Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ


ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ៊ូជូរ៉ត   អាយ៉ាត់:
وَلَوۡ أَنَّهُمۡ صَبَرُواْ حَتَّىٰ تَخۡرُجَ إِلَيۡهِمۡ لَكَانَ خَيۡرٗا لَّهُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
5. ወደ እነርሱም እስክትወጣ ድረስ ዝምብለው በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በሆነ ነበር:: አላህም እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن جَآءَكُمۡ فَاسِقُۢ بِنَبَإٖ فَتَبَيَّنُوٓاْ أَن تُصِيبُواْ قَوۡمَۢا بِجَهَٰلَةٖ فَتُصۡبِحُواْ عَلَىٰ مَا فَعَلۡتُمۡ نَٰدِمِينَ
6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬ ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ህዝባችሁን እንዳትጎዱና ከዚያም በሰራችሁት ነገር ላይ ተጸፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ فِيكُمۡ رَسُولَ ٱللَّهِۚ لَوۡ يُطِيعُكُمۡ فِي كَثِيرٖ مِّنَ ٱلۡأَمۡرِ لَعَنِتُّمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ حَبَّبَ إِلَيۡكُمُ ٱلۡإِيمَٰنَ وَزَيَّنَهُۥ فِي قُلُوبِكُمۡ وَكَرَّهَ إِلَيۡكُمُ ٱلۡكُفۡرَ وَٱلۡفُسُوقَ وَٱلۡعِصۡيَانَۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلرَّٰشِدُونَ
7. በውስጣችሁም የአላህ መልዕክተኛ መኖሩን እወቁ:: ከነገሩ በብዙው ነገሮች ቢከተላችሁ ኖሮ በእርግጥ በተቸገራችሁ ነበር:: ግን አላህ እምነትን ወደ እናንተ አስወደደ :: በልቦቻችሁም ውስጥ አስዋበው። ክህደትን፣ አመፅንና እምቢተኝነትንም ለናንተ የተጠላ አደረገ። እነዚያ እምነትን የወደዱና ክሕደትን የጠሉ ሰዎች እነርሱ ትክክለኛ ቅኖቹ ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَضۡلٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَنِعۡمَةٗۚ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
8. ከአላህ በሆነው ችሮታና ጸጋ ሲሆን ቅኖች ናቸው። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن طَآئِفَتَانِ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱقۡتَتَلُواْ فَأَصۡلِحُواْ بَيۡنَهُمَاۖ فَإِنۢ بَغَتۡ إِحۡدَىٰهُمَا عَلَى ٱلۡأُخۡرَىٰ فَقَٰتِلُواْ ٱلَّتِي تَبۡغِي حَتَّىٰ تَفِيٓءَ إِلَىٰٓ أَمۡرِ ٱللَّهِۚ فَإِن فَآءَتۡ فَأَصۡلِحُواْ بَيۡنَهُمَا بِٱلۡعَدۡلِ وَأَقۡسِطُوٓاْۖ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُقۡسِطِينَ
9. ሁለት የምዕምናን ቡድኖች እርስ በእርስ ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ:: ከሁለት አንደኛይቱ በሌላኛይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመጣ ድረስ ተጋደሏት፤ ብትመለስ ግን በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ:: በነገሩ ሁሉ አስተካክሉ:: አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ إِخۡوَةٞ فَأَصۡلِحُواْ بَيۡنَ أَخَوَيۡكُمۡۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
10.(አማኞች ሆይ!) ምዕመናኖች ወንድማማቾች ናቸውና በሁለት ወንድሞቻችሁ መካከል አስታርቁ:: ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا يَسۡخَرۡ قَوۡمٞ مِّن قَوۡمٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُونُواْ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَلَا نِسَآءٞ مِّن نِّسَآءٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُنَّ خَيۡرٗا مِّنۡهُنَّۖ وَلَا تَلۡمِزُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ وَلَا تَنَابَزُواْ بِٱلۡأَلۡقَٰبِۖ بِئۡسَ ٱلِٱسۡمُ ٱلۡفُسُوقُ بَعۡدَ ٱلۡإِيمَٰنِۚ وَمَن لَّمۡ يَتُبۡ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
11.እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች በወንዶች አይሳለቁ:: ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና:: ሴቶችም በሴቶች አይሳለቁ:: ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና:: ነፍሶቻችሁንም አታነዉሩ በመጥፎ ሰሞችም አትጠራሩ:: ከእምነት በኋላ መጥፎ ስም ከፋ:: ያልተጸጸተ ሰው በእውነት እነርሱ በዳዮቹ ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ៊ូជូរ៉ត
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ