Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್- ಅನ್ ಆಮ್   ಶ್ಲೋಕ:
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَمۡ يَلۡبِسُوٓاْ إِيمَٰنَهُم بِظُلۡمٍ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلۡأَمۡنُ وَهُم مُّهۡتَدُونَ
82. እነዚያ በአላህ ያመኑና እምነታቸውን በእሱ በማጋራት ያልቀላቀሉ ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ የተሟላ ደህንነት አለላቸው:: ወደ ቀናው መንገድ የተመሩም እነርሱው ናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَتِلۡكَ حُجَّتُنَآ ءَاتَيۡنَٰهَآ إِبۡرَٰهِيمَ عَلَىٰ قَوۡمِهِۦۚ نَرۡفَعُ دَرَجَٰتٖ مَّن نَّشَآءُۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
83. እነዚህ ማስረጃዎቻችን ናቸው:: ለኢብራሂም በህዝቦቹ ላይ አስረጅ እንዲሆኑ ሰጠነው:: የምንፈልገውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَۚ كُلًّا هَدَيۡنَاۚ وَنُوحًا هَدَيۡنَا مِن قَبۡلُۖ وَمِن ذُرِّيَّتِهِۦ دَاوُۥدَ وَسُلَيۡمَٰنَ وَأَيُّوبَ وَيُوسُفَ وَمُوسَىٰ وَهَٰرُونَۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
84. ለእርሱም ልጁን ነብዩ ኢስሀቅንና የልጅ ልጁን ነብዩ የዕቆብን ሰጠነው:: ሁሉንም ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: ኑህንም ከእነርሱ በፊት ወደ ቀናው መንገድ መራነው:: ከዘሮቹም ነብዩ ዳውድንም፤ ነብዩ ሱለይማንንም፤ ነብዩ አዩብንም፤ ነብዩ ዮሱፍንም፤ ነብዩ ሙሳንና፤ ነብዩ ሀሩንንም መራን:: በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ልክ እንደዚሁ እንመነዳለን::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَزَكَرِيَّا وَيَحۡيَىٰ وَعِيسَىٰ وَإِلۡيَاسَۖ كُلّٞ مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
85. ዘከርያን፤ ያህያን፤ ዒሳን፤ ኢልያስንም ወደ ቀናው መንገድ መራን:: ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَإِسۡمَٰعِيلَ وَٱلۡيَسَعَ وَيُونُسَ وَلُوطٗاۚ وَكُلّٗا فَضَّلۡنَا عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
86. ነብዩ ኢስማኢልንም፤ ነብዩ አል የሰዕንም፤ ነብዩ ዩኑስንም፤ ነብዩ ሉጥንም መራን:: ሁሉንም በዓለማት ላይ አበለጥናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَمِنۡ ءَابَآئِهِمۡ وَذُرِّيَّٰتِهِمۡ وَإِخۡوَٰنِهِمۡۖ وَٱجۡتَبَيۡنَٰهُمۡ وَهَدَيۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
87. ከአባቶቻቸዉም፣ ከዘሮቻቸዉም፣ ከወንድሞቻቸዉም ብዙዎችን መራን:: መረጥናቸዉም:: ወደ ቀጥታኛዉም መንገድ መራናቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهۡدِي بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۚ وَلَوۡ أَشۡرَكُواْ لَحَبِطَ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
88. ይህ የአላህ መመሪያ ነው:: በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ወደ ቀናው መንገድ ይመራበታል:: በአላህ ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት መልካም ተግባር ሁሉ ከእነርሱ በታበሰባቸው ነበር::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحُكۡمَ وَٱلنُّبُوَّةَۚ فَإِن يَكۡفُرۡ بِهَا هَٰٓؤُلَآءِ فَقَدۡ وَكَّلۡنَا بِهَا قَوۡمٗا لَّيۡسُواْ بِهَا بِكَٰفِرِينَ
89. እነዚህ እነዚያ መጽሐፍትንና ጥበብን ነብይነትንም የሰጠናቸው ሰዎች ናቸው:: እነዚህ የመካ ከሓዲያን በእርሷ ቢክዱም በእርሷ የማይክዱ ሕዝቦችን አዘጋጅተንላታል::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ هَدَى ٱللَّهُۖ فَبِهُدَىٰهُمُ ٱقۡتَدِهۡۗ قُل لَّآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًاۖ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡعَٰلَمِينَ
90. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ነብያት እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው:: ስለሆነም ፈለጋቸውን ተከተል:: «በእርሱ (በቁርኣን) ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: እርሱ ለዓለማት ግሳጼ ሊሆን የወረደ እንጂ ሌላ አይደለም።» በላቸው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್- ಅನ್ ಆಮ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ