Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហាជ្ជ   អាយ៉ាត់:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٞ فَٱسۡتَمِعُواْ لَهُۥٓۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَن يَخۡلُقُواْ ذُبَابٗا وَلَوِ ٱجۡتَمَعُواْ لَهُۥۖ وَإِن يَسۡلُبۡهُمُ ٱلذُّبَابُ شَيۡـٔٗا لَّا يَسۡتَنقِذُوهُ مِنۡهُۚ ضَعُفَ ٱلطَّالِبُ وَٱلۡمَطۡلُوبُ
73. ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ:: ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ሁሉ ዝንብን ለመፍጠር ቢሰበሰቡ ፈጽሞ መፍጠር እንኳ አይችሉም:: አንዳችንም ነገር ዝንብ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም:: ፈላጊዉም (አምላኪው) ተፈላጊዉም (ተመላኪው) ደከሙ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَا قَدَرُواْ ٱللَّهَ حَقَّ قَدۡرِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ
74. አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም:: አላህ በጣም ሀያልና ሁሉን አሸናፊ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ يَصۡطَفِي مِنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلٗا وَمِنَ ٱلنَّاسِۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٞ
75. አላህ ከመላእክት ውስጥ መልዕክተኞችን ይመርጣል:: ከሰዎችም መካከል እንደዚሁ መልዕክተኞችን ይመርጣል:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
76. በስተፊታቸዉም ሆነ በስተኋላቸው ያለን ሁሉ ያውቃል:: ወደ አላህም ነገሮች ሁሉ ይመለሳሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱرۡكَعُواْ وَٱسۡجُدُواْۤ وَٱعۡبُدُواْ رَبَّكُمۡ وَٱفۡعَلُواْ ٱلۡخَيۡرَ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ۩
77. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአላህ ቁጣ ትድኑ ዘንድ በስግደታችሁ አጎንብሱ:: በግንባራችሁም ላይ ተደፉ:: (ሩኩዕና ሱጁድ አድርጉ) ጌታችሁንም በትክክል ተገዙት:: በጎንም ነገር ስሩ:: ልትድኑ ይከጀልላችኋልና:: {1}
{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁድ ትላዋ) ይደረጋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَجَٰهِدُواْ فِي ٱللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِۦۚ هُوَ ٱجۡتَبَىٰكُمۡ وَمَا جَعَلَ عَلَيۡكُمۡ فِي ٱلدِّينِ مِنۡ حَرَجٖۚ مِّلَّةَ أَبِيكُمۡ إِبۡرَٰهِيمَۚ هُوَ سَمَّىٰكُمُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ مِن قَبۡلُ وَفِي هَٰذَا لِيَكُونَ ٱلرَّسُولُ شَهِيدًا عَلَيۡكُمۡ وَتَكُونُواْ شُهَدَآءَ عَلَى ٱلنَّاسِۚ فَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱعۡتَصِمُواْ بِٱللَّهِ هُوَ مَوۡلَىٰكُمۡۖ فَنِعۡمَ ٱلۡمَوۡلَىٰ وَنِعۡمَ ٱلنَّصِيرُ
78. በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ:: እርሱ መርጧችኋል:: በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም:: የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ:: እርሱ (አላህ) ከዚህ በፊት በነበሩት መጽሐፍትም ሆነ በዚህ ቁርኣን ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል። (ይሄዉም) መልዕክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እና እናንተም በሰዎች ላይ መስካሪዎች እንድትሆኑ ነው:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም በአግባቡ ለተገቢው ስጡ:: በአላህም ተጠበቁ:: እርሱ ረዳታችሁ ነውና:: እርሱ ምን ያማረ ጠባቂ፤ ምን ያማረም ረዳት ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហាជ្ជ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ