። በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ። እነርሱ በእርግጥ የሚሰምጡ ናቸውና።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ៊ូទ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ