Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អើររ៉ូម   អាយ៉ាត់:

አር ሩም

الٓمٓ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
غُلِبَتِ ٱلرُّومُ
2. ሩም (በፋርሶች) ተሸነፈች፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فِيٓ أَدۡنَى ٱلۡأَرۡضِ وَهُم مِّنۢ بَعۡدِ غَلَبِهِمۡ سَيَغۡلِبُونَ
3. በጣም (ለዐረቡ ዓለም) ቅርብ በሆነችው ምድር ላይ እነርሱም (ከሶስት አመት ያላነሰ ከዘጠኝ ባልበለጠ በጥቂት አመታት ውስጥ) ከመሸነፋቸው በኋላ ያሸንፋሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فِي بِضۡعِ سِنِينَۗ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡرُ مِن قَبۡلُ وَمِنۢ بَعۡدُۚ وَيَوۡمَئِذٖ يَفۡرَحُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ
4. (ከሶስት አመት ያላነሰ ከዘጠኝ ባልበለጠ) በጥቂት አመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)። ጉዳዩ በፊትም ሆነ በኋላ የአላህ ነውና:: በዚያ ቀንም ምዕምናን ይደሰታሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
بِنَصۡرِ ٱللَّهِۚ يَنصُرُ مَن يَشَآءُۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
5. በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ይረዳል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَعۡدَ ٱللَّهِۖ لَا يُخۡلِفُ ٱللَّهُ وَعۡدَهُۥ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
6. አላህ እርዳታን በቁርጥ ቀጠረ:: አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያውቁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَعۡلَمُونَ ظَٰهِرٗا مِّنَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُمۡ عَنِ ٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ غَٰفِلُونَ
7. ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ:: እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም ፍጹም ዘንጊዎች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوَلَمۡ يَتَفَكَّرُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۗ مَّا خَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَأَجَلٖ مُّسَمّٗىۗ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِ بِلِقَآيِٕ رَبِّهِمۡ لَكَٰفِرُونَ
8. በነፍሶቻቸው ሁኔታ አያስተውሉምን ? ሰማያትን፤ ምድርንና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸዉም:: ከሰዎች መካከል ብዙዎቹ ከጌታቸው ጋር በመገናኘት ከሓዲያን ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗ وَأَثَارُواْ ٱلۡأَرۡضَ وَعَمَرُوهَآ أَكۡثَرَ مِمَّا عَمَرُوهَا وَجَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
9. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር አይመለከቱምን? በኃይል ከእነርሱ ይበልጡ ነበሩ:: ምድርንም አረሱ:: እነዚህ ከአለሟትም የበለጠ አለሟት:: መልዕክተኞቻቸዉም በተአምራቶች መጡባቸው:: ግና አስተባበሉና ጠፉ:: አላህም የሚበድላቸው አልነበረም:: ግና ነፍሶቻቸውን በራሳቸው ይበድሉ ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ كَانَ عَٰقِبَةَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ ٱلسُّوٓأَىٰٓ أَن كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَكَانُواْ بِهَا يَسۡتَهۡزِءُونَ
10. ከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አናቅጽ ማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳሳቁ የሚያፌዙ መሆናቸው (ምክንያት መጥፎ ቅጣት) ሆነ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
11. አላህ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም ይመልሰዋል:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳለችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُبۡلِسُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ
12. ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ (ተስፋ ይቆርጣሉ)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَمۡ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَآئِهِمۡ شُفَعَٰٓؤُاْ وَكَانُواْ بِشُرَكَآئِهِمۡ كَٰفِرِينَ
13. ለእነርሱም ከሚያጋሯቸው ጣዖታት መካከል አማላጆች አይኖሩዋቸዉም:: በሚያጋሯቸዉም ጣዖታት ከሓዲያን ይሆናሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوۡمَئِذٖ يَتَفَرَّقُونَ
14. ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን በዚያ ቀን ይለያያሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَهُمۡ فِي رَوۡضَةٖ يُحۡبَرُونَ
15. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካሞችን ስራዎች የሰሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآيِٕ ٱلۡأٓخِرَةِ فَأُوْلَٰٓئِكَ فِي ٱلۡعَذَابِ مُحۡضَرُونَ
16. እነዚያም በአላህ የካዱትማ በአናቅጻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ حِينَ تُمۡسُونَ وَحِينَ تُصۡبِحُونَ
17. አላህንም በምታመሹና በምታነጉም ጊዜ አጥሩት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَعَشِيّٗا وَحِينَ تُظۡهِرُونَ
18. ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለእርሱ ብቻ የተገባው ነው:: በሰርክም በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ አጥሩት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَيُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ وَكَذَٰلِكَ تُخۡرَجُونَ
19. ህያውን ከሙት ያወጣል:: ሙትንም ከህያው ያወጣል:: ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል:: ልክ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنۡ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ إِذَآ أَنتُم بَشَرٞ تَنتَشِرُونَ
20. እናንተንም ከአፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنۡ خَلَقَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجٗا لِّتَسۡكُنُوٓاْ إِلَيۡهَا وَجَعَلَ بَيۡنَكُم مَّوَدَّةٗ وَرَحۡمَةًۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
21. ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ خَلۡقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَٰفُ أَلۡسِنَتِكُمۡ وَأَلۡوَٰنِكُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّلۡعَٰلِمِينَ
22. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለአዋቂዎች አያሌ ታዐምራት አሉበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ مَنَامُكُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَٱبۡتِغَآؤُكُم مِّن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَسۡمَعُونَ
23. በሌሊትም ሆነ በቀን መተኛታችሁ ከችሮታዉም መፈለጋችሁም ከምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ታዐምራት አሉበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ يُرِيكُمُ ٱلۡبَرۡقَ خَوۡفٗا وَطَمَعٗا وَيُنَزِّلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَيُحۡيِۦ بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
24. ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ታዐምራት አሉበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَن تَقُومَ ٱلسَّمَآءُ وَٱلۡأَرۡضُ بِأَمۡرِهِۦۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمۡ دَعۡوَةٗ مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ إِذَآ أَنتُمۡ تَخۡرُجُونَ
25. ሰማይና ምድርም ያለ ምሰሶ በትእዛዙ መቆማቸው ከዚያም መልአክ ለትንሳኤ ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ كُلّٞ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
26. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَهُوَ ٱلَّذِي يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَهُوَ أَهۡوَنُ عَلَيۡهِۚ وَلَهُ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
27. እርሱ ያ ፍጡራንን ከምንም የሚጀምር (የሚያስገኝ) ከዚያም የሚመልሳቸው ብቸኛ አምላክ ነው:: መመለሱም በእርሱ ላይ በጣም ቀላል ነው:: ለእርሱም በሰማያትና በምድር ከፍተኛው ምሳሌ (ባህሪ) አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ضَرَبَ لَكُم مَّثَلٗا مِّنۡ أَنفُسِكُمۡۖ هَل لَّكُم مِّن مَّا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُم مِّن شُرَكَآءَ فِي مَا رَزَقۡنَٰكُمۡ فَأَنتُمۡ فِيهِ سَوَآءٞ تَخَافُونَهُمۡ كَخِيفَتِكُمۡ أَنفُسَكُمۡۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
28. (ጣዖት አምላኪዎች ሆይ!) ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ የሆነን ምሳሌ አደረገላችሁ:: እርሱም እጆቻችሁ ከያዟቸው ባሮች ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለእናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በእርሱ እኩል ለኩል (ትክክል) ናችሁን? ነፍሶቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንደምትፈሩ ትፈሯቸዋላችሁን ? ልክ እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እንገልጻለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
بَلِ ٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَهۡوَآءَهُم بِغَيۡرِ عِلۡمٖۖ فَمَن يَهۡدِي مَنۡ أَضَلَّ ٱللَّهُۖ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ
29. ይልቁንም እነዚህ የበደሉ ሰዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ:: አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَقِمۡ وَجۡهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفٗاۚ فِطۡرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِي فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيۡهَاۚ لَا تَبۡدِيلَ لِخَلۡقِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلۡقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እውነት ተዘንባይ ሆነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ:: የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርሷ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት (ያዟት):: የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ مُنِيبِينَ إِلَيۡهِ وَٱتَّقُوهُ وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَلَا تَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
31. ወደ እርሱ ተመላሾች ሆናችሁ የአላህን ሃይማኖት ያዙ:: ፍሩትም:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ከአጋሪዎችም አትሁኑ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مِنَ ٱلَّذِينَ فَرَّقُواْ دِينَهُمۡ وَكَانُواْ شِيَعٗاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ
32. ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍልም ከሆኑት አትሁኑ:: ህዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ብቻ ተደሳቾች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا مَسَّ ٱلنَّاسَ ضُرّٞ دَعَوۡاْ رَبَّهُم مُّنِيبِينَ إِلَيۡهِ ثُمَّ إِذَآ أَذَاقَهُم مِّنۡهُ رَحۡمَةً إِذَا فَرِيقٞ مِّنۡهُم بِرَبِّهِمۡ يُشۡرِكُونَ
33. ሰዎችንም ችግር ባገኛቸው ጊዜ ጌታቸውን ወደ እርሱ ተመላሾች ሆነው ይጠሩታል:: ከዚያም ከእርሱ ችሮታንም ባቀመሳቸው ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ በጌታቸው ጣዖትን ያጋራሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لِيَكۡفُرُواْ بِمَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡۚ فَتَمَتَّعُواْ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ
34. በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱ (ያጋራሉ):: ተጣቀሙም:: በእርግጥም መጨረሻችሁን ወደፊት ታውቃላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمۡ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٗا فَهُوَ يَتَكَلَّمُ بِمَا كَانُواْ بِهِۦ يُشۡرِكُونَ
35. በእነርሱ ላይ አላህ አስረጅን አወረደን? ታድያ እርሱ በነዚያ በእርሱ ያጋሩ በነበሩት ነገር ይናገራልን? የለም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَآ أَذَقۡنَا ٱلنَّاسَ رَحۡمَةٗ فَرِحُواْ بِهَاۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ إِذَا هُمۡ يَقۡنَطُونَ
36. ሰዎችንም ችሮታን ባቀመስናቸው ጊዜ በእርሷ ይደሰታሉ:: እጆቻቸዉም ባሳለፉት ምክንያት መከራ ብታገኛቸው ወዲያውኑ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
37. አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አሉበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَـَٔاتِ ذَا ٱلۡقُرۡبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلۡمِسۡكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ يُرِيدُونَ وَجۡهَ ٱللَّهِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
38.ስለዚህ (አማኝ ሆይ!) የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው:: ለድሃም ለመንገደኛም እርዳ:: ይህ ለእነዚያ የአላህን ፊት ለሚሹ ሁሉ መልካም ነው:: እነዚያ እነርሱም በሁለተኛው ዓለም የፈለጉትን የሚያገኙ ምርጥ ክፍሎች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَآ ءَاتَيۡتُم مِّن رِّبٗا لِّيَرۡبُوَاْ فِيٓ أَمۡوَٰلِ ٱلنَّاسِ فَلَا يَرۡبُواْ عِندَ ٱللَّهِۖ وَمَآ ءَاتَيۡتُم مِّن زَكَوٰةٖ تُرِيدُونَ وَجۡهَ ٱللَّهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُضۡعِفُونَ
39. (ሰዎች ሆይ!) በሰዎች ውስጥም ይጨመር ዘንድ በማቀድ የምትሰጡት ገንዘብ በአላህ ዘንድ ቅንጣት አይጨምርም:: የአላህን ፊት ብቻ የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት ምጽዋት ግን እነዚያ እውነተኛ ሰጪዎች (አበርካቾች) እነርሱ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ ثُمَّ رَزَقَكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يُحۡيِيكُمۡۖ هَلۡ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَفۡعَلُ مِن ذَٰلِكُم مِّن شَيۡءٖۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
40. አላህ ያ የፈጠራችሁ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ህያው የሚያደርጋችሁ ነው:: ከምታጋሯቸው ጣዖታት ውስጥ ከዚሃችሁ አንዳችን የሚሰራ አለን? ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ظَهَرَ ٱلۡفَسَادُ فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ بِمَا كَسَبَتۡ أَيۡدِي ٱلنَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعۡضَ ٱلَّذِي عَمِلُواْ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
41. የሰዎች እጆች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት የዚያን የሰሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባህር ተገለጠ (ተሰራጨ)። እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلُۚ كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّشۡرِكِينَ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የእነዚያንም በፊት የነበሩት ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው:: አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَقِمۡ وَجۡهَكَ لِلدِّينِ ٱلۡقَيِّمِ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَ يَوۡمٞ لَّا مَرَدَّ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِۖ يَوۡمَئِذٖ يَصَّدَّعُونَ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን የትንሳኤ ቀን ከአላህ ሳይመጣ በፊት ፊትህን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ አድርግ :: በዚያ ቀን ወደ ገነትና ወደ እሳት ይለያያሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَن كَفَرَ فَعَلَيۡهِ كُفۡرُهُۥۖ وَمَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِأَنفُسِهِمۡ يَمۡهَدُونَ
44. በአላህ የካደ ሰው የክህደቱ ጠንቁ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: መልካምም የሰሩ ሁሉ ለነፍሶቻቸው ማረፊያዎችን ያዘጋጃሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡكَٰفِرِينَ
45. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሰሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ (ይለያያሉ):: እርሱ ከሓዲያንን አይወድምና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَن يُرۡسِلَ ٱلرِّيَاحَ مُبَشِّرَٰتٖ وَلِيُذِيقَكُم مِّن رَّحۡمَتِهِۦ وَلِتَجۡرِيَ ٱلۡفُلۡكُ بِأَمۡرِهِۦ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
46. (ሰዎች ሆይ!) ንፋሶችንም (በዝናብ) ልታበስራችሁ ከችሮታዉም (በእርሷ) ሊያቀምሳችሁ መርከቦችም በትእዛዙ እንዲንሻለሉ ከችሮታዉም እንድትፈልጉ ታመሰግኑትም ዘንድ መላኩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ رُسُلًا إِلَىٰ قَوۡمِهِمۡ فَجَآءُوهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَٱنتَقَمۡنَا مِنَ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْۖ وَكَانَ حَقًّا عَلَيۡنَا نَصۡرُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም መልዕክተኞችን ወደ የህዝቦቻቸው በእርግጥ ላክን:: በግልጽ ማስረጃዎችም መጡባቸው:: ከእነዚያ ካመጹትም ተበቀልን:: ምዕመናኖችንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي يُرۡسِلُ ٱلرِّيَٰحَ فَتُثِيرُ سَحَابٗا فَيَبۡسُطُهُۥ فِي ٱلسَّمَآءِ كَيۡفَ يَشَآءُ وَيَجۡعَلُهُۥ كِسَفٗا فَتَرَى ٱلۡوَدۡقَ يَخۡرُجُ مِنۡ خِلَٰلِهِۦۖ فَإِذَآ أَصَابَ بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦٓ إِذَا هُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ
48. አላህ ያ ! ንፋሶችን የሚልክ ነው:: ደመናንም ይቀሰቅሳል:: በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል :: ቁርጥራጮችም ያደርገዋል:: ዝናቡንም ከደመናው መካከል ሲወጣ ታያለህ:: በእርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይደሰታሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن كَانُواْ مِن قَبۡلِ أَن يُنَزَّلَ عَلَيۡهِم مِّن قَبۡلِهِۦ لَمُبۡلِسِينَ
49. በእነርሱም ላይ ከመውረዱ በፊት ከእርሱ በፊት በእርግጥ ተስፋ ቆራጮች ነበሩ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱنظُرۡ إِلَىٰٓ ءَاثَٰرِ رَحۡمَتِ ٱللَّهِ كَيۡفَ يُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
50. ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ህያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ችሮታ ፈለጎች ተመልከት:: ይህን አድራጊ ጌታ ሙታንንም በእርግጥ ህያው አድራጊ ነው :: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَئِنۡ أَرۡسَلۡنَا رِيحٗا فَرَأَوۡهُ مُصۡفَرّٗا لَّظَلُّواْ مِنۢ بَعۡدِهِۦ يَكۡفُرُونَ
51. ንፋስንም በአዝመራዎች ላይ ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከእርሱ በኋላ በእርግጥ ችሮታውን የሚክዱ ይሆናሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِنَّكَ لَا تُسۡمِعُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَلَا تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوۡاْ مُدۡبِرِينَ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሙታንን አታሰማም:: ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥሪን አታሰማም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِ ٱلۡعُمۡيِ عَن ضَلَٰلَتِهِمۡۖ إِن تُسۡمِعُ إِلَّا مَن يُؤۡمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسۡلِمُونَ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ እውሮችንም ከጥመታቸው የምታቀና አይደለህም:: በአናቅጻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም:: እነርሱም ታዛዦች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن ضَعۡفٖ ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعۡدِ ضَعۡفٖ قُوَّةٗ ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٖ ضَعۡفٗا وَشَيۡبَةٗۚ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ وَهُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡقَدِيرُ
54. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ ከደካማ ፍትወት ጠብታ የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያ ከደካማነት በኋላም ኃይልን አደረገ:: ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትና ሽበትንም አደረገ:: የሚሻውን ይፈጥራል:: እርሱም ሁሉን አዋቂውና ቻዩ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُقۡسِمُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ مَا لَبِثُواْ غَيۡرَ سَاعَةٖۚ كَذَٰلِكَ كَانُواْ يُؤۡفَكُونَ
55. ሰዓቲቱ በምትከሰትበት ቀን ከሓዲያን «ከአንዲት ሰዓት በስተቀር በመቃብር (በዱንያ) አልቆየንም።» ብለው ይምላሉ:: ልክ እንደዚሁ በዚህኛው ዐለምም እያሉ ከእውነት ይመለሱ ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ وَٱلۡإِيمَٰنَ لَقَدۡ لَبِثۡتُمۡ فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡبَعۡثِۖ فَهَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡبَعۡثِ وَلَٰكِنَّكُمۡ كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ
56. እነዚያም እውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ ፍርድ እስከ ትንሳኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ ይህም የካዳችሁት የትንሳኤ ቀን ነው:: ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ።» ይሏቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَعۡذِرَتُهُمۡ وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ
57. በዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ ضَرَبۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖۚ وَلَئِن جِئۡتَهُم بِـَٔايَةٖ لَّيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا مُبۡطِلُونَ
58. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች የምሳሌ አይነቶችን ሁሉ በእርግጥ ገለጽን:: በተዓምርን ብታመጣላቸው እንኳን እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች የጥፋት ተጣሪ ዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» ይላሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ
59 ልክ እንደዚሁ አላህ በነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱصۡبِرۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۖ وَلَا يَسۡتَخِفَّنَّكَ ٱلَّذِينَ لَا يُوقِنُونَ
60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለዚህ ታገሥ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: እነዚያም በትንሳኤ የማያረጋግጡት ሰዎች አያቅልሉህ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អើររ៉ូម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ