Check out the new design

पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । * - अनुवादहरूको सूची


अर्थको अनुवाद सूरः: बकरः   श्लोक:
قُلۡ إِن كَانَتۡ لَكُمُ ٱلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ عِندَ ٱللَّهِ خَالِصَةٗ مِّن دُونِ ٱلنَّاسِ فَتَمَنَّوُاْ ٱلۡمَوۡتَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለአይሁድ) «የመጨረሻይቱ አገር ገነት በአላህ ዘንድ ከሌሎች በተለየ ለእናንተ ብቻ በመሆኗ እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ።» በላቸው።
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَن يَتَمَنَّوۡهُ أَبَدَۢا بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ
95. እጆቻቸው (ባሳለፉት) በሰሩት ወንጀል ምክንያት ሞትን ምንጊዜም ፈጽሞ አይመኙትም:: አላህ በዳዩችን አዋቂ ነው፡፡
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَتَجِدَنَّهُمۡ أَحۡرَصَ ٱلنَّاسِ عَلَىٰ حَيَوٰةٖ وَمِنَ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْۚ يَوَدُّ أَحَدُهُمۡ لَوۡ يُعَمَّرُ أَلۡفَ سَنَةٖ وَمَا هُوَ بِمُزَحۡزِحِهِۦ مِنَ ٱلۡعَذَابِ أَن يُعَمَّرَۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ
96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድ ሁሉ እና ከእነዚያ ጣኦትን በአላህ ካጋሩት ይበልጥ በሕይወት ላይ የሚጓጉ ሆነው በእርግጥ ታገኛቸዋለህ:: ለአንዳቸውም አንድ ሺህ ዓመት ዕድሜ ቢሰጥ ይወዳል:: እርሱም (ዕድሜ መሰጠቱ) ከቅጣት የሚያድነው አይደለም:: አላህም የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።
अरबी व्याख्याहरू:
قُلۡ مَن كَانَ عَدُوّٗا لِّـجِبۡرِيلَ فَإِنَّهُۥ نَزَّلَهُۥ عَلَىٰ قَلۡبِكَ بِإِذۡنِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَهُدٗى وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ
97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመልዐኩ ጅብሪል ጠላት የሆነ (ግልጽ ከሃዲ ነው)። ከርሱ በፊት የወረዱ መጽሐፍትን የሚያረጋግጥ ለአማኞች መሪና ብስራት ነጋሪ ሲሆን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ ያወረደው መሆኑን ንገራቸው።
अरबी व्याख्याहरू:
مَن كَانَ عَدُوّٗا لِّلَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَرُسُلِهِۦ وَجِبۡرِيلَ وَمِيكَىٰلَ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَدُوّٞ لِّلۡكَٰفِرِينَ
98. ለአላህና ለመላዕክቱ፤ እንዲሁም ለመልዕክተኞቹ፤ ለጅብሪልና ለሚካኢልም ጠላት የሆነ ሁሉ ግልጽ ከሐዲ ነው:: አላህ ደግሞ ለከሓዲያን ሁሉ ጠላት ነው::
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَقَدۡ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۖ وَمَا يَكۡفُرُ بِهَآ إِلَّا ٱلۡفَٰسِقُونَ
99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ አንተ ግልጽ የሆኑ (አናቅጽን) መመሪያዎችን በእርግጥ አውርደናል:: በእነርሱም አመጸኞች እንጂ ሌላ አይክድም::
अरबी व्याख्याहरू:
أَوَكُلَّمَا عَٰهَدُواْ عَهۡدٗا نَّبَذَهُۥ فَرِيقٞ مِّنۡهُمۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
100. ቃልኪዳን በገቡ ቁጥር ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ቃል ኪዳኑን ይጥለዋልን? (ያፈርሰዋልን?):: ይልቁንም አብዛኞቻቸው አያምኑም፡፡
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَمَّا جَآءَهُمۡ رَسُولٞ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٞ لِّمَا مَعَهُمۡ نَبَذَ فَرِيقٞ مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَرَآءَ ظُهُورِهِمۡ كَأَنَّهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
101. ከእነርሱ ጋር ያለን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ከአላህ ዘንድ ተልኮ በመጣ ጊዜ ከእነዚያው መጽሐፍት ከተሰጣቸው ወገኖች ከፊሎቹ ምንም እንደማያውቁ ሆነው የአላህን መጽሐፍ ወደ ኋላቸው ወረወሩት (ጣሉት)።
अरबी व्याख्याहरू:
 
अर्थको अनुवाद सूरः: बकरः
अध्यायहरूको (सूरःहरूको) सूची رقم الصفحة
 
पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । - अनुवादहरूको सूची

अनुवाद : मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दिन । अफ्रिका एकेडेमीबाट प्रकाशित ।

बन्द गर्नुस्