Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ


ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್ -ಇಸ್ರಾಅ್   ಶ್ಲೋಕ:
وَمَا مَنَعَنَآ أَن نُّرۡسِلَ بِٱلۡأٓيَٰتِ إِلَّآ أَن كَذَّبَ بِهَا ٱلۡأَوَّلُونَۚ وَءَاتَيۡنَا ثَمُودَ ٱلنَّاقَةَ مُبۡصِرَةٗ فَظَلَمُواْ بِهَاۚ وَمَا نُرۡسِلُ بِٱلۡأٓيَٰتِ إِلَّا تَخۡوِيفٗا
59. ተዓምራትን ከመላክ የቀድሞዎቹ ሰዎች በእርሷ ማስተባበልና መጥፋት እንጂ ሌላ አልከለከለንም። ለሠሙድም ግመልን ግልጽ ተዓምር ሆና ሰጠናቸው:: በእርሷም በደሉ፤ ተዓምራትንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَإِذۡ قُلۡنَا لَكَ إِنَّ رَبَّكَ أَحَاطَ بِٱلنَّاسِۚ وَمَا جَعَلۡنَا ٱلرُّءۡيَا ٱلَّتِيٓ أَرَيۡنَٰكَ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلنَّاسِ وَٱلشَّجَرَةَ ٱلۡمَلۡعُونَةَ فِي ٱلۡقُرۡءَانِۚ وَنُخَوِّفُهُمۡ فَمَا يَزِيدُهُمۡ إِلَّا طُغۡيَٰنٗا كَبِيرٗا
60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተም ጌታህ በእውቀቱ ሰዎችን ያካበበ መሆኑን በነገርንህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በሌሊቱ ጉዞ በዓይንህ ያሳየንህም ትርኢት ለሰዎች ፈተና እንጂ አላደረግነዉም:: በቁርኣንም የተረገመችውን ዛፍ እንደዚሁ ፈተና እንጂ አላደረግንም፤ እናስፈራራቸዋለንም፤ ትልቅንም ጥመት እንጂ አይጨምርላቸዉም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ قَالَ ءَأَسۡجُدُ لِمَنۡ خَلَقۡتَ طِينٗا
61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክትም «ለአደም ስገዱ» ባልናቸው ጊዜ የነበረውን ሁኔታ አስታውስ:: ወዲያዉም ሰገዱ ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን?» አለ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
قَالَ أَرَءَيۡتَكَ هَٰذَا ٱلَّذِي كَرَّمۡتَ عَلَيَّ لَئِنۡ أَخَّرۡتَنِ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَأَحۡتَنِكَنَّ ذُرِّيَّتَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٗا
62. «እስቲ ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን? እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ።» አለ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
قَالَ ٱذۡهَبۡ فَمَن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ فَإِنَّ جَهَنَّمَ جَزَآؤُكُمۡ جَزَآءٗ مَّوۡفُورٗا
63. አላህም አለው: «ሂድ ከእነርሱም የተከተለህ ገሀነም የተሟላች ቅጣት ስትሆን ፍዳችሁ ናት።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَٱسۡتَفۡزِزۡ مَنِ ٱسۡتَطَعۡتَ مِنۡهُم بِصَوۡتِكَ وَأَجۡلِبۡ عَلَيۡهِم بِخَيۡلِكَ وَرَجِلِكَ وَشَارِكۡهُمۡ فِي ٱلۡأَمۡوَٰلِ وَٱلۡأَوۡلَٰدِ وَعِدۡهُمۡۚ وَمَا يَعِدُهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ إِلَّا غُرُورًا
64. «ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ ገፋፋ:: በእነርሱም ላይ በፈረሰኞችህ በእግረኞችህም ሆነህ ለልብ (አውጅ)። በገንዘቦቻቸዉም በልጆቻቸዉም ተጋራቸው:: የተስፋ ቃልም ግባላቸው።» ሰይጣንም ማታለልን እንጂ ተስፋ ቃልን አይገባላቸዉም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
إِنَّ عِبَادِي لَيۡسَ لَكَ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٞۚ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ وَكِيلٗا
65. ንጹህ ባሮቼ ግን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም:: ዋስም በጌታህ በቃ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
رَّبُّكُمُ ٱلَّذِي يُزۡجِي لَكُمُ ٱلۡفُلۡكَ فِي ٱلۡبَحۡرِ لِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ كَانَ بِكُمۡ رَحِيمٗا
66. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ ያ ከችሮታው ትፈልጉ ዘንድ መርከቦችን በባህር ላይ ለእናንተ የሚነዳላችሁ ነው:: እነሆ እርሱ ለእናንተ አዛኝ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್ -ಇಸ್ರಾಅ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ