Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: بقره   آیت:
وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِـۧمُ رَبِّ أَرِنِي كَيۡفَ تُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰۖ قَالَ أَوَلَمۡ تُؤۡمِنۖ قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِن لِّيَطۡمَئِنَّ قَلۡبِيۖ قَالَ فَخُذۡ أَرۡبَعَةٗ مِّنَ ٱلطَّيۡرِ فَصُرۡهُنَّ إِلَيۡكَ ثُمَّ ٱجۡعَلۡ عَلَىٰ كُلِّ جَبَلٖ مِّنۡهُنَّ جُزۡءٗا ثُمَّ ٱدۡعُهُنَّ يَأۡتِينَكَ سَعۡيٗاۚ وَٱعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
260. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ እስቲ አሳየኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውስ:: አላህ፡- «አላመንክምን?» አለው:: ኢብራሂምም «በፍጹም (አይደለም) አምኛለሁ:: ግን ልቤ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋጋ ነው።» አለው:: አላህም፡- «አራት ወፎችን ያዝና ወደ አንተ ሰብስባቸው:: ከዚያ ቆራርጣቸው:: ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከእነርሱ ቁራጭ ቁራጭ አካላቸውን አስቀምጥ:: ከዚያም ጥራቸው በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ:: አላህ አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቅ።» አለው::
عربي تفسیرونه:
مَّثَلُ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنۢبَتَتۡ سَبۡعَ سَنَابِلَ فِي كُلِّ سُنۢبُلَةٖ مِّاْئَةُ حَبَّةٖۗ وَٱللَّهُ يُضَٰعِفُ لِمَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
261. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች ልግስና ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንዳበቀለች አንዲት ፍሬ ምሳሌ ነው:: አላህ ለሚሻው ሁሉ አባዝቶ ይለግሳል:: አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነውና::
عربي تفسیرونه:
ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ لَا يُتۡبِعُونَ مَآ أَنفَقُواْ مَنّٗا وَلَآ أَذٗى لَّهُمۡ أَجۡرُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ وَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
262. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ከዚያ በሰጡት ነገር መመፃደቅና ማስከፋት የማያስከትሉ ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አለላቸው:: በእነርሱም ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።
عربي تفسیرونه:
۞ قَوۡلٞ مَّعۡرُوفٞ وَمَغۡفِرَةٌ خَيۡرٞ مِّن صَدَقَةٖ يَتۡبَعُهَآ أَذٗىۗ وَٱللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٞ
263. መልካም ንግግርና ይቅር ባይነት ብቻ ማስከፋት ከሚከተለው ምጽዋት በላጭ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂና ታጋሽ ነውና::
عربي تفسیرونه:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُبۡطِلُواْ صَدَقَٰتِكُم بِٱلۡمَنِّ وَٱلۡأَذَىٰ كَٱلَّذِي يُنفِقُ مَالَهُۥ رِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَلَا يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۖ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ صَفۡوَانٍ عَلَيۡهِ تُرَابٞ فَأَصَابَهُۥ وَابِلٞ فَتَرَكَهُۥ صَلۡدٗاۖ لَّا يَقۡدِرُونَ عَلَىٰ شَيۡءٖ مِّمَّا كَسَبُواْۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
264. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ገንዘብን ለሰዎች ለማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻው ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመፃደቅና ተረጂውን በማስከፋት አታበላሹ:: የዚህ አይነቱም ድርጊት ምሳሌው በላዩ ላይ አፈር እንዳረፈበት ለስላሳ ድንጋይ ሲሆን እሱም ሀይለኛ ዝናብ አግኝቶት እንደተራቆተ ብጤ ነው:: እነኝህ አይነት ሰዎች ከሰሩት ነገር በምኑም ሊጠቀሙ አይችሉም:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን በፍጹም ወደ ቀናው መንገድ አይመራምና::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: بقره
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول