Check out the new design

แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา * - สารบัญ​คำแปล


แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: An-Noor   อายะฮ์:
يُقَلِّبُ ٱللَّهُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ
44. አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፤ በዚህም ለአስተዋዮች በእርግጥ ማስረጃ አለበት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱللَّهُ خَلَقَ كُلَّ دَآبَّةٖ مِّن مَّآءٖۖ فَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰ بَطۡنِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰ رِجۡلَيۡنِ وَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰٓ أَرۡبَعٖۚ يَخۡلُقُ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
45. አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ:: ከእነርሱም መካከል በሆዱ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በሁለት እግሮቹ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በአራት እግሩ የሚሄድ አለ:: አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
لَّقَدۡ أَنزَلۡنَآ ءَايَٰتٖ مُّبَيِّنَٰتٖۚ وَٱللَّهُ يَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
46. አብራሪን አናቅጽ በእርግጥ አወረድን፤ አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራዋል::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَيَقُولُونَ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَبِٱلرَّسُولِ وَأَطَعۡنَا ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٞ مِّنۡهُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَۚ وَمَآ أُوْلَٰٓئِكَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ
47. (አስመሳዮች) «በአላህና በመልዕክተኛው አምነናል ታዘናልም» ይላሉ። ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ከፊሉ ይሸሻል:: እነዚያም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِذَا دُعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ إِذَا فَرِيقٞ مِّنۡهُم مُّعۡرِضُونَ
48. ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛዉም በመካከላቸው ለሚከሰቱ ጉዳዮች ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِن يَكُن لَّهُمُ ٱلۡحَقُّ يَأۡتُوٓاْ إِلَيۡهِ مُذۡعِنِينَ
49. እውነቱም (ሐቁ) ለእነርሱ ቢሆን ወደ እርሱ ታዛዣች ሆነው ይመጣሉ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَفِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ أَمِ ٱرۡتَابُوٓاْ أَمۡ يَخَافُونَ أَن يَحِيفَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَرَسُولُهُۥۚ بَلۡ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
50. በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ አለን? ወይስ በነብይነቱ ተጠራጠሩን? ወይስ አላህና መልዕክተኛው በእነርሱ ላይ የሚበድሉ መሆንን ይፈራሉን? ይልቁንም እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّمَا كَانَ قَوۡلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذَا دُعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ أَن يَقُولُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
51. የምዕምናን ቃል ግን የነበረው ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ «ሰማን ታዘዝንም» ማለት ብቻ ነው:: እነዚህ ማለት እነዚያ የፈለጉትን የሚያገኙቱ ናቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَخۡشَ ٱللَّهَ وَيَتَّقۡهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ
52. አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ፤ አላህንም የሚፈራና ቁጣውን የሚጠነቀቀው፤ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ እነዚያ እነርሱ ናቸው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
۞ وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِنۡ أَمَرۡتَهُمۡ لَيَخۡرُجُنَّۖ قُل لَّا تُقۡسِمُواْۖ طَاعَةٞ مَّعۡرُوفَةٌۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዘመቻ ብታዛቸው በእርግጥ እንደሚወጡ የጠነከሩ መሓላዎቻቸውን በአላህ ስም ይምላሉ፤ «አትማሉ:: የታወቀ የንፍቅና መታዘዝ ነውና:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
 
แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: An-Noor
สารบัญสูเราะฮ์ หมายเลข​หน้า​
 
แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา - สารบัญ​คำแปล

แปลโดย มุฮัมมัด ซายน์ ซะฮ์รุดดีน. จัดพิมพ์โดยสถาบันแอฟริกา

ปิด