Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាន់នីសាក   អាយ៉ាត់:
وَمَا كَانَ لِمُؤۡمِنٍ أَن يَقۡتُلَ مُؤۡمِنًا إِلَّا خَطَـٔٗاۚ وَمَن قَتَلَ مُؤۡمِنًا خَطَـٔٗا فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مُّؤۡمِنَةٖ وَدِيَةٞ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦٓ إِلَّآ أَن يَصَّدَّقُواْۚ فَإِن كَانَ مِن قَوۡمٍ عَدُوّٖ لَّكُمۡ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مُّؤۡمِنَةٖۖ وَإِن كَانَ مِن قَوۡمِۭ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُم مِّيثَٰقٞ فَدِيَةٞ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ وَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مُّؤۡمِنَةٖۖ فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ شَهۡرَيۡنِ مُتَتَابِعَيۡنِ تَوۡبَةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا
92. አማኝ በስህተት ካልሆነ በስተቀር አማኝን መግደል አይገባዉም:: አማኝን በስህተት የገደለም አማኝ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ምህረት ካላደረጉለት በስተቀር ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማ መክፈል አለበት:: ተገዳዩ ምዕመን ሆኖ ለእናንተ ጠላት ከሆኑ ህዝቦች ዘንድ ቢሆንም አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ተገዳዩ በእናንተ እና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ካላቸዉም ህዝቦች ጋር ቢሆን ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማና አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ይህንን ያላገኘም በተከታታይ ሁለት ወሮችን መፆም አለበት:: ከአላህ የሆነ ጸጸት (ለመቀበል ደነገገላችሁ::) አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَن يَقۡتُلۡ مُؤۡمِنٗا مُّتَعَمِّدٗا فَجَزَآؤُهُۥ جَهَنَّمُ خَٰلِدٗا فِيهَا وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ وَلَعَنَهُۥ وَأَعَدَّ لَهُۥ عَذَابًا عَظِيمٗا
93. አማኝን አስቦ የሚገድል ቅጣቱ በውስጧ ዘወታሪ ሲሆን ገሀነም ናት:: አላህ በእርሱ ላይ ተቆጣ:: ረገመዉም:: ለእርሱ ከባድ ቅጣትን አዘጋጀቶለታል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا ضَرَبۡتُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَتَبَيَّنُواْ وَلَا تَقُولُواْ لِمَنۡ أَلۡقَىٰٓ إِلَيۡكُمُ ٱلسَّلَٰمَ لَسۡتَ مُؤۡمِنٗا تَبۡتَغُونَ عَرَضَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا فَعِندَ ٱللَّهِ مَغَانِمُ كَثِيرَةٞۚ كَذَٰلِكَ كُنتُم مِّن قَبۡلُ فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمۡ فَتَبَيَّنُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٗا
94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ለመዋጋት በተጓዛችሁ ጊዜ አረጋግጡ:: ሰላምታን ወደ እናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ሆናችሁ «ትክክለኛ አማኝ አይደለህም።» አትበሉት:: አላህ ዘንድ ብዙ ምርኮዎች አሉና:: እናንተም ከዚህ በፊት ልክ እንደዚሁ ነበራችሁ:: አላህ በእናንተ ላይ ለገሰ:: ስለዚህም አረጋግጡ:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាន់នីសាក
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ