Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: معارج   آیت:
يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ
11. (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል::
عربي تفسیرونه:
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ
12. በሚስቱም በወንድሙም፤
عربي تفسیرونه:
وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ
13. በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤
عربي تفسیرونه:
وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ يُنجِيهِ
14. በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል)::
عربي تفسیرونه:
كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ
15. ይተው፤እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት።
عربي تفسیرونه:
نَزَّاعَةٗ لِّلشَّوَىٰ
16. የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤
عربي تفسیرونه:
تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ
17. (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች::
عربي تفسیرونه:
وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ
18. ገንዘብን የሰበሰበንና ዘካውን ሳይሰጥ የቆጠረንም (ትጠራለች)::
عربي تفسیرونه:
۞ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا
19. ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ::
عربي تفسیرونه:
إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعٗا
20. ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا
21. መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ::
عربي تفسیرونه:
إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ
22. ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ::
عربي تفسیرونه:
ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ
23. እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት::
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ مَّعۡلُومٞ
24. እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤
عربي تفسیرونه:
لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ
25. ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)፤
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
26. እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት የሚያረጋግጡ::
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ
27. እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونٖ
28. የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና።
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ
29. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤
عربي تفسیرونه:
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ
30. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር:: እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና::
عربي تفسیرونه:
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ
31. ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ
32. እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት::
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ
33. እነዚያም እነርሱ በምስክሮቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት::
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ
34. እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት::
عربي تفسیرونه:
أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتٖ مُّكۡرَمُونَ
35. እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው::
عربي تفسیرونه:
فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ
36. እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
عربي تفسیرونه:
عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ
37. ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤
عربي تفسیرونه:
أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٖ
38. ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
عربي تفسیرونه:
كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ
39. ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍተወት ጠብታ) ፈጠርናቸው::
عربي تفسیرونه:
فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ
40. (እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: معارج
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول