Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: അഹ്ഖാഫ്   ആയത്ത്:
وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُواْ لَهُمۡ أَعۡدَآءٗ وَكَانُواْ بِعِبَادَتِهِمۡ كَٰفِرِينَ
6. ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ ጣኦቶቹ ለእነርሱ ጠላቶች ይሆናሉ:: እነርሱን መገዛታቸውንም ይክዳሉ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ هَٰذَا سِحۡرٞ مُّبِينٌ
7. በእነርሱም ላይ አንቀፆቻችን ግልፆች ሆነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ክፍሎች «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ إِنِ ٱفۡتَرَيۡتُهُۥ فَلَا تَمۡلِكُونَ لِي مِنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔاۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَا تُفِيضُونَ فِيهِۚ كَفَىٰ بِهِۦ شَهِيدَۢا بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۖ وَهُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «(ሙሐመድ ራሱ) ቀጠፈው» ይላሉን? «ብቀጥፈው ኖሮ እኔን ከአላህ ቅጣት ለማዳን በምንም አትችሉም:: እርሱ ያንን የምትቀባዥሩበትን ነገር ሁሉ አዋቂ ነው:: በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪነት እሱው በቃ:: እርሱ መሀሪ እና አዛኝ ነውና» በላቸው።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
قُلۡ مَا كُنتُ بِدۡعٗا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدۡرِي مَا يُفۡعَلُ بِي وَلَا بِكُمۡۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٞ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች የተለየሁ ብጤ የሌለኝ አይደለሁም:: በእኔም በእናንተም ላይ ምን እንደሚሰራብንም አላውቅም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ ሌላን መመሪያ አልከተልም:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كَانَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ وَكَفَرۡتُم بِهِۦ وَشَهِدَ شَاهِدٞ مِّنۢ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ عَلَىٰ مِثۡلِهِۦ فَـَٔامَنَ وَٱسۡتَكۡبَرۡتُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
10. «(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስቲ ንገሩኝ ቁርኣኑ ከአላህ ዘንድ ቢሆንና በእርሱ ብትክዱ ከኢስራኢል ልጆች የሆነ መስካሪ ደግሞ በቢጤው ቢያምንና በእርሱ ላይ ቢመሰክር እናንተ (ግን) ብትኮሩ (በዳይ አትሆኑምን)? አላህ በእርግጥ በደለኛ ህዝቦችን ሁሉ አያቀናም» በላቸው።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَوۡ كَانَ خَيۡرٗا مَّا سَبَقُونَآ إِلَيۡهِۚ وَإِذۡ لَمۡ يَهۡتَدُواْ بِهِۦ فَسَيَقُولُونَ هَٰذَآ إِفۡكٞ قَدِيمٞ
11. እነዚያም የካዱት ሰዎች ስላመኑት ሰዎች «እምነቱ መልካም ነገር በሆነ ኖሮ ወደ እርሱ ባልቀደሙን ነበር» አሉ:: በእርሱም ባልተቀኑ ጊዜ «ይህ ቁርኣን ጥንታዊ ቅጥፈት ነው» ይላሉ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَمِن قَبۡلِهِۦ كِتَٰبُ مُوسَىٰٓ إِمَامٗا وَرَحۡمَةٗۚ وَهَٰذَا كِتَٰبٞ مُّصَدِّقٞ لِّسَانًا عَرَبِيّٗا لِّيُنذِرَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُحۡسِنِينَ
12. ከፊቱም የሙሳን መጽሐፍ ለሰዎች መሪና የአላህ ጸጋ ሲሆን እንዳወረድን አላየህምን? ይህ ቁርኣን እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ የወረደ ሲሆን የፊቶቹንም መጽሐፍት አረጋጋጭ እና ለበጎ አድራጊዎችም ሁሉ የብስራት መጽሐፍ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُواْ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسۡتَقَٰمُواْ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
13. «እነዚያ ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም በዚሁ ቃላቸው ላይ ቀጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ምንም (ይደርስብናል ብለው) ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም (ነገር ያመልጠናል ብለው) አያዝኑምም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِ خَٰلِدِينَ فِيهَا جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
14. እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው:: በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በዚያ በዱንያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ያገኙት ምንዳ ነው።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: അഹ്ഖാഫ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക