Check out the new design

แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา * - สารบัญ​คำแปล


แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: Yūsuf   อายะฮ์:
فَلَمَّا ذَهَبُواْ بِهِۦ وَأَجۡمَعُوٓاْ أَن يَجۡعَلُوهُ فِي غَيَٰبَتِ ٱلۡجُبِّۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ لَتُنَبِّئَنَّهُم بِأَمۡرِهِمۡ هَٰذَا وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
15. እርሱንም ወስደውት በጉድጓድ ወለል ላይ ሊጥሉት በወሰኑ ጊዜ «እነርሱ ሳያውቁ ይህን ጸያፍ ተግባራቸውን ወደ ፊት ትነግራቸዋለህ» የሚል መልዕክት ላክንለት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَجَآءُوٓ أَبَاهُمۡ عِشَآءٗ يَبۡكُونَ
16. አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
قَالُواْ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّا ذَهَبۡنَا نَسۡتَبِقُ وَتَرَكۡنَا يُوسُفَ عِندَ مَتَٰعِنَا فَأَكَلَهُ ٱلذِّئۡبُۖ وَمَآ أَنتَ بِمُؤۡمِنٖ لَّنَا وَلَوۡ كُنَّا صَٰدِقِينَ
17. «አባታችን ሆይ! እኛ ለሩጫና ለውርወራ ልንሽቀዳደም ሄድን። ዩሱፍንም እቃችን ዘንድ ተውነው:: ወዲያዉም ተኩላ በላው:: አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም።» አሉ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَجَآءُو عَلَىٰ قَمِيصِهِۦ بِدَمٖ كَذِبٖۚ قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٞۖ وَٱللَّهُ ٱلۡمُسۡتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ
18. በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ:: አባታቸውም: «ይህ ትክክል አይደለም። ይልቁን ነፍሶቻችሁ ውሸት ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ:: ስለዚህ መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው።» አለ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَجَآءَتۡ سَيَّارَةٞ فَأَرۡسَلُواْ وَارِدَهُمۡ فَأَدۡلَىٰ دَلۡوَهُۥۖ قَالَ يَٰبُشۡرَىٰ هَٰذَا غُلَٰمٞۚ وَأَسَرُّوهُ بِضَٰعَةٗۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ
19. መንገደኞችም መጡ:: ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ:: አኮሌውንም ወደ ጉድጎዱ ሰደደ:: የምስራች:: «ይህ ልጅ ነው።» አለ:: ሸቀጥ አድርገዉም ደበቁት:: አላህ የሚሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَشَرَوۡهُ بِثَمَنِۭ بَخۡسٖ دَرَٰهِمَ مَعۡدُودَةٖ وَكَانُواْ فِيهِ مِنَ ٱلزَّٰهِدِينَ
20. በርካሽ ዋጋና በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት:: በእርሱም ላይ ከቸልተኞቹ ነበሩ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَقَالَ ٱلَّذِي ٱشۡتَرَىٰهُ مِن مِّصۡرَ لِٱمۡرَأَتِهِۦٓ أَكۡرِمِي مَثۡوَىٰهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوۡ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدٗاۚ وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلِنُعَلِّمَهُۥ مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِۚ وَٱللَّهُ غَالِبٌ عَلَىٰٓ أَمۡرِهِۦ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
21. ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «ይህ ልጅ መኖሪያውን አክብሪ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጅላልና።» አላት:: ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ገዥ ልናደርገውና የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አሸናፊ ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን አያውቁም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥٓ ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
22. ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ልክ እንደዚህም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
 
แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: Yūsuf
สารบัญสูเราะฮ์ หมายเลข​หน้า​
 
แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา - สารบัญ​คำแปล

แปลโดย มุฮัมมัด ซายน์ ซะฮ์รุดดีน. จัดพิมพ์โดยสถาบันแอฟริกา

ปิด