Check out the new design

ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ * - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್ -ಅನ್ ಫಾಲ್   ಶ್ಲೋಕ:
وَإِن يُرِيدُوٓاْ أَن يَخۡدَعُوكَ فَإِنَّ حَسۡبَكَ ٱللَّهُۚ هُوَ ٱلَّذِيٓ أَيَّدَكَ بِنَصۡرِهِۦ وَبِٱلۡمُؤۡمِنِينَ
62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሊያታልሉህ ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው:: እርሱ ያ በእርዳታውና በምዕምናን ያበረታህ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
وَأَلَّفَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡۚ لَوۡ أَنفَقۡتَ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مَّآ أَلَّفۡتَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ أَلَّفَ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّهُۥ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
63. በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ያለውን ሁሉ ሀብት ብትለገስ ኖሮ እንኳን በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር:: ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَسۡبُكَ ٱللَّهُ وَمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
64. አንተ ነብይ ሆይ! ለሁሉ ነገር በቂህ አላህ ነው:: ለተከተሉህም ምዕምናን በቂያቸው አላህ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَى ٱلۡقِتَالِۚ إِن يَكُن مِّنكُمۡ عِشۡرُونَ صَٰبِرُونَ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ
65. አንተ ነብይ ሆይ! አማኞችን ጠላቶቻቸውን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: ከናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም መካከል መቶ ሰዎች ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት ሕዝቦች መካከል አንድ ሺሕን ያሸንፋሉ:: ምክንያቱም እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች ናቸዉና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
ٱلۡـَٰٔنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمۡ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمۡ ضَعۡفٗاۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ صَابِرَةٞ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمۡ أَلۡفٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفَيۡنِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
66. አሁን አላህ ከናንተ ላይ አቀለለላችሁ:: በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን አወቀ:: ስለዚህ ከናንተ መካካል መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም አንድ ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፍቃድ ሁለት ሺዎችን ያሸንፋሉ:: አላህ ከታጋሾቹ ጋር ነዉና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
مَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَكُونَ لَهُۥٓ أَسۡرَىٰ حَتَّىٰ يُثۡخِنَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ تُرِيدُونَ عَرَضَ ٱلدُّنۡيَا وَٱللَّهُ يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
67. ለነብይ በምድር ላይ ጠላቶቹን እስኪያደክም ድረስ ለእርሱ ምረኮኞች ሊኖሩት አይገባም:: (አማኞች ሆይ!) የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ:: አላህ መጨረሻይቱን ይሻል:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
لَّوۡلَا كِتَٰبٞ مِّنَ ٱللَّهِ سَبَقَ لَمَسَّكُمۡ فِيمَآ أَخَذۡتُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ
68. ከአላህ ያለፈ ውሳኔ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት ቤዛ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
فَكُلُواْ مِمَّا غَنِمۡتُمۡ حَلَٰلٗا طَيِّبٗاۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
69. (አማኞች ሆይ!) ያ! ከጠላት የማረካችሁትን ሀብት የተፈቀደና መልካም ሲሆን ብሉ:: አላህንም ፍሩ:: አላህም መሓሪና አዛኝ ነውና::
ಅರಬ್ಬಿ ವ್ಯಾಖ್ಯಾನಗಳು:
 
ಅರ್ಥಗಳ ಅನುವಾದ ಅಧ್ಯಾಯ: ಅಲ್ -ಅನ್ ಫಾಲ್
ಅಧ್ಯಾಯಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ
 
ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ - ಅನುವಾದಗಳ ವಿಷಯಸೂಚಿ

ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಝೈನ್ ಝಹ್ರುದ್ದೀನ್. ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿಯಿಂದ ಪ್ರಕಾಶಿತ

ಮುಚ್ಚಿ