Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់ហ្វាល   អាយ៉ាត់:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ لَمۡ يَكُ مُغَيِّرٗا نِّعۡمَةً أَنۡعَمَهَا عَلَىٰ قَوۡمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُواْ مَا بِأَنفُسِهِمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
53. ይህ ቅጣት አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመሆኑ ምክንያት ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَغۡرَقۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَۚ وَكُلّٞ كَانُواْ ظَٰلِمِينَ
54. እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያ ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸዉም)። በጌታቸው ታዓምራት አስተባበሉና በኃጢአቶቻቸው አጠፋናቸው:: የፈርዖንን ቤተሰቦች አስመጥናቸው:: ሁሉም በዳዮች ነበሩና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
55. ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ የካዱት ሰዎች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ عَٰهَدتَّ مِنۡهُمۡ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهۡدَهُمۡ فِي كُلِّ مَرَّةٖ وَهُمۡ لَا يَتَّقُونَ
56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከእነርሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸውና ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው:: እነርሱም አይጠነቀቁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِمَّا تَثۡقَفَنَّهُمۡ فِي ٱلۡحَرۡبِ فَشَرِّدۡ بِهِم مَّنۡ خَلۡفَهُمۡ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ
57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦር ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት ሌሎቹ ከሓዲያን ይገሠጡ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِمَّا تَخَافَنَّ مِن قَوۡمٍ خِيَانَةٗ فَٱنۢبِذۡ إِلَيۡهِمۡ عَلَىٰ سَوَآءٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡخَآئِنِينَ
58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦችም በኩል ክህደትን ብትፈራ የቃል ኪዳኑን መፍረስ በማወቅ በኩል ተመሳሳይ ሆናችሁ ቃል ኪዳናቸውን ወደ እነርሱ ጣልላቸው:: አላህ ከዳተኞችን ሁሉ አይወድምና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا يَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ سَبَقُوٓاْۚ إِنَّهُمۡ لَا يُعۡجِزُونَ
59. እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መሆናቸውን አያስቡ:: እነርሱ አያቅቱምና (አያሸንፉምና)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَعِدُّواْ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةٖ وَمِن رِّبَاطِ ٱلۡخَيۡلِ تُرۡهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمۡ وَءَاخَرِينَ مِن دُونِهِمۡ لَا تَعۡلَمُونَهُمُ ٱللَّهُ يَعۡلَمُهُمۡۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِن شَيۡءٖ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ يُوَفَّ إِلَيۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ
60. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ለእነርሱ ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶች የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በስተቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ ብቻ የሚያውቃቸውን አስመሳዮች የምታሸብሩበት ስትሆኑ አዘጋጁላቸው:: ከማንኛዉም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱት ምንዳው ወደ እናንተ በሙሉ ይሰጣል:: እናንተ ቅንጣት አትበደሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ وَإِن جَنَحُواْ لِلسَّلۡمِ فَٱجۡنَحۡ لَهَا وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዕርቅ ቢያዘነብሉ አንተም ወደ እርቁ ተዘንበልና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂው ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់ហ្វាល
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ