Check out the new design

ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය * - පරිවර්තන පටුන

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

අර්ථ කථනය පරිච්ඡේදය: අල් අන්ආම්   වාක්‍යය:
قُلۡ أَيُّ شَيۡءٍ أَكۡبَرُ شَهَٰدَةٗۖ قُلِ ٱللَّهُۖ شَهِيدُۢ بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۚ وَأُوحِيَ إِلَيَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ لِأُنذِرَكُم بِهِۦ وَمَنۢ بَلَغَۚ أَئِنَّكُمۡ لَتَشۡهَدُونَ أَنَّ مَعَ ٱللَّهِ ءَالِهَةً أُخۡرَىٰۚ قُل لَّآ أَشۡهَدُۚ قُلۡ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ وَإِنَّنِي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ
19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምስክርነት ሁሉ ይበልጥ ታላቁ የትኛው ነው?» በላቸው። «አላህ፤ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው። ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውንም ሁሉ ላስፈራራበት ወደ እኔ ተወረደ:: ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላቸሁን?» በላቸው:: «እኔ ግን ፈጽሞ በዚህ አልመሰክርም።» በላቸው:: «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔም በአላህ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡرِفُونَهُۥ كَمَا يَعۡرِفُونَ أَبۡنَآءَهُمُۘ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
20. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው አይሁድና ክርስቲያኖች ልክ ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ ሙሐመድንም በትክክል ያውቁታል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ ፈጽሞ አያምኑም::
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
21. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአናቅጽ ካስተባበለ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም።
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
وَيَوۡمَ نَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ أَيۡنَ شُرَكَآؤُكُمُ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ
22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁላቸውንም በምንሰበሰብበትና ከዚያም ለእነዚያም በአላህ ላጋሩት፤ «‹እነዚያም ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው› ብላችሁ ታስቧቸው የነበሩት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው?» የምንልበትን ቀን (አስታውስ)።
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
ثُمَّ لَمۡ تَكُن فِتۡنَتُهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ وَٱللَّهِ رَبِّنَا مَا كُنَّا مُشۡرِكِينَ
23. ከዚያም የፊትና መልሳቸው «በጌታችን በአላህ ይሁንብን አጋሪዎች አልነበርንም።» ማለት እንጂ ሌላ አይሆንም።
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
ٱنظُرۡ كَيۡفَ كَذَبُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡۚ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነፍሶቻቸው ላይ እንዴት እንደዋሹና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ሁሉ ከእነርሱ እንዴት እንደተሰወረባቸው ተመልከት::
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
وَمِنۡهُم مَّن يَسۡتَمِعُ إِلَيۡكَۖ وَجَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۚ وَإِن يَرَوۡاْ كُلَّ ءَايَةٖ لَّا يُؤۡمِنُواْ بِهَاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوكَ يُجَٰدِلُونَكَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
25. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አለ:: በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ላይ እንዳይሰሙት ድንቁርናን አደረግን:: ተዐምርን ሁሉ እንኳን ቢያዩ በእርሷ አያምኑም:: ወደ አንተ በመጡ ጊዜ የሚከራከሩህ ሆነው እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን የቀድሞዎቹ ሰዎች ጹሑፍ ተረቶች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
وَهُمۡ يَنۡهَوۡنَ عَنۡهُ وَيَنۡـَٔوۡنَ عَنۡهُۖ وَإِن يُهۡلِكُونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ
26. እነርሱም ሰዎችን ከእርሱ ይከልክላሉ፤ ከእርሱም ይርቃሉ፤ በዚህም ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን አያጠፉም:: ግን አያውቁም::
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ وُقِفُواْ عَلَى ٱلنَّارِ فَقَالُواْ يَٰلَيۡتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእሳትም ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ «ምን ነው ወደ ምድረ ዓለም በተመለስንና በጌታችን አናቅጽ ባላስተባበልን ከትክክለኛ አማኞችም ጋር በሆንን ዋ! ምኞታችን።» ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያስደነግጥህን ነገር ባየህ ነበር)
අල්කුර්ආන් අරාබි අර්ථ විවරණ:
 
අර්ථ කථනය පරිච්ඡේදය: අල් අන්ආම්
සූරා පටුන පිටු අංක
 
ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය - පරිවර්තන පටුන

මොහමඩ් සෙයින් සහර් අල් දීන් විසින් පරිවර්තනය කරන ලදී. අප්‍රිකානු අකඩමියෙන් ප්‍රකාශිතය.

වසන්න