Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ


ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅರ್‍ರಅ್ ದ್   ಶ್ಲೋಕ:
وَيَسۡتَعۡجِلُونَكَ بِٱلسَّيِّئَةِ قَبۡلَ ٱلۡحَسَنَةِ وَقَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِمُ ٱلۡمَثُلَٰتُۗ وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغۡفِرَةٖ لِّلنَّاسِ عَلَىٰ ظُلۡمِهِمۡۖ وَإِنَّ رَبَّكَ لَشَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎ ያስቸኩሉሃል! ጌታህም ለሰዎች ሁሉ ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው:: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ብርቱም ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦٓۗ إِنَّمَآ أَنتَ مُنذِرٞۖ وَلِكُلِّ قَوۡمٍ هَادٍ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተአምር ለምን አልተወረደለትም?» ይላሉ:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፤ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አለላቸው።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
ٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا تَحۡمِلُ كُلُّ أُنثَىٰ وَمَا تَغِيضُ ٱلۡأَرۡحَامُ وَمَا تَزۡدَادُۚ وَكُلُّ شَيۡءٍ عِندَهُۥ بِمِقۡدَارٍ
8. አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ጽንስ ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: ማሕጸኖች የሚያጎድሉትንም ሆነ የሚጨምሩትን ያውቃል:: ነገሩ ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلۡكَبِيرُ ٱلۡمُتَعَالِ
9. ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ታላቅና የላቀ ጌታ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
سَوَآءٞ مِّنكُم مَّنۡ أَسَرَّ ٱلۡقَوۡلَ وَمَن جَهَرَ بِهِۦ وَمَنۡ هُوَ مُسۡتَخۡفِۭ بِٱلَّيۡلِ وَسَارِبُۢ بِٱلنَّهَارِ
10. ከናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ፤ በእርሱ የጮኸም፤ እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን ተገልፆ ሂያጅም የሆነ ሁሉ (እርሱ አላህ ዘንድ) እኩል ነው (አላህ ያውቀዋል)።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
لَهُۥ مُعَقِّبَٰتٞ مِّنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَمِنۡ خَلۡفِهِۦ يَحۡفَظُونَهُۥ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُواْ مَا بِأَنفُسِهِمۡۗ وَإِذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِقَوۡمٖ سُوٓءٗا فَلَا مَرَدَّ لَهُۥۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَالٍ
11. ለእርሱ ለሰው በስተፊቱም ከኋላዉም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላዕክት አሉት:: አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም:: አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለዉም:: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸዉም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
هُوَ ٱلَّذِي يُرِيكُمُ ٱلۡبَرۡقَ خَوۡفٗا وَطَمَعٗا وَيُنشِئُ ٱلسَّحَابَ ٱلثِّقَالَ
12. እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَيُسَبِّحُ ٱلرَّعۡدُ بِحَمۡدِهِۦ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ مِنۡ خِيفَتِهِۦ وَيُرۡسِلُ ٱلصَّوَٰعِقَ فَيُصِيبُ بِهَا مَن يَشَآءُ وَهُمۡ يُجَٰدِلُونَ فِي ٱللَّهِ وَهُوَ شَدِيدُ ٱلۡمِحَالِ
13. ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል:: መላዕክትም እርሱን ከመፍራት ያጠሩታል፤ መብረቆችም ይልካል። እነርሱም (ከሓዲያን) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል:: እርሱም ሀይለ ብርቱ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅರ್‍ರಅ್ ದ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ