Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: بقره   آیت:
۞ وَإِن كُنتُمۡ عَلَىٰ سَفَرٖ وَلَمۡ تَجِدُواْ كَاتِبٗا فَرِهَٰنٞ مَّقۡبُوضَةٞۖ فَإِنۡ أَمِنَ بَعۡضُكُم بَعۡضٗا فَلۡيُؤَدِّ ٱلَّذِي ٱؤۡتُمِنَ أَمَٰنَتَهُۥ وَلۡيَتَّقِ ٱللَّهَ رَبَّهُۥۗ وَلَا تَكۡتُمُواْ ٱلشَّهَٰدَةَۚ وَمَن يَكۡتُمۡهَا فَإِنَّهُۥٓ ءَاثِمٞ قَلۡبُهُۥۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ عَلِيمٞ
283. በጉዞ ላይ ብትሆኑና ጸሐፊ ባታገኙ በእጅ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ:: ከፊላችሁ ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን በትክክል ያድርስ:: አላህንም ጌታውን ይፍራ:: ምስክርነትንም አትደብቁ። ምስክርነትን የሚደብቃት ልበ ኃጢአተኛ ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
عربي تفسیرونه:
لِّلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَإِن تُبۡدُواْ مَا فِيٓ أَنفُسِكُمۡ أَوۡ تُخۡفُوهُ يُحَاسِبۡكُم بِهِ ٱللَّهُۖ فَيَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
284. በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹት ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል የሚሻውን ሰው ይምራል:: የሚሻውንም ሰው ይቀጣል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና:: ይተሳሰባችኋል፡፡
عربي تفسیرونه:
ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّن رُّسُلِهِۦۚ وَقَالُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۖ غُفۡرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيۡكَ ٱلۡمَصِيرُ
285. መልዕክተኛው (ሙሐመድ) ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደለት (ቁርኣን) አምኗል:: አማኞችም እንደዚሁ አመኑ:: ሁሉም በአላህ፣ በመልዕክቱ፣ በመጽሐፉትና በመልዕክተኞቹ «ከእነርሱ በአንዱም መካከል አንለይም (አንክድም)» የሚሉ ሲሆኑ አመኑ:: «የአላህን ትዕዛዛትንም ሰማን ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምህረትህን እንሻለን :: የሁሉም መመለሻ ወደ አንተው ብቻ ነው። አሉም::
عربي تفسیرونه:
لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ لَهَا مَا كَسَبَتۡ وَعَلَيۡهَا مَا ٱكۡتَسَبَتۡۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذۡنَآ إِن نَّسِينَآ أَوۡ أَخۡطَأۡنَاۚ رَبَّنَا وَلَا تَحۡمِلۡ عَلَيۡنَآ إِصۡرٗا كَمَا حَمَلۡتَهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِنَاۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلۡنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِۦۖ وَٱعۡفُ عَنَّا وَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَآۚ أَنتَ مَوۡلَىٰنَا فَٱنصُرۡنَا عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
286. አላህ የትኛዋንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም:: ነፍስ ሁሉ ለሰራችው መልካም ስራ ሁሉ ተገቢው ምንዳ አላት:: በእርሷም ላይ ባፈራችው (ኃጢአት) ተገቢው ቅጣት አለባት:: (ሙስሊሞች) «ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንሳሳት (አትቅጣን):: ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ እንደጫንከው ሁሉ በእኛ ላይ አትጫንብን:: ጌታችን ሆይ! ለእኛ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን:: ለእኛም ይቅርታ አድርግልን:: ለእኛም ምህረትን አድርግልን:: እዘንልንም:: ረዳታችን አንተ ብቻ ነህና:: በከሓዲ ሕዝቦች ላይም ድልን አጎናጽፈን።» (በሉ።)
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: بقره
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول