Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ഫുർഖാൻ   ആയത്ത്:
وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةٗ لَّا يَخۡلُقُونَ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ وَلَا يَمۡلِكُونَ لِأَنفُسِهِمۡ ضَرّٗا وَلَا نَفۡعٗا وَلَا يَمۡلِكُونَ مَوۡتٗا وَلَا حَيَوٰةٗ وَلَا نُشُورٗا
3. ከሓዲያን ከእርሱ ከአላህ ሌላ ምንንም የማይፈጥሩንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩ፤ ለነፍሶቻቸዉም (ከራሳቸው ላይ) ጉዳትን መከላከልም ሆነ ለራሳቸው ጥቅምን ማምጣት (ማስከበር) የማይችሉ፤ ለሞት ማብቃትም ሆነ ህይወትን መለገስና ከሞት መቀስቀስንም የማይችሉን አማልክትን አምላክ አድርገው ያዙ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ إِفۡكٌ ٱفۡتَرَىٰهُ وَأَعَانَهُۥ عَلَيۡهِ قَوۡمٌ ءَاخَرُونَۖ فَقَدۡ جَآءُو ظُلۡمٗا وَزُورٗا
4. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን እርሱ (ሙሐመድ) በራሱ የቀጠፈውና በእርሱም ላይ ሌሎች ህዝቦች ያገዙት ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ። በእርግጥም በደልንና እብለትን ፈጸሙ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَقَالُوٓاْ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ ٱكۡتَتَبَهَا فَهِيَ تُمۡلَىٰ عَلَيۡهِ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلٗا
5. «እነዚህ የመጀመሪያ ሰዎች ተረቶች (አፈታሪክ) ናቸው። አስጽፎታል፤ እናም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች።» አሉ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
قُلۡ أَنزَلَهُ ٱلَّذِي يَعۡلَمُ ٱلسِّرَّ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّهُۥ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَقَالُواْ مَالِ هَٰذَا ٱلرَّسُولِ يَأۡكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمۡشِي فِي ٱلۡأَسۡوَاقِ لَوۡلَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِ مَلَكٞ فَيَكُونَ مَعَهُۥ نَذِيرًا
7. አሉም: «ይህ መልዕክተኛ ምን አይነት መልዕክተኛ ነው? ምግብ የሚመገብ ወደ ገበያ የሚመላለስ፤ ከእርሱ ጋር አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ወደ እርሱ መልአክ (በገሃድ) አይወረድም ኖሯልን?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
أَوۡ يُلۡقَىٰٓ إِلَيۡهِ كَنزٌ أَوۡ تَكُونُ لَهُۥ جَنَّةٞ يَأۡكُلُ مِنۡهَاۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلٗا مَّسۡحُورًا
8. «ወይም ወደ እርሱ ድልብ አይሰጠዉምን? ወይም ከእርሷ የሚበላባት አትክልት ለእርሱ አትኖረዉምን?» አሉ። «በዳዮችም ላመኑት የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላን አትከተሉም።» አሉ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ٱنظُرۡ كَيۡفَ ضَرَبُواْ لَكَ ٱلۡأَمۡثَٰلَ فَضَلُّواْ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ سَبِيلٗا
9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነት ለመድረስ መንገድንም አይችሉም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
تَبَارَكَ ٱلَّذِيٓ إِن شَآءَ جَعَلَ لَكَ خَيۡرٗا مِّن ذَٰلِكَ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ وَيَجۡعَل لَّكَ قُصُورَۢا
10. ያ ቢሻ ከዚህ ካሉት የተሻለን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አትክልት ስፍራዎችን ላንተ የሚያደርግልህ ህንጻ ቤቶችንም የሚያደርግልህ የሆነው ጌታ ችሮታው በዛ:: (ክብሩ ላቀ)
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
بَلۡ كَذَّبُواْ بِٱلسَّاعَةِۖ وَأَعۡتَدۡنَا لِمَن كَذَّبَ بِٱلسَّاعَةِ سَعِيرًا
11. ይልቁንም እነርሱ በትንሳኤ አስተባበሉ:: በትንሳኤ ላስተባበለም ሁሉ አቃጣይ እሳት አዘጋጅተናል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ഫുർഖാൻ
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക