Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: അഹ്ഖാഫ്   ആയത്ത്:
وَإِذۡ صَرَفۡنَآ إِلَيۡكَ نَفَرٗا مِّنَ ٱلۡجِنِّ يَسۡتَمِعُونَ ٱلۡقُرۡءَانَ فَلَمَّا حَضَرُوهُ قَالُوٓاْ أَنصِتُواْۖ فَلَمَّا قُضِيَ وَلَّوۡاْ إِلَىٰ قَوۡمِهِم مُّنذِرِينَ
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን የሚያደምጡ ሁነው በላክንልህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ሲነበብ በደረሱ ጊዜ «ዝም በሉ» ተባባሉ:: ንባቡ ሲጠናቀቅም ወገኖቻቸውን ለማስጠንቀቅ ወደ ህዝቦቻቸው ተመለሱ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
قَالُواْ يَٰقَوۡمَنَآ إِنَّا سَمِعۡنَا كِتَٰبًا أُنزِلَ مِنۢ بَعۡدِ مُوسَىٰ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِ يَهۡدِيٓ إِلَى ٱلۡحَقِّ وَإِلَىٰ طَرِيقٖ مُّسۡتَقِيمٖ
30. አሉም ለወገኖቻቸው: «ወገኖቻችን ሆይ! ከሙሳ ተውራት በኋላ የተወረደንና ከእርሱ በፊት የወረዱትን መጽሐፍት አጽዳቂ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛው ጎዳና መሪም የሆነን መጽሐፍ አደመጥን::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَٰقَوۡمَنَآ أَجِيبُواْ دَاعِيَ ٱللَّهِ وَءَامِنُواْ بِهِۦ يَغۡفِرۡ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمۡ وَيُجِرۡكُم مِّنۡ عَذَابٍ أَلِيمٖ
31. «ወገኖቻችን ሆይ! ለዚህ ወደ አላህ ለሚጠራችሁ ሰው በጎ ምላሽ ስጡ:: በእርሱ እመኑም:: ይህን ካረጋችሁ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃችኋል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَمَن لَّا يُجِبۡ دَاعِيَ ٱللَّهِ فَلَيۡسَ بِمُعۡجِزٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَيۡسَ لَهُۥ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءُۚ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
32. ወደ አላህ ለሚጠራ ሰው ሁሉ በጎ ምላሽ ያልሰጠ በምድር ላይ ከአላህ ቅጣት አያመልጥም:: ከእርሱ ሌላም ረዳት አይኖረዉም:: እንዲህ አይነት ሰዎች ግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::» (አሉ)
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَلَمۡ يَعۡيَ بِخَلۡقِهِنَّ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰۚ بَلَىٰٓۚ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
33. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው እርሱም በመፍጠሩም ድካም ያልተሰማው አላህ ሙታንን ህያው ማድረግ እንደሚችል አላዩምን ? በእርግጥም ይህን ማድረግ የሚሳነው አይደለም :: እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَيَوۡمَ يُعۡرَضُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَلَى ٱلنَّارِ أَلَيۡسَ هَٰذَا بِٱلۡحَقِّۖ قَالُواْ بَلَىٰ وَرَبِّنَاۚ قَالَ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ
34. እነዚያም የካዱት ሰዎች ሁሉ ወደ እሳት እንዲቀርቡ በሚደረጉ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። «ይህ እውነት አይደለምን ?» ይባላሉ :: «አዎ እውነት መሆኑን በጌታችን በመማል እናረጋግጣለን» ይላሉ:: እርሱም «ታስተባብሉት በነበራችሁት ሰበብ ቅጣትን ቅመሱ» ይላቸዋል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
فَٱصۡبِرۡ كَمَا صَبَرَ أُوْلُواْ ٱلۡعَزۡمِ مِنَ ٱلرُّسُلِ وَلَا تَسۡتَعۡجِل لَّهُمۡۚ كَأَنَّهُمۡ يَوۡمَ يَرَوۡنَ مَا يُوعَدُونَ لَمۡ يَلۡبَثُوٓاْ إِلَّا سَاعَةٗ مِّن نَّهَارِۭۚ بَلَٰغٞۚ فَهَلۡ يُهۡلَكُ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ
35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች መካከል የጽናት ባለቤቶች እንደታገሱት ሁሉ አንተም ታገስ::(በህዝቦችህ ላይ) ቅጣቱ ይፋጠንባቸው ዘንድም አትጠይቅ:: ያን ቃል የተገባላቸውን ቅጣት በሚያዩ ጊዜ ምድር ላይ ከቀን ውስጥ የተወሰነ ወቅት ብቻ እንጂ እንዳልቆዩ ይሰማቸዋል:: ይህ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው:: ከአመጸኞች ህዝቦች ውጪ ሌሎች እንዲጠፉ ይደረጋልን?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: അഹ്ഖാഫ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക