Check out the new design

पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । * - अनुवादहरूको सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थको अनुवाद सूरः: यूसुफ   श्लोक:
فَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمۡ جَعَلَ ٱلسِّقَايَةَ فِي رَحۡلِ أَخِيهِ ثُمَّ أَذَّنَ مُؤَذِّنٌ أَيَّتُهَا ٱلۡعِيرُ إِنَّكُمۡ لَسَٰرِقُونَ
70. እቃቸውን ባዘጋጀላቸው ጊዜ ዋንጫይቱን በወንድሙ እቃ ውስጥ አደረገና ከዚያ «እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በእርግጥ ሌቦች ናችሁ።» ሲል ጠሪ ተጣራ።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ وَأَقۡبَلُواْ عَلَيۡهِم مَّاذَا تَفۡقِدُونَ
71. ወደ እነርሱ ዞረዉም: «ምንድን ጠፋችሁ?» አሉ።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ نَفۡقِدُ صُوَاعَ ٱلۡمَلِكِ وَلِمَن جَآءَ بِهِۦ حِمۡلُ بَعِيرٖ وَأَنَا۠ بِهِۦ زَعِيمٞ
72. «የንጉሱ መስፈሪያ ጠፍቶናል እርሱንም ላመጣ ሰው የአንድ ግመል ጭነት አለው። እኔም በእርሱ ተያዥ ነኝ።» አለ።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ تَٱللَّهِ لَقَدۡ عَلِمۡتُم مَّا جِئۡنَا لِنُفۡسِدَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا كُنَّا سَٰرِقِينَ
73. «በአላህ እንምላለን! በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ አውቃችኋል ሌቦችም አልነበርንም።» አሉ።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ فَمَا جَزَٰٓؤُهُۥٓ إِن كُنتُمۡ كَٰذِبِينَ
74. «ውሸታሞች ብትሆኑስ ቅጣቱ ምንድን ነው?» አሏቸው።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ جَزَٰٓؤُهُۥ مَن وُجِدَ فِي رَحۡلِهِۦ فَهُوَ جَزَٰٓؤُهُۥۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّٰلِمِينَ
75. «ቅጣቱ በየዕቁብ ሕግ እቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው ራሱ ባሪያ ተደርጎ መውሰድ ነው። እርሱም ቅጣቱ ነው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን።» አሉ።
अरबी व्याख्याहरू:
فَبَدَأَ بِأَوۡعِيَتِهِمۡ قَبۡلَ وِعَآءِ أَخِيهِ ثُمَّ ٱسۡتَخۡرَجَهَا مِن وِعَآءِ أَخِيهِۚ كَذَٰلِكَ كِدۡنَا لِيُوسُفَۖ مَا كَانَ لِيَأۡخُذَ أَخَاهُ فِي دِينِ ٱلۡمَلِكِ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ نَرۡفَعُ دَرَجَٰتٖ مَّن نَّشَآءُۗ وَفَوۡقَ كُلِّ ذِي عِلۡمٍ عَلِيمٞ
76. ምርመራውን ከወንድሙ እቃ በፊትም በእቃዎቻቸው ጀመረ:: ከዚያ ዋንጫይቱን ከወንድሙ እቃ ውስጥ አወጣት። ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው:: አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሱ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባዉም ነበር:: የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ከእውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም አዋቂ አለ::
अरबी व्याख्याहरू:
۞ قَالُوٓاْ إِن يَسۡرِقۡ فَقَدۡ سَرَقَ أَخٞ لَّهُۥ مِن قَبۡلُۚ فَأَسَرَّهَا يُوسُفُ فِي نَفۡسِهِۦ وَلَمۡ يُبۡدِهَا لَهُمۡۚ قَالَ أَنتُمۡ شَرّٞ مَّكَانٗاۖ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا تَصِفُونَ
77. «እርሱ ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የእርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል።» አሉ። ዩሱፍም ይህችን (አስቀያሚ ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት:: ለእነርሱም አልገለጣትም። በልቡ «እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው:: አላህ የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው።» አለ።
अरबी व्याख्याहरू:
قَالُواْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡعَزِيزُ إِنَّ لَهُۥٓ أَبٗا شَيۡخٗا كَبِيرٗا فَخُذۡ أَحَدَنَا مَكَانَهُۥٓۖ إِنَّا نَرَىٰكَ مِنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
78. «አንተ የተከበርከው ሆይ! ለእርሱ በእርግጥ ታላቅ ሽማግሌ አባት አለው:: ስለዚህ በእርሱ ስፍራ አንደኛችንን ያዝ:: እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና።» አሉት።
अरबी व्याख्याहरू:
 
अर्थको अनुवाद सूरः: यूसुफ
अध्यायहरूको (सूरःहरूको) सूची رقم الصفحة
 
पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । - अनुवादहरूको सूची

अनुवाद : मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दिन । अफ्रिका एकेडेमीबाट प्रकाशित ।

बन्द गर्नुस्