Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: مدثر   آیت:
فَقُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ
19. እናም ተረገመ:: እንዴት ገመተ!
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ قُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ
20. ከዚያ ተረገመ። እንዴትስ ገመተ!
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ نَظَرَ
21. ከዚያም እንደገና (በቁርኣን ጉዳይ) ተመለከተ።
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ
22. ከዚያ ፊቱን አጨፈገገ አኮማተረም::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ أَدۡبَرَ وَٱسۡتَكۡبَرَ
23. ከዚያ (በአላህ ከማመን) ዞረ:: ኮራም::
عربي تفسیرونه:
فَقَالَ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ يُؤۡثَرُ
24. «ይህ ከሌላ (ሰው) የሚቀዳ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
عربي تفسیرونه:
إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا قَوۡلُ ٱلۡبَشَرِ
25. «ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም» አለ::
عربي تفسیرونه:
سَأُصۡلِيهِ سَقَرَ
26. ሰቀር (በተባለ የገሀነም ዋሻ ውስጥ) በእርግጥ አስገባዋለሁ::
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سَقَرُ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰቀር ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
عربي تفسیرونه:
لَا تُبۡقِي وَلَا تَذَرُ
28. (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም:: አትተዉምም::
عربي تفسیرونه:
لَوَّاحَةٞ لِّلۡبَشَرِ
29. የሰዎችን ቆዳ በጣም አክሳይ ናት።
عربي تفسیرونه:
عَلَيۡهَا تِسۡعَةَ عَشَرَ
30. በእርሷም ላይ አስራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት::
عربي تفسیرونه:
وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةٗۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنٗا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ
31. የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::
عربي تفسیرونه:
كَلَّا وَٱلۡقَمَرِ
32. (ከክህደት) ይከልከሉ:: በጨረቃ (እምላለሁ)፤
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّيۡلِ إِذۡ أَدۡبَرَ
33. በሌሊቱም በሄደ ጊዜ፤
عربي تفسیرونه:
وَٱلصُّبۡحِ إِذَآ أَسۡفَرَ
34. በንጋቱም ባበራ ጊዜ እምላለሁ።
عربي تفسیرونه:
إِنَّهَا لَإِحۡدَى ٱلۡكُبَرِ
35. (ሰቀር) ከታላላቆች አደጋዎች አንዱ፤
عربي تفسیرونه:
نَذِيرٗا لِّلۡبَشَرِ
36. ለሰዎች አስፈራሪ ናት።
عربي تفسیرونه:
لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَتَقَدَّمَ أَوۡ يَتَأَخَّرَ
37. ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለፈለገ (ሰው) ሁሉ፤
عربي تفسیرونه:
كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ رَهِينَةٌ
38. ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ተያዥ ናት::
عربي تفسیرونه:
إِلَّآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡيَمِينِ
39. እነዚያ መዝገባቸውን በቀኝ እጃቸው የሚሰጡት ብቻ ሲቀሩ::
عربي تفسیرونه:
فِي جَنَّٰتٖ يَتَسَآءَلُونَ
40. (እነርሱማ) በገነቶች ውስጥ ሁነው እርስ በራሳቸው ይጠያየቃሉ::
عربي تفسیرونه:
عَنِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
41. ከአመጸኞች ሁኔታ (ይጠያየቃሉ)
عربي تفسیرونه:
مَا سَلَكَكُمۡ فِي سَقَرَ
42. (ከዚያ ለእነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል።) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّينَ
43. «ከሰጋጆች አልነበርንም።
عربي تفسیرونه:
وَلَمۡ نَكُ نُطۡعِمُ ٱلۡمِسۡكِينَ
44. «ለድሆችም የምናበላም አልነበርንም።
عربي تفسیرونه:
وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلۡخَآئِضِينَ
45. «ከዘባራቂዎችም ጋር እንዘባርቅ ነበር።
عربي تفسیرونه:
وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
46. «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበር፤
عربي تفسیرونه:
حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلۡيَقِينُ
47. «እርግጠኛው ነገር ሞት እስከመጣብን ድረስ።» ይላሉ
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: مدثر
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول