Check out the new design

पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । * - अनुवादहरूको सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थको अनुवाद सूरः: हूद   श्लोक:
وَيَٰقَوۡمِ لَا يَجۡرِمَنَّكُمۡ شِقَاقِيٓ أَن يُصِيبَكُم مِّثۡلُ مَآ أَصَابَ قَوۡمَ نُوحٍ أَوۡ قَوۡمَ هُودٍ أَوۡ قَوۡمَ صَٰلِحٖۚ وَمَا قَوۡمُ لُوطٖ مِّنكُم بِبَعِيدٖ
89. «ወገኖቼ ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑህን ህዝቦች ወይም የሁድን ህዝቦች ወይም የሷሊህን ህዝቦች ያገኛቸው ቅጣት ብጤ አይነት እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ:: የሉጥም ህዝቦች ከናንተ ሩቅ አይደሉም።
अरबी व्याख्याहरू:
وَٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٞ وَدُودٞ
90. «ጌታችሁንም ምህረት ለምኑት ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ። ጌታዬ አዛኝና ወዳድ ነውና።» አለ።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ يَٰشُعَيۡبُ مَا نَفۡقَهُ كَثِيرٗا مِّمَّا تَقُولُ وَإِنَّا لَنَرَىٰكَ فِينَا ضَعِيفٗاۖ وَلَوۡلَا رَهۡطُكَ لَرَجَمۡنَٰكَۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡنَا بِعَزِيزٖ
91. «ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀዉም (አይገባንም):: እኛም አንተን በኛ ውስጥ ደከማ ሆነህ እናይሃለን:: ጎሶችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር:: አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም።» አሉት::
अरबी व्याख्याहरू:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَهۡطِيٓ أَعَزُّ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَٱتَّخَذۡتُمُوهُ وَرَآءَكُمۡ ظِهۡرِيًّاۖ إِنَّ رَبِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ
92. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ? ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን? አላህን ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አደረጋችሁት:: ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው።
अरबी व्याख्याहरू:
وَيَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَٰمِلٞۖ سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَمَنۡ هُوَ كَٰذِبٞۖ وَٱرۡتَقِبُوٓاْ إِنِّي مَعَكُمۡ رَقِيبٞ
93. «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ እኔ ሠሪ ነኝ። የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትንና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደ ሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ:: ጠብቁም እኔም ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና።» አለ።
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا شُعَيۡبٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَأَخَذَتِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلصَّيۡحَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دِيَٰرِهِمۡ جَٰثِمِينَ
94. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው። በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ::
अरबी व्याख्याहरू:
كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَآۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّمَدۡيَنَ كَمَا بَعِدَتۡ ثَمُودُ
95. በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ:: አስተዉሉ! ሠሙድ ከአላህ እዝነት እንደራቀች መድየንም ትራቅ::
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ
96. ሙሳንም በታዐምራቶቻችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው::
अरबी व्याख्याहरू:
إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱتَّبَعُوٓاْ أَمۡرَ فِرۡعَوۡنَۖ وَمَآ أَمۡرُ فِرۡعَوۡنَ بِرَشِيدٖ
ወደ ፈርዖንና ወደስዎቹ ላክነው፡፡የፈርዖንን ነገር ህዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገር ቀጥተኛ አል ነበረም፡፡
अरबी व्याख्याहरू:
 
अर्थको अनुवाद सूरः: हूद
अध्यायहरूको (सूरःहरूको) सूची رقم الصفحة
 
पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । - अनुवादहरूको सूची

अनुवाद : मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दिन । अफ्रिका एकेडेमीबाट प्रकाशित ।

बन्द गर्नुस्