Check out the new design

पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । * - अनुवादहरूको सूची


अर्थको अनुवाद सूरः: अहजाब   श्लोक:
مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ رِجَالٞ صَدَقُواْ مَا عَٰهَدُواْ ٱللَّهَ عَلَيۡهِۖ فَمِنۡهُم مَّن قَضَىٰ نَحۡبَهُۥ وَمِنۡهُم مَّن يَنتَظِرُۖ وَمَا بَدَّلُواْ تَبۡدِيلٗا
23. ከአማኞች መካከል በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ። ከእነርሱም ስለቱን የፈጸመ ለሃይማኖቱ የተገደለም አለ:: ከእነርሱም መካከል ገና የሚጠባበቅ አለ:: የገቡትን ቃል መለወጥንም አለወጡም::
अरबी व्याख्याहरू:
لِّيَجۡزِيَ ٱللَّهُ ٱلصَّٰدِقِينَ بِصِدۡقِهِمۡ وَيُعَذِّبَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ إِن شَآءَ أَوۡ يَتُوبَ عَلَيۡهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
24. አላህ እውነተኞችን በእውነተኛነታቸው ሊመነዳ፤ አስመሳዮችንም ቢፈልግ ሊቀጣ ወይም ቢመለሱ በእነርሱ ላይ ጸጸታቸቸውን ሊቀበል ይህን አደረገ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::
अरबी व्याख्याहरू:
وَرَدَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِغَيۡظِهِمۡ لَمۡ يَنَالُواْ خَيۡرٗاۚ وَكَفَى ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلۡقِتَالَۚ وَكَانَ ٱللَّهُ قَوِيًّا عَزِيزٗا
25. እነዚያንም በአላህ የካዱትን በቁጭታቸው የተሞሉ መልካምን ነገር ያላገኙ ሆነው አላህ መለሳቸው:: አማኞቹንም አላህ መጋደልን በቃቸው:: አላህም ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::
अरबी व्याख्याहरू:
وَأَنزَلَ ٱلَّذِينَ ظَٰهَرُوهُم مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مِن صَيَاصِيهِمۡ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعۡبَ فَرِيقٗا تَقۡتُلُونَ وَتَأۡسِرُونَ فَرِيقٗا
26. እነዚያንም ከመጽሐፉ ባለቤቶች አህዛቦችን የረዷቸውን (ቁረይዟን) ከምሽጎቻቸው አወረዳቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ መባባትን ጣለባቸው። ከፊሉን ትገድላላችሁ፤ ከፊሉንም ትማርካላችሁ::
अरबी व्याख्याहरू:
وَأَوۡرَثَكُمۡ أَرۡضَهُمۡ وَدِيَٰرَهُمۡ وَأَمۡوَٰلَهُمۡ وَأَرۡضٗا لَّمۡ تَطَـُٔوهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٗا
27. ምድራቸውንም ቤቶቻቸውንም ገንዘቦቻቸውንም ገና ያልረገጣችኋትንም ምድር አወረሳችሁ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
अरबी व्याख्याहरू:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ قُل لِّأَزۡوَٰجِكَ إِن كُنتُنَّ تُرِدۡنَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا وَزِينَتَهَا فَتَعَالَيۡنَ أُمَتِّعۡكُنَّ وَأُسَرِّحۡكُنَّ سَرَاحٗا جَمِيلٗا
28. አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው: «ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ:: አጣቅማችኋለሁና መልካምንም መፍታት እፈታችኋለሁና::
अरबी व्याख्याहरू:
وَإِن كُنتُنَّ تُرِدۡنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَ فَإِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلۡمُحۡسِنَٰتِ مِنكُنَّ أَجۡرًا عَظِيمٗا
29. «አላህንና መልዕክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ከሆናችሁ እነሆ አላህ ከናንተ ለመልካም ሰሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል።»
अरबी व्याख्याहरू:
يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِيِّ مَن يَأۡتِ مِنكُنَّ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖ يُضَٰعَفۡ لَهَا ٱلۡعَذَابُ ضِعۡفَيۡنِۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا
30. እናንተ የነብዩ ሚስቶች ሆይ! ከናንተ ውስጥ ግልጽ የሆነን መጥፎ ስራ የምትሰራ ሴት ቅጣቷ ሁለት እጥፍ ሆኖ ይነባበርባታል:: ይህም በአላህ ዘንድ ገር ነው::
अरबी व्याख्याहरू:
 
अर्थको अनुवाद सूरः: अहजाब
अध्यायहरूको (सूरःहरूको) सूची رقم الصفحة
 
पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । - अनुवादहरूको सूची

अनुवाद : मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दिन । अफ्रिका एकेडेमीबाट प्रकाशित ।

बन्द गर्नुस्