Check out the new design

Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika * - Indise ng mga Salin


Salin ng mga Kahulugan Surah: Al-Baqarah   Ayah:
حَٰفِظُواْ عَلَى ٱلصَّلَوَٰتِ وَٱلصَّلَوٰةِ ٱلۡوُسۡطَىٰ وَقُومُواْ لِلَّهِ قَٰنِتِينَ
238. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሶላቶችን በተለይ መካከለኛይቱን ሶላት ወቅታቸውንና ስርዓታቸውን ጠብቃችሁ ስገዱ:: በሙሉ ታዛዥነትም ለአላህ ቁሙ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
فَإِنۡ خِفۡتُمۡ فَرِجَالًا أَوۡ رُكۡبَانٗاۖ فَإِذَآ أَمِنتُمۡ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَمَا عَلَّمَكُم مَّا لَمۡ تَكُونُواْ تَعۡلَمُونَ
239. (ሙስሊሞች ሆይ!) የደህንነት ስጋት ሲኖር በእግር እየሄዳችሁም ሆነ ተሳፍራች ስገዱ:: ሰላም ሲሰፍን በተለመደው ሥርዓት (ስገዱ።) ታውቁት ያልነበራችሁትን እንዳሳወቃችሁ ሁሉ አላህን በአግባቡ አውሱ (ስገዱ)::
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوۡنَ مِنكُمۡ وَيَذَرُونَ أَزۡوَٰجٗا وَصِيَّةٗ لِّأَزۡوَٰجِهِم مَّتَٰعًا إِلَى ٱلۡحَوۡلِ غَيۡرَ إِخۡرَاجٖۚ فَإِنۡ خَرَجۡنَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِي مَا فَعَلۡنَ فِيٓ أَنفُسِهِنَّ مِن مَّعۡرُوفٖۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
240. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ ሚስቶችን ትተው የሚሞቱ ሁሉ ለሚስቶቻቸው ከየቤቶቻቸው የማይወጡ ሆነው ሳለ ዓመት ድረስ ወጫቸው እንዲሸፈን መናዘዝ ይኖርባቸዋል:: ሚስቶች በፈቃዳቸው ከቤት ቢወጡ ግን ደንብ ጠብቀውና ኃላፊነትን ወስደው በሰሩት ጉዳይ ላይ በሟች ዘመዶች ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَلِلۡمُطَلَّقَٰتِ مَتَٰعُۢ بِٱلۡمَعۡرُوفِۖ حَقًّا عَلَى ٱلۡمُتَّقِينَ
241. ለተፈቱ ሴቶች ሁሉ በፈችው ባል ችሎታ መጠን ዳረጎት (የገንዘብ ድጎማ) ይሰጣቸዋል:: ይህ አላህን በሚፈሩ ሰዎች ሁሉ ላይ ተደንግጓል::
Ang mga Tafsir na Arabe:
كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
242. ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ ያብራራላችኋል::
Ang mga Tafsir na Arabe:
۞ أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ خَرَجُواْ مِن دِيَٰرِهِمۡ وَهُمۡ أُلُوفٌ حَذَرَ ٱلۡمَوۡتِ فَقَالَ لَهُمُ ٱللَّهُ مُوتُواْ ثُمَّ أَحۡيَٰهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشۡكُرُونَ
243. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብዙ ሺህ ሆነው ሞትን በመፍራት ከሀገሮቻቸው የወጡ ሰዎችን ታሪክ አላየህምን (አላወክምን?) አላህ ለእነርሱ «ሙቱ» አላቸው:: ሞቱም:: ከዚያ እንደገና ነፍስ ዘራባቸው:: አላህም ለሰዎች እጅግ ቸር ነው:: ይሁንና አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَقَٰتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
244. (ሙስሊሞች ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ተጋደሉ:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ መሆኑንም እወቁ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
مَّن ذَا ٱلَّذِي يُقۡرِضُ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥٓ أَضۡعَافٗا كَثِيرَةٗۚ وَٱللَّهُ يَقۡبِضُ وَيَبۡصُۜطُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
245. ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና አላህም ብዙ እጥፍ ድርብ አድርጎ እንዲከፍለው የሚሻ ማን ነው? አላህ ለፈለገው ሰው ሲሳዩን ያጠብበታል፤ ለፈለገው ደግሞ ያሰፋለታልም:: ወደ እርሱ ብቻ ትመለሳላችሁ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
 
Salin ng mga Kahulugan Surah: Al-Baqarah
Indise ng mga Surah Numero ng Pahina
 
Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika - Indise ng mga Salin

Isinalin ni Muhammad Zain Zahr Al-Din. Inilabas ng Akademya ng Aprika.

Isara