Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್- ಅಅ್ ರಾಫ್   ಶ್ಲೋಕ:
وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ جَعَلَكُمۡ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعۡدِ عَادٖ وَبَوَّأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ تَتَّخِذُونَ مِن سُهُولِهَا قُصُورٗا وَتَنۡحِتُونَ ٱلۡجِبَالَ بُيُوتٗاۖ فَٱذۡكُرُوٓاْ ءَالَآءَ ٱللَّهِ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ
74. ከዓድ ህዝቦችም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ከሜዳዎቿ ሸክላ ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ:: ከተራራዎቿም ቤቶችን ትጠርባላችሁ:: ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لِلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ لِمَنۡ ءَامَنَ مِنۡهُمۡ أَتَعۡلَمُونَ أَنَّ صَٰلِحٗا مُّرۡسَلٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قَالُوٓاْ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلَ بِهِۦ مُؤۡمِنُونَ
75. ከወገኖቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት በተለይም ከእነርሱ ላመኑት ክፍሎች: «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን?» አሏቸው:: እነርሱም «አዎን እናውቃለን:: እኛ እርሱ በተላከበት ነገር ሁሉ ትክክለኛ አማኞች ነን» አሉ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا بِٱلَّذِيٓ ءَامَنتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ
76. እነዚያ የኮሩት እኛ ግን «በዚያ ባመናችሁበት ነገር ከሓዲያን ነን።» አሉ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَعَقَرُواْ ٱلنَّاقَةَ وَعَتَوۡاْ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِمۡ وَقَالُواْ يَٰصَٰلِحُ ٱئۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
77. እናም ወዲያው ግመሊቱን ወጓትና ከጌታቸው ትዕዛዝ ወጡ:: «ሷሊህ ሆይ! ከመልዕክተኞቹ እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دَارِهِمۡ جَٰثِمِينَ
78. ወዲያዉም የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተደፍተው አደሩ::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰقَوۡمِ لَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُمۡ رِسَالَةَ رَبِّي وَنَصَحۡتُ لَكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُحِبُّونَ ٱلنَّٰصِحِينَ
79. ሷሊህም ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልዕክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ:: ለእናንተም መከርኳችሁ:: ግን እናንተ መካሪዎችን አትወዱም።» አለ።
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَلُوطًا إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَتَأۡتُونَ ٱلۡفَٰحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنۡ أَحَدٖ مِّنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ
80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥም ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ከዓለማት ከናንተ በፊት አንድም ህዝብ ያልፈጸመውን አስቀያሚ ሥራ ትሠራላችሁን?
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
إِنَّكُمۡ لَتَأۡتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهۡوَةٗ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٞ مُّسۡرِفُونَ
81. «እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል ትመጡባቸዋላችሁ። ይልቁንም እናንተ ወሰንን አላፊ ሕዝቦች ናችሁ።»
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್- ಅಅ್ ರಾಫ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ