แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - الترجمة الأمهرية - زين * - สารบัญ​คำแปล


แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: Fātir   อายะฮ์:

ሱረቱ ፋጢር

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ جَاعِلِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلًا أُوْلِيٓ أَجۡنِحَةٖ مَّثۡنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَۚ يَزِيدُ فِي ٱلۡخَلۡقِ مَا يَشَآءُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
1. ምስጋና ሁሉ ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፤ መላእክትንም ባለ ሁለት ሁለት፤ ባለ ሶስት ሶስትና ባለ አራት አራት ክንፎች የሆኑ መላዕክተኞች አድራጊ ለሆነው አላህ ይገባው:: በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
مَّا يَفۡتَحِ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ مِن رَّحۡمَةٖ فَلَا مُمۡسِكَ لَهَاۖ وَمَا يُمۡسِكۡ فَلَا مُرۡسِلَ لَهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
2. አላህ ለሰዎች ከችሮታ የሚከፍታትን ለእርሷ ምንም አጋጅ የላትም:: የሚያግደዉም ከእርሱ በኋላ ለእርሱ ምንም ለቃቂ የለዉም:: እርሱ ብቸኛ አሸናፊና ጥበበኛ ው ነውና።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡۚ هَلۡ مِنۡ خَٰلِقٍ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ
3. እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ (ያለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدۡ كُذِّبَتۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِكَۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊት የነበሩ ነብያትም ህዝቦቻቸው አስተባብለዋቸዋል:: የሁሉ ነገር መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلۡغَرُورُ
5. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: እናም የቅርቢቱም ህይወት አታታላችሁ:: አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ ላይ አያታላችሁ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لَكُمۡ عَدُوّٞ فَٱتَّخِذُوهُ عَدُوًّاۚ إِنَّمَا يَدۡعُواْ حِزۡبَهُۥ لِيَكُونُواْ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
6. ሰይጣን ለእናንተ የለየለት ጠላት ነውና ስለዚህ እሱን ጠላት አድርጋችሁ ያዙት:: ሰይጣን ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَأَجۡرٞ كَبِيرٌ
7. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው:: እነዚያም በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ በአላህ ዘንድ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَفَمَن زُيِّنَ لَهُۥ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ فَرَءَاهُ حَسَنٗاۖ فَإِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۖ فَلَا تَذۡهَبۡ نَفۡسُكَ عَلَيۡهِمۡ حَسَرَٰتٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا يَصۡنَعُونَ
8. መጥፎ ሥራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?) አላህም የሚሻውን ሰው ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ላይ (ባለመቅናታቸው) ስለመቆላጨት ነፍስህ አትጥፋ፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱللَّهُ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ ٱلرِّيَٰحَ فَتُثِيرُ سَحَابٗا فَسُقۡنَٰهُ إِلَىٰ بَلَدٖ مَّيِّتٖ فَأَحۡيَيۡنَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ كَذَٰلِكَ ٱلنُّشُورُ
9. አላህም ያ ንፋሶችን የላከ ነው:: ከዚያም ዳመናዎችን ትቀሰቅሳለች። ወደ ሙት (ድርቅ) አገርም እንነዳዋለን:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው እናደርጋታለን:: ሙታንንም መቀስቀስ ልክ እነደዚሁ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡعِزَّةَ فَلِلَّهِ ٱلۡعِزَّةُ جَمِيعًاۚ إِلَيۡهِ يَصۡعَدُ ٱلۡكَلِمُ ٱلطَّيِّبُ وَٱلۡعَمَلُ ٱلصَّٰلِحُ يَرۡفَعُهُۥۚ وَٱلَّذِينَ يَمۡكُرُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞۖ وَمَكۡرُ أُوْلَٰٓئِكَ هُوَ يَبُورُ
10. ማሸነፍን የሚፈልግ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው። (እርሱን በመገዛት ይፈልገው):: መልካም ንግግር ወደ እርሱ (ወደ አላህ) ይወጣል:: በጎ ስራም ከፍ ያደርገዋል:: እነዚያ መጥፎ ስራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው :: የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ جَعَلَكُمۡ أَزۡوَٰجٗاۚ وَمَا تَحۡمِلُ مِنۡ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلۡمِهِۦۚ وَمَا يُعَمَّرُ مِن مُّعَمَّرٖ وَلَا يُنقَصُ مِنۡ عُمُرِهِۦٓ إِلَّا فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ
11. አላህም ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ዓይነቶች አደረጋችሁ:: የትኛዋም ሴት አታረግዝም አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን አንጂ:: እድሜው ከሚረዝምለትም አንድም አይረዘምለትም ከእድሜዉም አይጎድልበትም በመጽሀፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ገር ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡبَحۡرَانِ هَٰذَا عَذۡبٞ فُرَاتٞ سَآئِغٞ شَرَابُهُۥ وَهَٰذَا مِلۡحٌ أُجَاجٞۖ وَمِن كُلّٖ تَأۡكُلُونَ لَحۡمٗا طَرِيّٗا وَتَسۡتَخۡرِجُونَ حِلۡيَةٗ تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ فِيهِ مَوَاخِرَ لِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
12. ሁለቱ ባህሮች አይስተካከሉም ይህ ጣፋጭ፤ ጥምን ቆራጭ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው:: ይህኛው ደግሞ ጨው መርጋጋ ነው:: ከሁሉም እርጥብ ስጋን ትበላላችሁ:: የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑትም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۚ وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِيرٍ
13. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: ጸሀይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም እስከ ተወሰነለት ጊዜ ድረስ ይሮጣል :: ይህን የሚያደርገው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው :: ንግስናው የእሱ ብቻ ነው:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا يَسۡمَعُواْ دُعَآءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُواْ مَا ٱسۡتَجَابُواْ لَكُمۡۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِيرٖ
14. ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም:: በትንሳኤም ቀን እነርሱን በአላህ ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ አዋቂው አላህ ማንም አይነግርህም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ أَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ
15. እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ:: አላህም እርሱ ተብቃቂውና ምስጉኑ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَأۡتِ بِخَلۡقٖ جَدِيدٖ
16. (አላህ) ቢሻ ያስወግዳችሁና አዲስን ፍጡር ያመጣል (ይፈጥራል)::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٖ
17. ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ وَإِن تَدۡعُ مُثۡقَلَةٌ إِلَىٰ حِمۡلِهَا لَا يُحۡمَلۡ مِنۡهُ شَيۡءٞ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰٓۗ إِنَّمَا تُنذِرُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَۚ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفۡسِهِۦۚ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ
18. ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም:: የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰገዱትን ብቻ ነው:: ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው:: መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُ
19. እውርና የሚያይ አይሰተካከሉም፤
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَا ٱلظُّلُمَٰتُ وَلَا ٱلنُّورُ
20. ጨለማዎችና ብርሃንም፤
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَا ٱلظِّلُّ وَلَا ٱلۡحَرُورُ
21. ጥላና ሐሩርም።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَحۡيَآءُ وَلَا ٱلۡأَمۡوَٰتُۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُسۡمِعُ مَن يَشَآءُۖ وَمَآ أَنتَ بِمُسۡمِعٖ مَّن فِي ٱلۡقُبُورِ
22. ህያውና ሙታንም አይስተካከሉም:: አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ግን በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنۡ أَنتَ إِلَّا نَذِيرٌ
23. አንተ አስጠንቃቂ እንጂ ሌላ አይደለህም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗاۚ وَإِن مِّنۡ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٞ
24. እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ:: ማንኛይቱም ህዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدۡ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَبِٱلزُّبُرِ وَبِٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُنِيرِ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነዚህ ከበፊታቸው የነበሩትም ህዝቦች በእርግጥ ነብያትን አስተባብለዋል:: መልዕክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎች፣ በጹሁፎችም አብራሪ በሆነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ثُمَّ أَخَذۡتُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ
26. ከዚያም እነዚያን የካዱትን ቀጣኋቸው:: ቅጣቴም እንዴት ነበር! (በስፍራው ነው ተገቢ ነው)።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ ثَمَرَٰتٖ مُّخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهَاۚ وَمِنَ ٱلۡجِبَالِ جُدَدُۢ بِيضٞ وَحُمۡرٞ مُّخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهَا وَغَرَابِيبُ سُودٞ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱን አላየህምን? በእርሱም ዓይነቶቻቸው የተለያዩ ፍሬዎችን አወጣን:: ከጋራዎችም መልካቸው የተለያዩ ነጮችም፤ ቀዮችም፤ በጣም ጥቁሮችም የሆኑ መንገዶች አሉ።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ وَٱلدَّوَآبِّ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ مُخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهُۥ كَذَٰلِكَۗ إِنَّمَا يَخۡشَى ٱللَّهَ مِنۡ عِبَادِهِ ٱلۡعُلَمَٰٓؤُاْۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ
28. ከሰዎችም፤ ከተንቀሳቃሾችም፤ ከቤት እንስሳዎችም እንደዚሁ መልኮቻቸው የተለያዩ አሉ:: አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው:: አላህ አሸናፊና መሃሪ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَتۡلُونَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ يَرۡجُونَ تِجَٰرَةٗ لَّن تَبُورَ
29. እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ በምስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
لِيُوَفِّيَهُمۡ أُجُورَهُمۡ وَيَزِيدَهُم مِّن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ غَفُورٞ شَكُورٞ
30. ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ተስፋ ያደርጋሉ:: እርሱ በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ هُوَ ٱلۡحَقُّ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِعِبَادِهِۦ لَخَبِيرُۢ بَصِيرٞ
31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድነው ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ ሲሆን እርሱ እውነት ነው:: አላህ በእርግጥ በባሮቹ ውስጥ አዋቂና ተመልካች ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ثُمَّ أَوۡرَثۡنَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلَّذِينَ ٱصۡطَفَيۡنَا مِنۡ عِبَادِنَاۖ فَمِنۡهُمۡ ظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ وَمِنۡهُم مُّقۡتَصِدٞ وَمِنۡهُمۡ سَابِقُۢ بِٱلۡخَيۡرَٰتِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَضۡلُ ٱلۡكَبِيرُ
32. ከዚያ እነዚያ ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው :: ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አለ:: ከእነርሱም መካከለኛ አለ:: ከእነርሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አለ:: ያንኑ ማውረስ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَلُؤۡلُؤٗاۖ وَلِبَاسُهُمۡ فِيهَا حَرِيرٞ
33. የመኖሪያ ገነቶችን በውስጧ የወርቅ አንባሮችን ሉልንም የሚሸለሙ ሆነው ይገቡበታል:: በእርሷ ውስጥ አልባሳታቸዉም ሀር ነው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِيٓ أَذۡهَبَ عَنَّا ٱلۡحَزَنَۖ إِنَّ رَبَّنَا لَغَفُورٞ شَكُورٌ
34. ይላሉም «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከእኛ ላይ ሐዘንን ላስወገደልን ይገባው። ጌታችን በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ٱلَّذِيٓ أَحَلَّنَا دَارَ ٱلۡمُقَامَةِ مِن فَضۡلِهِۦ لَا يَمَسُّنَا فِيهَا نَصَبٞ وَلَا يَمَسُّنَا فِيهَا لُغُوبٞ
35. እርሱም ያ ከችሮታው የዘላለም መኖሪያን አገር ያሰፈረን ነው:: በእርሷም ውስጥ መከራ አይነካንም:: በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካንም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ نَارُ جَهَنَّمَ لَا يُقۡضَىٰ عَلَيۡهِمۡ فَيَمُوتُواْ وَلَا يُخَفَّفُ عَنۡهُم مِّنۡ عَذَابِهَاۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي كُلَّ كَفُورٖ
36. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ የገሀነም እሳት አለላቸው:: ይሞቱ ዘንድም በእነርሱ ላይ ሞት አይፈረድም:: ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ ከሓዲያንን ሁሉ እንመነዳለን::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَهُمۡ يَصۡطَرِخُونَ فِيهَا رَبَّنَآ أَخۡرِجۡنَا نَعۡمَلۡ صَٰلِحًا غَيۡرَ ٱلَّذِي كُنَّا نَعۡمَلُۚ أَوَلَمۡ نُعَمِّرۡكُم مَّا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَن تَذَكَّرَ وَجَآءَكُمُ ٱلنَّذِيرُۖ فَذُوقُواْ فَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِن نَّصِيرٍ
37. እነርሱም በእርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኃይል ይጮሃሉ:: «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን እድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂዉም መጥቶላችኋል:: አስተባብላችኋልም:: ስለዚህ ቅመሱ:: ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸዉም» ይባላሉ::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
إِنَّ ٱللَّهَ عَٰلِمُ غَيۡبِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
38. አላህ የሰማያትንና የምድርን ምስጢር በእርግጥ አዋቂ ነው:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ እንኳ አዋቂ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَكُمۡ خَلَٰٓئِفَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ فَمَن كَفَرَ فَعَلَيۡهِ كُفۡرُهُۥۖ وَلَا يَزِيدُ ٱلۡكَٰفِرِينَ كُفۡرُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ إِلَّا مَقۡتٗاۖ وَلَا يَزِيدُ ٱلۡكَٰفِرِينَ كُفۡرُهُمۡ إِلَّا خَسَارٗا
39. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው:: የካደም ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ክስረትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ شُرَكَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُواْ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ لَهُمۡ شِرۡكٞ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَمۡ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ كِتَٰبٗا فَهُمۡ عَلَىٰ بَيِّنَتٖ مِّنۡهُۚ بَلۡ إِن يَعِدُ ٱلظَّٰلِمُونَ بَعۡضُهُم بَعۡضًا إِلَّا غُرُورًا
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ተጋሪዎቻችሁ አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ? ወይስ ለእነርሱ በሰማያት ውስጥ ሽርክና አላቸውን? ወይስ ለእነርሱ መፅሀፍ ሰጠናቸውና ከእርሱ በግልፅ አስረጂ ላይ ናቸውን? አይደለም በደለኞች ከፊላቸው ከፊሉን ማታለልን እንጂ አይቀጥሩም» በላቸው::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ يُمۡسِكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ أَن تَزُولَاۚ وَلَئِن زَالَتَآ إِنۡ أَمۡسَكَهُمَا مِنۡ أَحَدٖ مِّنۢ بَعۡدِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ كَانَ حَلِيمًا غَفُورٗا
41. አላህ ሰማያትንና ምድርን እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል:: ቢወገዱም ከእርሱ ሌላ አንድም የሚይዛቸው የለም:: እነሆ እርሱ ታጋሽና መሃሪ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِن جَآءَهُمۡ نَذِيرٞ لَّيَكُونُنَّ أَهۡدَىٰ مِنۡ إِحۡدَى ٱلۡأُمَمِۖ فَلَمَّا جَآءَهُمۡ نَذِيرٞ مَّا زَادَهُمۡ إِلَّا نُفُورًا
42. አስፈራሪም ቢመጣላቸው ከህዝቦች ሁሉ ከአንደኛዋ ይበልጥ የተመሩ ሊሆኑ የመሃላቸውን ዲካ አድርሰው በአላህ ማሉ:: አስፈራሪም በመጣላቸው ጊዜ መበርገግን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
ٱسۡتِكۡبَارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَكۡرَ ٱلسَّيِّيِٕۚ وَلَا يَحِيقُ ٱلۡمَكۡرُ ٱلسَّيِّئُ إِلَّا بِأَهۡلِهِۦۚ فَهَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا سُنَّتَ ٱلۡأَوَّلِينَۚ فَلَن تَجِدَ لِسُنَّتِ ٱللَّهِ تَبۡدِيلٗاۖ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّتِ ٱللَّهِ تَحۡوِيلًا
43. በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ ተንኮል መዶለትንም እንጂ አልጨመረላቸዉም:: ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም:: የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠብቃሉን? በመሆኑም ለአላህ ደንብ መለወጥን አታገኝም፤ ለአላህ ደንብም መዛወርን (መቀየር) አታገኝም።
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ وَكَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعۡجِزَهُۥ مِن شَيۡءٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَلِيمٗا قَدِيرٗا
44. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? ከእነርሱም በኃይል የበረቱ ነበሩ:: አላህም በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም:: እርሱ ሁሉን አዋቂና በሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
وَلَوۡ يُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِمَا كَسَبُواْ مَا تَرَكَ عَلَىٰ ظَهۡرِهَا مِن دَآبَّةٖ وَلَٰكِن يُؤَخِّرُهُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗىۖ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِعِبَادِهِۦ بَصِيرَۢا
45. አላህ ሰዎችን በሰሩት ኃጢአት ሁሉ ቢቀጣ ኖሮ በምድር ወለል ላይ ምንንም ተንቀሳቃሽ ባልተወ ነበር:: ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት በኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል:: አላህ በባሮቹ ሁኔታ ሁሉ ተመልካች ነውና::
ตัฟสีรต่างๆ​ ภาษาอาหรับ:
 
แปลความหมาย​ สูเราะฮ์: Fātir
สารบัญสูเราะฮ์ หมายเลข​หน้า​
 
แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - الترجمة الأمهرية - زين - สารบัญ​คำแปล

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

ปิด