Check out the new design

पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । * - अनुवादहरूको सूची


अर्थको अनुवाद सूरः: ज्जुखरूफ   श्लोक:
وَكَذَٰلِكَ مَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتۡرَفُوهَآ إِنَّا وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٖ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّقۡتَدُونَ
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው:: ከበፊትም በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስፈራሪን አላክንም ቅምጥሎቿ «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘን:: እኛም ፈለጎቻቸውን ተከታዩች ነን» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::
अरबी व्याख्याहरू:
۞ قَٰلَ أَوَلَوۡ جِئۡتُكُم بِأَهۡدَىٰ مِمَّا وَجَدتُّمۡ عَلَيۡهِ ءَابَآءَكُمۡۖ قَالُوٓاْ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ
24. አስፈራሪው «አባቶቻችሁን በእርሱ ላይ ካገኛችሁበት ይበልጥ ቀጥተኛው ሃይማኖት ባመጣላችሁም?» ቢላቸው «እኛ በተላካችሁበት ነገር (ሀይማኖት) ከሓዲያን ነን» አሉ።
अरबी व्याख्याहरू:
فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
25. ከእነርሱም ተበቀልን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተባባዮች መጨረሻ እንዴት እንደነበር ተመልከት::
अरबी व्याख्याहरू:
وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦٓ إِنَّنِي بَرَآءٞ مِّمَّا تَعۡبُدُونَ
26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምም ለአባቱና ለህዝቦቹ «እኔ ከምትገዙት ጣኦታት ሁሉ ንጹህ ነኝ::
अरबी व्याख्याहरू:
إِلَّا ٱلَّذِي فَطَرَنِي فَإِنَّهُۥ سَيَهۡدِينِ
27. «ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር ማንንም አልገዛም:: አላህንማ በእርግጥ ይመራኛልና ብቻውን አመልከዋለሁ» ባለ ጊዜ የነበረውን አስታውስ::
अरबी व्याख्याहरू:
وَجَعَلَهَا كَلِمَةَۢ بَاقِيَةٗ فِي عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
28. በዝርዮቹም ውስጥ ወደ አላህ ይመለሱ ዘንድ (በአንድ አምላክ) ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት::
अरबी व्याख्याहरू:
بَلۡ مَتَّعۡتُ هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ وَرَسُولٞ مُّبِينٞ
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁን እነዚህን ቁረይሾችንም አባቶቻቸውንም ቁርኣንንና ገላጭ መልዕክተኛ እስካመጣላቸው ድረስ አጣቀምኳቸው::
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ قَالُواْ هَٰذَا سِحۡرٞ وَإِنَّا بِهِۦ كَٰفِرُونَ
30. እውነት በመጣላቸው ጊዜም «ይህ ያመጣሀው ድግምት ነው። እኛም በእርሱ ከሓዲያን ነን።» አሉ::
अरबी व्याख्याहरू:
وَقَالُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنَ ٱلۡقَرۡيَتَيۡنِ عَظِيمٍ
31. ይህም «ቁርኣን በሁለቱ ከተሞች በአንዱ በሚኖር ታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?» አሉ።
अरबी व्याख्याहरू:
أَهُمۡ يَقۡسِمُونَ رَحۡمَتَ رَبِّكَۚ نَحۡنُ قَسَمۡنَا بَيۡنَهُم مَّعِيشَتَهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَرَفَعۡنَا بَعۡضَهُمۡ فَوۡقَ بَعۡضٖ دَرَجَٰتٖ لِّيَتَّخِذَ بَعۡضُهُم بَعۡضٗا سُخۡرِيّٗاۗ وَرَحۡمَتُ رَبِّكَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ
32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ የጌታህን ስጦታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት እንኳን ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል:: ከፊላቸዉም ከፊሉን አገልጋይ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ (በሀብት) አበለጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው::
अरबी व्याख्याहरू:
وَلَوۡلَآ أَن يَكُونَ ٱلنَّاسُ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ لَّجَعَلۡنَا لِمَن يَكۡفُرُ بِٱلرَّحۡمَٰنِ لِبُيُوتِهِمۡ سُقُفٗا مِّن فِضَّةٖ وَمَعَارِجَ عَلَيۡهَا يَظۡهَرُونَ
33. ሰዎችም (በክህደት) ላይ አንድ ህዝብ የሚሆኑ ባልነበሩ ኖሮ በአል-ረህማን ለሚክዱ ሰዎች ሁሉ (በዚህች ዓለም) ለቤቶቻቸው የብር ጣራዎች፤ የሚወጣጡባቸውም የብር መሰላሎች፤ ባደረግንላቸው ነበር።
अरबी व्याख्याहरू:
 
अर्थको अनुवाद सूरः: ज्जुखरूफ
अध्यायहरूको (सूरःहरूको) सूची رقم الصفحة
 
पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी । - अनुवादहरूको सूची

अनुवाद : मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दिन । अफ्रिका एकेडेमीबाट प्रकाशित ।

बन्द गर्नुस्