แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - الترجمة الأمهرية - زين * - สารบัญ​คำแปล


แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: Al-‘Ankabūt   อายะฮ์:

ሱረቱ አል ዐንከቡት

الٓمٓ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَحَسِبَ ٱلنَّاسُ أَن يُتۡرَكُوٓاْ أَن يَقُولُوٓاْ ءَامَنَّا وَهُمۡ لَا يُفۡتَنُونَ
2. ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ (ከአላህ በልዩ ልዩ ነገሮች) ሳይፈተኑ የሚተው መሰላቸውን?
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَقَدۡ فَتَنَّا ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ فَلَيَعۡلَمَنَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ صَدَقُواْ وَلَيَعۡلَمَنَّ ٱلۡكَٰذِبِينَ
3. እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትንም ህዝቦች በርግጥ ፈትነናል። እነዚያን እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል። ውሸታሞችንም ያውቃል።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَمۡ حَسِبَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن يَسۡبِقُونَاۚ سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ
4.ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሰዎች የሚያመልጡን መሰላቸውን? ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
مَن كَانَ يَرۡجُواْ لِقَآءَ ٱللَّهِ فَإِنَّ أَجَلَ ٱللَّهِ لَأٓتٖۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
5. የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ሁሉ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነው:: እርሱም ሰሚም ሁሉን አዋቂ ነው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَن جَٰهَدَ فَإِنَّمَا يُجَٰهِدُ لِنَفۡسِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ ٱلۡعَٰلَمِينَ
6. በአላህ መንገድ ላይ የታገለ ሰው የሚታገለው ለነፍሱ ብቻ ነው:: አላህ ከዓለማት ሁሉ በእርግጥ የተብቃቃ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُكَفِّرَنَّ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَحۡسَنَ ٱلَّذِي كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
7. እነዚያም በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑና መልካም ተግባራትንም የሠሩ መጥፎ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ ላይ እናብስላቸዋለን። በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَوَصَّيۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيۡهِ حُسۡنٗاۖ وَإِن جَٰهَدَاكَ لِتُشۡرِكَ بِي مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٞ فَلَا تُطِعۡهُمَآۚ إِلَيَّ مَرۡجِعُكُمۡ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
8. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ መልካም ተግባርን ሁሉ እንዲፈጽም አዘዝነው:: ወላጆችም ላንተም በእርሱ እውቀት የሌለህን ጣኦት በእኔ እንድታጋራው ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ እነግራችኋለሁ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُدۡخِلَنَّهُمۡ فِي ٱلصَّٰلِحِينَ
9. እነዚያንም በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከደጋጎቹ ውስጥ በእርግጥ እናስገባቸዋለን::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ فَإِذَآ أُوذِيَ فِي ٱللَّهِ جَعَلَ فِتۡنَةَ ٱلنَّاسِ كَعَذَابِ ٱللَّهِۖ وَلَئِن جَآءَ نَصۡرٞ مِّن رَّبِّكَ لَيَقُولُنَّ إِنَّا كُنَّا مَعَكُمۡۚ أَوَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِأَعۡلَمَ بِمَا فِي صُدُورِ ٱلۡعَٰلَمِينَ
10. ከሰዎች መካከል «በአላህ አመንን።» የሚል ሰው አለ:: ከዚያ በአላህ በማመኑ ምክኒያት በተሰቃየ ጊዜ የሰዎችን ማሰቃየት እንደ አላህ ቅጣት ያደርጋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም እርዳታ ቢመጣ እኛ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነበርን ይላሉ:: አላህ በዓለማት ሕዝብ ልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ አይደለምን?
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَيَعۡلَمَنَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَيَعۡلَمَنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ
11. አላህ እነዚያንም በትክክል ያመኑትን በእርግጥ ያውቃል:: መናፍቆቹንም ያውቃል::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّبِعُواْ سَبِيلَنَا وَلۡنَحۡمِلۡ خَطَٰيَٰكُمۡ وَمَا هُم بِحَٰمِلِينَ مِنۡ خَطَٰيَٰهُم مِّن شَيۡءٍۖ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ
12. እነዚያንም የካዱት ሰዎች ለእነዚያ ላመኑት «መንገዳችንን ተከተሉ:: ኃጢአቶቻችሁንም እንሸከማለን» አሉ:: እነርሱም ከኃጢአቶቻቸው ምንንም ተሸካሚዎች አይደሉም:: እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَيَحۡمِلُنَّ أَثۡقَالَهُمۡ وَأَثۡقَالٗا مَّعَ أَثۡقَالِهِمۡۖ وَلَيُسۡـَٔلُنَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَمَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
13. ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር ሌሎች ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ:: በትንሳኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት ሁሉ በእርግጥ ይጠየቃሉ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَلَبِثَ فِيهِمۡ أَلۡفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمۡسِينَ عَامٗا فَأَخَذَهُمُ ٱلطُّوفَانُ وَهُمۡ ظَٰلِمُونَ
14. ኑሕንም ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው:: በውስጣቸዉም ሺህ ዓመትን ሀምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ:: እነርሱ በዳዮች ሆነዉም የውሃው ማዕበል አጥለቀለቃቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَصۡحَٰبَ ٱلسَّفِينَةِ وَجَعَلۡنَٰهَآ ءَايَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ
15. ኑህንና የመርከቢቱን ጓዶች አዳንናቸው:: እርሷንም ለዓለማት ተዓምር አደረግናት::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِبۡرَٰهِيمَ إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُۖ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
16. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ኢብራሒም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)። «አላህን ተገዙ ፍሩትም ይህን ማድረጋችሁ የምታውቁት ብትሆኑ ለናንተ በላጭ ነው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡثَٰنٗا وَتَخۡلُقُونَ إِفۡكًاۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمۡلِكُونَ لَكُمۡ رِزۡقٗا فَٱبۡتَغُواْ عِندَ ٱللَّهِ ٱلرِّزۡقَ وَٱعۡبُدُوهُ وَٱشۡكُرُواْ لَهُۥٓۖ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
17. (ሰዎች ሆይ!) ከአላህ ሌላ የምትገዙት ጣኦታትን ብቻ ነው:: ውሸትንም ትቀጥፋላችሁ:: እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም:: ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ:: ተገዙትም:: ለርሱም አመስግኑ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِن تُكَذِّبُواْ فَقَدۡ كَذَّبَ أُمَمٞ مِّن قَبۡلِكُمۡۖ وَمَا عَلَى ٱلرَّسُولِ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ
18. ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ህዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል:: በመልዕክተኛዉም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ كَيۡفَ يُبۡدِئُ ٱللَّهُ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥٓۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ
19. አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀምርና ከዚያ እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን? ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ بَدَأَ ٱلۡخَلۡقَۚ ثُمَّ ٱللَّهُ يُنشِئُ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأٓخِرَةَۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ:: እናም መፍጠርን እንዴት እንደጀመረ ተመልከቱ:: ከዚያም አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَيَرۡحَمُ مَن يَشَآءُۖ وَإِلَيۡهِ تُقۡلَبُونَ
21. የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ
22. እናንተ በምድርም ሆነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም። ከአላህም ሌላ ወዳጅም ተከላካይም ምንም የላችሁም።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَلِقَآئِهِۦٓ أُوْلَٰٓئِكَ يَئِسُواْ مِن رَّحۡمَتِي وَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
23. እነዚያም በአላህ አናቅጽና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ:: እነዚያም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُواْ ٱقۡتُلُوهُ أَوۡ حَرِّقُوهُ فَأَنجَىٰهُ ٱللَّهُ مِنَ ٱلنَّارِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
24. የህዝቦቹም መልስ፡- «ግደሉት ወይም አቃጥሉት።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም። ከዚያም ከእሳቲቱ አላህ አዳነው። በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ብዙ ተዐምራት አሉበት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَقَالَ إِنَّمَا ٱتَّخَذۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡثَٰنٗا مَّوَدَّةَ بَيۡنِكُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ ثُمَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَكۡفُرُ بَعۡضُكُم بِبَعۡضٖ وَيَلۡعَنُ بَعۡضُكُم بَعۡضٗا وَمَأۡوَىٰكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن نَّٰصِرِينَ
25. (ኢብራሂም) አለ፡- «ከአላህ ሌላ ጣኦታትን አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ህይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው። ከዚያም በትንሳኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል:: ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል:: መኖሪያችሁም እሳት ናት:: ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።»
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
۞ فَـَٔامَنَ لَهُۥ لُوطٞۘ وَقَالَ إِنِّي مُهَاجِرٌ إِلَىٰ رَبِّيٓۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
26. ከዚያም ሉጥ ለእርሱ አመነ:: (ኢብራሂምም) «እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ:: እነሆ እርሱ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና።» አለ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَجَعَلۡنَا فِي ذُرِّيَّتِهِ ٱلنُّبُوَّةَ وَٱلۡكِتَٰبَ وَءَاتَيۡنَٰهُ أَجۡرَهُۥ فِي ٱلدُّنۡيَاۖ وَإِنَّهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
27. ለእርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው በዘሩም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍን አደረግን:: ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلُوطًا إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ إِنَّكُمۡ لَتَأۡتُونَ ٱلۡفَٰحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنۡ أَحَدٖ مِّنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ: «እናንተ ጠያፍን ሥራ ትሰራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም ሰው አልቀደማችሁም።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَئِنَّكُمۡ لَتَأۡتُونَ ٱلرِّجَالَ وَتَقۡطَعُونَ ٱلسَّبِيلَ وَتَأۡتُونَ فِي نَادِيكُمُ ٱلۡمُنكَرَۖ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُواْ ٱئۡتِنَا بِعَذَابِ ٱللَّهِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
29. «እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድንም ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን?» አላቸው:: የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
30. «ጌታዬ ሆይ! በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ።» አለ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَمَّا جَآءَتۡ رُسُلُنَآ إِبۡرَٰهِيمَ بِٱلۡبُشۡرَىٰ قَالُوٓاْ إِنَّا مُهۡلِكُوٓاْ أَهۡلِ هَٰذِهِ ٱلۡقَرۡيَةِۖ إِنَّ أَهۡلَهَا كَانُواْ ظَٰلِمِينَ
31. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በብስራት በመጡ ጊዜ «እኛ የዚችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን ሰዎችዋ በዳዮች ነበሩና።» አሉት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
قَالَ إِنَّ فِيهَا لُوطٗاۚ قَالُواْ نَحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَن فِيهَاۖ لَنُنَجِّيَنَّهُۥ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ
32. «በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ?» አላቸው:: «እኛ በውስጧ ያለውን ካንተ ይበልጥ አዋቂ ነን:: እርሱንማ በእርግጥ እናድነዋለን:: ቤተሰቦቹንም ጭምር ሚስቱ ብቻ ስትቀር እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት።» አሉት::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَمَّآ أَن جَآءَتۡ رُسُلُنَا لُوطٗا سِيٓءَ بِهِمۡ وَضَاقَ بِهِمۡ ذَرۡعٗاۖ وَقَالُواْ لَا تَخَفۡ وَلَا تَحۡزَنۡ إِنَّا مُنَجُّوكَ وَأَهۡلَكَ إِلَّا ٱمۡرَأَتَكَ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ
33. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡት ጊዜ በነሱ ምክንያት አዘነ:: በእነርሱም ልቡ ተጨነቀ። አሉትም: «አትፍራ። አትዘንም። እኛ አዳኞችህ ነን:: ቤተሰቦችህንም ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እርሷ ግን በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ ናት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّا مُنزِلُونَ عَلَىٰٓ أَهۡلِ هَٰذِهِ ٱلۡقَرۡيَةِ رِجۡزٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ
34. «እኛ በዚህ ከተማ ሰዎች ላይ ያምጹ በነበሩበት ምክንያት ከሰማይ ቅጣትን አውራጆች ነን።» (አሉት)
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَقَد تَّرَكۡنَا مِنۡهَآ ءَايَةَۢ بَيِّنَةٗ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
35. በእርግጥም ለሚያስቡ ሰዎች ሁሉ ከእርሷ ግልጽ ምልክትን ተውን (አስቀረን)::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗا فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱرۡجُواْ ٱلۡيَوۡمَ ٱلۡأٓخِرَ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ
36. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ:: የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ:: በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ።» አላቸው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دَارِهِمۡ جَٰثِمِينَ
37. እናም አስተባበሉትና የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው፡፡ ባገራቸዉም ውስጥ ተንከፍረው አደሩ (አነጉ)።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَعَادٗا وَثَمُودَاْ وَقَد تَّبَيَّنَ لَكُم مِّن مَّسَٰكِنِهِمۡۖ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَصَدَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَكَانُواْ مُسۡتَبۡصِرِينَ
38. ዓድንና ሠሙድንም አጠፋን:: የመኖሪያዎቻቸውን ፍርስራሾች በማየት መጥፋታቸው ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ:: ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው:: ከመንገድም አገዳቸው:: የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ:: ግን አላስተዋሉም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَقَٰرُونَ وَفِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مُّوسَىٰ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا كَانُواْ سَٰبِقِينَ
39. ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም አጠፋን:: ሙሳም በተዐምራት በእርግጥ መጣባቸው:: በምድርም ላይ ኮሩ:: አምላጮችም አልነበሩም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
فَكُلًّا أَخَذۡنَا بِذَنۢبِهِۦۖ فَمِنۡهُم مَّنۡ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِ حَاصِبٗا وَمِنۡهُم مَّنۡ أَخَذَتۡهُ ٱلصَّيۡحَةُ وَمِنۡهُم مَّنۡ خَسَفۡنَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ وَمِنۡهُم مَّنۡ أَغۡرَقۡنَاۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
40. ሁሉንም በኃጢአቱ ያዝነው:: ከእነርሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፍስን የላክንበት አለ:: ከእነርሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አለ:: ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አለ:: ከእነርሱም ውስጥ ያሰመጥነው አለ:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
مَثَلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡلِيَآءَ كَمَثَلِ ٱلۡعَنكَبُوتِ ٱتَّخَذَتۡ بَيۡتٗاۖ وَإِنَّ أَوۡهَنَ ٱلۡبُيُوتِ لَبَيۡتُ ٱلۡعَنكَبُوتِۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
41. የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣኦታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደሠራች ሸረሪት ብጤ ነው:: ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው:: ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይገዟቸዉም ነበር::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مِن شَيۡءٖۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
42. አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚገዙትን ማንኛውንም ያውቃል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና ጥበበኛው ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَتِلۡكَ ٱلۡأَمۡثَٰلُ نَضۡرِبُهَا لِلنَّاسِۖ وَمَا يَعۡقِلُهَآ إِلَّا ٱلۡعَٰلِمُونَ
43. እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን:: ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎችአያውቋትም፡፡
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
خَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ
44. አላህም ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፤ በዚህ ውስጥ ለአማኞች ተዐምር አለበት።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ٱتۡلُ مَآ أُوحِيَ إِلَيۡكَ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَۖ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ تَنۡهَىٰ عَنِ ٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِۗ وَلَذِكۡرُ ٱللَّهِ أَكۡبَرُۗ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا تَصۡنَعُونَ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጽሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ:: ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና:: አላህን ማውሳት ከመልካም ነገር ሁሉ በላጭ ነው:: አላህም የምትሠሩትን ስራ ሁሉ ያውቃል::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
۞ وَلَا تُجَٰدِلُوٓاْ أَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡهُمۡۖ وَقُولُوٓاْ ءَامَنَّا بِٱلَّذِيٓ أُنزِلَ إِلَيۡنَا وَأُنزِلَ إِلَيۡكُمۡ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمۡ وَٰحِدٞ وَنَحۡنُ لَهُۥ مُسۡلِمُونَ
46. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር የመጽሐፉ ባለቤቶችን በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ:። በሉም፡- «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን:: አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው:: እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን።»
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَۚ فَٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يُؤۡمِنُونَ بِهِۦۖ وَمِنۡ هَٰٓؤُلَآءِ مَن يُؤۡمِنُ بِهِۦۚ وَمَا يَجۡحَدُ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَّا ٱلۡكَٰفِرُونَ
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንደዚሁም ወደ አንተ መጽሐፍን አወረድን:: እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው በእርሱ ያምናሉ:: ከእነዚህም (ከመካ) ሰዎች በእርሱ የሚያምኑ አሉ:: በተዓምራታችንም ከሓዲያን እንጂ ማንም አይክድም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَا كُنتَ تَتۡلُواْ مِن قَبۡلِهِۦ مِن كِتَٰبٖ وَلَا تَخُطُّهُۥ بِيَمِينِكَۖ إِذٗا لَّٱرۡتَابَ ٱلۡمُبۡطِلُونَ
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም:: ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
بَلۡ هُوَ ءَايَٰتُۢ بَيِّنَٰتٞ فِي صُدُورِ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَۚ وَمَا يَجۡحَدُ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَّا ٱلظَّٰلِمُونَ
49. አይደለም:: እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ እውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ የጠለቀ ግልፆች አናቅጽ ነው:: በአናቅጻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَقَالُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَٰتٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قُلۡ إِنَّمَا ٱلۡأٓيَٰتُ عِندَ ٱللَّهِ وَإِنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٞ مُّبِينٌ
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን «በእርሱ ላይ ከጌታው ዘንድ ተዐምራት ለምን አልተወረዱም?» አሉ:: »ተዐምራት ከአላህ ዘንድ ብቻ ናቸው:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَوَلَمۡ يَكۡفِهِمۡ أَنَّآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَرَحۡمَةٗ وَذِكۡرَىٰ لِقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
51. እኛ መጽሐፉን በእነርሱ ላይ የሚነበብ ሆኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ሁሉ ችሮታና ግሳጼ አለበት::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
قُلۡ كَفَىٰ بِٱللَّهِ بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡ شَهِيدٗاۖ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ وَكَفَرُواْ بِٱللَّهِ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ:: በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ያውቃል።» በላቸው:: እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑና በአላህ የካዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَيَسۡتَعۡجِلُونَكَ بِٱلۡعَذَابِ وَلَوۡلَآ أَجَلٞ مُّسَمّٗى لَّجَآءَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ وَلَيَأۡتِيَنَّهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅጣትም ያስቸኩሉሃል! የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር:: እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يَسۡتَعۡجِلُونَكَ بِٱلۡعَذَابِ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةُۢ بِٱلۡكَٰفِرِينَ
54. በቅጣት ያስቸኩሉሃል! ገሀነምም ከሓዲያንን በእርግጥ ከባቢ ናት::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يَوۡمَ يَغۡشَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِن فَوۡقِهِمۡ وَمِن تَحۡتِ أَرۡجُلِهِمۡ وَيَقُولُ ذُوقُواْ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
55. ቅጣቱ ከበላያቸው ከእግሮቻቸዉም ሥር በሚሸፍናቸው ቀን «ትሰሩት የነበራችሁትን ቅመሱ።» በሚላቸዉም ቀን ትከባቸዋለች።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يَٰعِبَادِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّ أَرۡضِي وَٰسِعَةٞ فَإِيَّٰيَ فَٱعۡبُدُونِ
56. እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት:: ብትቸገሩ ተሰደዱ እኔንም ብቻ ተገዙኝ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
كُلُّ نَفۡسٖ ذَآئِقَةُ ٱلۡمَوۡتِۖ ثُمَّ إِلَيۡنَا تُرۡجَعُونَ
57. ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ከዚያም ወደ እኛ ትመለሳላችሁ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُبَوِّئَنَّهُم مِّنَ ٱلۡجَنَّةِ غُرَفٗا تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ نِعۡمَ أَجۡرُ ٱلۡعَٰمِلِينَ
58. እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩ ከገነት በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን:: የሠራተኞችም ምንዳ ምንኛ አማረ!
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ
59. እነርሱ እነዚያ የታገሱ በጌታቸዉም ላይ የሚመኩ ናቸው፡
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَكَأَيِّن مِّن دَآبَّةٖ لَّا تَحۡمِلُ رِزۡقَهَا ٱللَّهُ يَرۡزُقُهَا وَإِيَّاكُمۡۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
60. ከተንቀሳቃሽ ፍጡራን ምግባቸውን የማይሸከሙ ብዙ ናቸው:: አላህ ይመግባቸዋል:: እናንተንም ይመግባል:: እርሱ ሰሚና አዋቂ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ
61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ ”አላህ ነው“ ይሉሃል:: ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ٱللَّهُ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦ وَيَقۡدِرُ لَهُۥٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ
62. አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሲሳይን ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّن نَّزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ مِنۢ بَعۡدِ مَوۡتِهَا لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ قُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡقِلُونَ
63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሰማይ ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው "አላህ ነው" ይሉሃል:: "ስለዚህ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነው።“ በላቸው:: ግን አብዛኞቻቸው ይህን አያውቁም።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَا هَٰذِهِ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَآ إِلَّا لَهۡوٞ وَلَعِبٞۚ وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَ لَهِيَ ٱلۡحَيَوَانُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
64. ይህም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለም:: የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ህይወት አገር ናት:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
فَإِذَا رَكِبُواْ فِي ٱلۡفُلۡكِ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ إِذَا هُمۡ يُشۡرِكُونَ
65. በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል:: ወደ የብስ በማውጣት ባዳናቸው ጊዜ ግን ወዲያውኑ እነርሱ ጣዖትን ያጋራሉ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
لِيَكۡفُرُواْ بِمَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ وَلِيَتَمَتَّعُواْۚ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
66. በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ ያጋራሉ፤ ወደ ፊትም የሚጠብቃቸውን ያውቃሉ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا جَعَلۡنَا حَرَمًا ءَامِنٗا وَيُتَخَطَّفُ ٱلنَّاسُ مِنۡ حَوۡلِهِمۡۚ أَفَبِٱلۡبَٰطِلِ يُؤۡمِنُونَ وَبِنِعۡمَةِ ٱللَّهِ يَكۡفُرُونَ
67. ሰዎቹ ከየዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ አገራቸውን ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን? በውድቅ ነገር ያምናሉን? በአላህም ጸጋ ይክዳሉን?
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُۥٓۚ أَلَيۡسَ فِي جَهَنَّمَ مَثۡوٗى لِّلۡكَٰفِرِينَ
68. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነት በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ሰው ይበልጥ ራሱን በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲያን መኖሪያ የለምን?(አለ)
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِينَ جَٰهَدُواْ فِينَا لَنَهۡدِيَنَّهُمۡ سُبُلَنَاۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَمَعَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
69. እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ ህዝቦችን መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን:: አላህ በእርግጥ ከበጎ ሰሪዎች ጋር ነውና፡:
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
 
แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: Al-‘Ankabūt
สารบัญสูเราะฮ์ หมายเลข​หน้า​
 
แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - الترجمة الأمهرية - زين - สารบัญ​คำแปล

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

ปิด