Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - الترجمة الأمهرية - زين * - Indise ng mga Salin


Salin ng mga Kahulugan Surah: Nūh   Ayah:

ሱረቱ ኑህ

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ أَنۡ أَنذِرۡ قَوۡمَكَ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
1. እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው::
Ang mga Tafsir na Arabe:
قَالَ يَٰقَوۡمِ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ
2. እርሱም አለ፡- «ሀዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) ገላጭ የሆንኩ አስጠንቃቂ ነኝ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ
3. «አላህን ተገዙት፡-ፍሩት፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
يَغۡفِرۡ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمۡ وَيُؤَخِّرۡكُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّىۚ إِنَّ أَجَلَ ٱللَّهِ إِذَا جَآءَ لَا يُؤَخَّرُۚ لَوۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
4. «ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል:: አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይቆይም:: በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ በታዘዛችሁ ነበር።»
Ang mga Tafsir na Arabe:
قَالَ رَبِّ إِنِّي دَعَوۡتُ قَوۡمِي لَيۡلٗا وَنَهَارٗا
5. ስለተቃወሙትም «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
فَلَمۡ يَزِدۡهُمۡ دُعَآءِيٓ إِلَّا فِرَارٗا
6. «ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَإِنِّي كُلَّمَا دَعَوۡتُهُمۡ لِتَغۡفِرَ لَهُمۡ جَعَلُوٓاْ أَصَٰبِعَهُمۡ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَٱسۡتَغۡشَوۡاْ ثِيَابَهُمۡ وَأَصَرُّواْ وَٱسۡتَكۡبَرُواْ ٱسۡتِكۡبَارٗا
7. «እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ:: ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ:: በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም:: ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
ثُمَّ إِنِّي دَعَوۡتُهُمۡ جِهَارٗا
8. «ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው።
Ang mga Tafsir na Arabe:
ثُمَّ إِنِّيٓ أَعۡلَنتُ لَهُمۡ وَأَسۡرَرۡتُ لَهُمۡ إِسۡرَارٗا
9. «ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ:: ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
فَقُلۡتُ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ إِنَّهُۥ كَانَ غَفَّارٗا
10. «እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: እርሱም በጣም መሀሪ ነውና።
Ang mga Tafsir na Arabe:
يُرۡسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡكُم مِّدۡرَارٗا
11. «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል።
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَيُمۡدِدۡكُم بِأَمۡوَٰلٖ وَبَنِينَ وَيَجۡعَل لَّكُمۡ جَنَّٰتٖ وَيَجۡعَل لَّكُمۡ أَنۡهَٰرٗا
12. «ገንዘቦችና ልጆችንም ይለግሳችኋል:: ለእናንተ አትክልቶችን ያደርግላችኋል:: ለእናተም ወንዞችን ያደርግላችኋል አልኳቸው።»
Ang mga Tafsir na Arabe:
مَّا لَكُمۡ لَا تَرۡجُونَ لِلَّهِ وَقَارٗا
13. ለአላህ ተገቢውን ልቅና የማትሰጡበት ምክንያት ለእናንተ ምን አላችሁ?
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَقَدۡ خَلَقَكُمۡ أَطۡوَارًا
14. በልዩ ልዩ (በተለያዩ) እርከኖች (ሁኔታዎች) በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲሆን::
Ang mga Tafsir na Arabe:
أَلَمۡ تَرَوۡاْ كَيۡفَ خَلَقَ ٱللَّهُ سَبۡعَ سَمَٰوَٰتٖ طِبَاقٗا
15. አላህ ሰባት ሰማያትን አንዱ በአንዱ ላይ የተነባበረ ሲሆን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَجَعَلَ ٱلۡقَمَرَ فِيهِنَّ نُورٗا وَجَعَلَ ٱلشَّمۡسَ سِرَاجٗا
16. በውስጣቸዉም ጨረቃን አብሪ አደረገ:: ጸሐይንም ብርሃን አደረገ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَٱللَّهُ أَنۢبَتَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ نَبَاتٗا
17. አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
ثُمَّ يُعِيدُكُمۡ فِيهَا وَيُخۡرِجُكُمۡ إِخۡرَاجٗا
18. ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል:: ማውጣትንም ያወጣችኋል::
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ بِسَاطٗا
19. አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት።
Ang mga Tafsir na Arabe:
لِّتَسۡلُكُواْ مِنۡهَا سُبُلٗا فِجَاجٗا
20. ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ::
Ang mga Tafsir na Arabe:
قَالَ نُوحٞ رَّبِّ إِنَّهُمۡ عَصَوۡنِي وَٱتَّبَعُواْ مَن لَّمۡ يَزِدۡهُ مَالُهُۥ وَوَلَدُهُۥٓ إِلَّا خَسَارٗا
21. ኑሕም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! እነርሱም አመጹብኝ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَمَكَرُواْ مَكۡرٗا كُبَّارٗا
22. «ከባድንም ተንኮል ያሴሩትን ሰዎች ተከተሉ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَقَالُواْ لَا تَذَرُنَّ ءَالِهَتَكُمۡ وَلَا تَذَرُنَّ وَدّٗا وَلَا سُوَاعٗا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسۡرٗا
23. መሪዎችም አሉ፡- <አማልክቶቻችሁን፤ ወድንም፤ ሰዋዕንም፤ የጉስንም፤ የዑቅንና ነስርንም አትተው።>
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَقَدۡ أَضَلُّواْ كَثِيرٗاۖ وَلَا تَزِدِ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا ضَلَٰلٗا
24. «በእርግጥ (እነዚህ መሪዎች ወይም ጣኦቶች) ብዙዎችን ሰዎች አሳሳቱ:: ከሓዲያንንም ጥመትን እንጂ ሌላን አትጨምርላቸው» አለ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
مِّمَّا خَطِيٓـَٰٔتِهِمۡ أُغۡرِقُواْ فَأُدۡخِلُواْ نَارٗا فَلَمۡ يَجِدُواْ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَنصَارٗا
25. በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ተሰመጡ:: እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ:: ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሆኑ ረዳቶችን አላገኙም::
Ang mga Tafsir na Arabe:
وَقَالَ نُوحٞ رَّبِّ لَا تَذَرۡ عَلَى ٱلۡأَرۡضِ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ دَيَّارًا
26. ኑህም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ከከሓዲያን በምድር ላይ (በዓለም ላይ) የሚኖርን አንድንም አትተው።
Ang mga Tafsir na Arabe:
إِنَّكَ إِن تَذَرۡهُمۡ يُضِلُّواْ عِبَادَكَ وَلَا يَلِدُوٓاْ إِلَّا فَاجِرٗا كَفَّارٗا
27. «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና:: ኃጢአተኛ ከሓዲንም እንጂ ሌላን አይወልዱም።
Ang mga Tafsir na Arabe:
رَّبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيَّ وَلِمَن دَخَلَ بَيۡتِيَ مُؤۡمِنٗا وَلِلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۖ وَلَا تَزِدِ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا تَبَارَۢا
28. «ጌታየ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ትክክለኛ አማኝ ሆኖ በቤቴ ለገባ ሁሉ ለአማኞችና ለምዕመናትም ምህረት አድርግ:: ከሓዲያንንም ከጥፋት በስተቀር አትጨምርላቸው።» አለ።
Ang mga Tafsir na Arabe:
 
Salin ng mga Kahulugan Surah: Nūh
Indise ng mga Surah Numero ng Pahina
 
Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - الترجمة الأمهرية - زين - Indise ng mga Salin

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

Isara