ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಝೈನ್ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ


ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಸೂರ ಅರ್‍ರಹ್ಮಾನ್   ಶ್ಲೋಕ:

ሱረቱ አር ረሕማን

ٱلرَّحۡمَٰنُ
1. አር-ረህማን
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
عَلَّمَ ٱلۡقُرۡءَانَ
2. ቁርኣንን አስተማረ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ
3. ሰውን ፈጠረ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
عَلَّمَهُ ٱلۡبَيَانَ
4. መግለፅንም አስተማረው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ بِحُسۡبَانٖ
5. ጸሐይና ጨረቃ በተወሰነ (በየሂሳባቸው) ልክ ይሄዳሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَٱلنَّجۡمُ وَٱلشَّجَرُ يَسۡجُدَانِ
6. የሰማይ ከዋክብትና የምድር ዛፎችም ለእርሱ ይሰግዳሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلۡمِيزَانَ
7. ሰማይንም ከፍ አደረጋት:: የትክክለኛነትን ሚዛንንም አስቀመጠ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
أَلَّا تَطۡغَوۡاْ فِي ٱلۡمِيزَانِ
8. በሚዛን ስትመዝኑም እንዳትበድሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَأَقِيمُواْ ٱلۡوَزۡنَ بِٱلۡقِسۡطِ وَلَا تُخۡسِرُواْ ٱلۡمِيزَانَ
9. መመዘንንም በትክክል መዝኑ:: ስትመዝኑም አታጉድሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَٱلۡأَرۡضَ وَضَعَهَا لِلۡأَنَامِ
10. ምድርንም ለፍጡር አደላደላት::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهَا فَٰكِهَةٞ وَٱلنَّخۡلُ ذَاتُ ٱلۡأَكۡمَامِ
11. በውስጧ እሸትም ባለ ሽፍን የሆኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትሆን፤
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَٱلۡحَبُّ ذُو ٱلۡعَصۡفِ وَٱلرَّيۡحَانُ
12. ባለቅርፊት ቅንጣትና ባለ መልካም መዓዛ ቅጠሎችም ያሉባት ስትሆን፤
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
13. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች መካከል በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن صَلۡصَٰلٖ كَٱلۡفَخَّارِ
14. ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَخَلَقَ ٱلۡجَآنَّ مِن مَّارِجٖ مِّن نَّارٖ
15. ጂንንም ከጭስ አልባ የእሳት ነበልባል ፈጠረው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
16. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ وَرَبُّ ٱلۡمَغۡرِبَيۡنِ
17. የሁለቱ ምስራቆችና የሁለቱ ምዕራቦች ጌታ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
18. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
مَرَجَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ يَلۡتَقِيَانِ
19. ሁለቱም ባህሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
بَيۡنَهُمَا بَرۡزَخٞ لَّا يَبۡغِيَانِ
20. እንዳይዋሀዱ በመካከላቸው የማይታይ መጋረጃ አለ:: አንዱ በሌላው ላይ ወሰን አያልፉም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
21. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَخۡرُجُ مِنۡهُمَا ٱللُّؤۡلُؤُ وَٱلۡمَرۡجَانُ
22. ሉልና መርጃን የተባሉት ማዕድናት ከሁለቱ (ባህሮች) ይወጣሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
23. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَلَهُ ٱلۡجَوَارِ ٱلۡمُنشَـَٔاتُ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ
24. እንደ ጋራዎች ሆነው በባህር ውስጥ የተሰሩት ተንሻላዮችም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
25. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
كُلُّ مَنۡ عَلَيۡهَا فَانٖ
26. በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَيَبۡقَىٰ وَجۡهُ رَبِّكَ ذُو ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ
27. የልቅና እና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊት ብቻ ይቀራል (አይጠፋም)::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
28. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَسۡـَٔلُهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ كُلَّ يَوۡمٍ هُوَ فِي شَأۡنٖ
29.በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል። በየቀኑ ሁሉ እርሱ በስራ ላይ ነው።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
30. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
سَنَفۡرُغُ لَكُمۡ أَيُّهَ ٱلثَّقَلَانِ
31. እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ መቆጣጠር በእርግጥ እንገኛለን::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
32. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ إِنِ ٱسۡتَطَعۡتُمۡ أَن تَنفُذُواْ مِنۡ أَقۡطَارِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ فَٱنفُذُواْۚ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلۡطَٰنٖ
33. የአጋንንትና የሰው ስብስቦች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ከቻላችሁ ውጡ:: በአላህ ስልጣን እንጂ አትወጡም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
34. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يُرۡسَلُ عَلَيۡكُمَا شُوَاظٞ مِّن نَّارٖ وَنُحَاسٞ فَلَا تَنتَصِرَانِ
35. በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበላባልና ጭስን ይላክባችኋል:: ሁለታችሁም ድል አታደርጉም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
36. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ !) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَإِذَا ٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ وَرۡدَةٗ كَٱلدِّهَانِ
37. ሰማይ በተሰነጠቀችና እንደጽጌረዳ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ (ጭንቁን ምን አበረታው)::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
38. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يُسۡـَٔلُ عَن ذَنۢبِهِۦٓ إِنسٞ وَلَا جَآنّٞ
39. በዚያ ቀን ሰዉም ጂንም ከሐጢአት አይጠየቅም::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
40. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يُعۡرَفُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ بِسِيمَٰهُمۡ فَيُؤۡخَذُ بِٱلنَّوَٰصِي وَٱلۡأَقۡدَامِ
41. ከሓዲያን በምልክታቸው ይታወቃሉ:: ከዚያ አናቶቻቸውንና እግሮቻቸውን ይያዛሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
42. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ
43. "ይህች ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት" (ይባላሉ)::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَطُوفُونَ بَيۡنَهَا وَبَيۡنَ حَمِيمٍ ءَانٖ
44. በእርሷና በጣም ሞቃት በሆነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
45. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَلِمَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ جَنَّتَانِ
46. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታዉም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁሉ ሁለት ገነቶች አሉት፡
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
47. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
ذَوَاتَآ أَفۡنَانٖ
48. የቀንዘሎች ባለቤቶች የሆኑ ገነቶች፤
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
49. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهِمَا عَيۡنَانِ تَجۡرِيَانِ
50. በሁለቱ ውስጥ የሚፈሱ ሁለት ምንጮች አሉ፤
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
51. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهِمَا مِن كُلِّ فَٰكِهَةٖ زَوۡجَانِ
52. በሁለቱ ውስጥ ከየፍራፍሬው ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አሉ፤
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
53. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ فُرُشِۭ بَطَآئِنُهَا مِنۡ إِسۡتَبۡرَقٖۚ وَجَنَى ٱلۡجَنَّتَيۡنِ دَانٖ
54. የውስጥ ጉዝጉዛቸው ከወፍራም ሀር በሆኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቸ ሲሆን ይንፈላሰሳሉ፤ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ ለለቃሚ ቅርብ ነው።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
55. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهِنَّ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٞ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنّٞ
56. በውስጣቸው ከባሎቻቸው በፊት ሰዉም ጂንም ያልዳሰሳቸው (ያልገሰሳቸው) ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ ብቻ) አሳጣሪዎች ሴቶች አሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
57. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
كَأَنَّهُنَّ ٱلۡيَاقُوتُ وَٱلۡمَرۡجَانُ
58. ልክ የያቁትንና የመርጃንን ማዕድናት ይመስላሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
59. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
هَلۡ جَزَآءُ ٱلۡإِحۡسَٰنِ إِلَّا ٱلۡإِحۡسَٰنُ
60. የበጎ ስራ ዋጋ በጎ እንጂ ሌላ ነውን?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
61. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَمِن دُونِهِمَا جَنَّتَانِ
62. ከሁለት ገነቶች ሌላም ሁለት ገነቶች አሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
63. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
مُدۡهَآمَّتَانِ
64. ከልምላሜዎቻቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
65. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهِمَا عَيۡنَانِ نَضَّاخَتَانِ
66. በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
67. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهِمَا فَٰكِهَةٞ وَنَخۡلٞ وَرُمَّانٞ
68. በውስጣቸው ፍራፍሬ ዘንባባና ሩማን አለ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
69. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فِيهِنَّ خَيۡرَٰتٌ حِسَانٞ
70. በውስጣቸው ጸባየ መልካሞችና መልከ ውብ ሴቶች አሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
71. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
حُورٞ مَّقۡصُورَٰتٞ فِي ٱلۡخِيَامِ
72. በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቸቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆኑ ናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
73. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٞ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنّٞ
74. ከእነርሱ በፊት ሰዉም ሆነ ጃን አልዳሰሳቸዉም (አልገሰሳቸዉም) ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
75. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ رَفۡرَفٍ خُضۡرٖ وَعَبۡقَرِيٍّ حِسَانٖ
76. በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲሆኑ ይቀመጣሉ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
77. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
تَبَٰرَكَ ٱسۡمُ رَبِّكَ ذِي ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ
78. የግርማ የመከበር ባለቤት የሆነው ጌታህ ስም ላቀ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಸೂರ ಅರ್‍ರಹ್ಮಾನ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಝೈನ್ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ

ಮುಚ್ಚಿ