Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: حج   آیت:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ وَأَنَّهُۥ يُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَأَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
6. ይህ ሁሉ አላህ ፍፁም እውነት፤ እርሱም ሙታንን ህያው የሚያደርግ፤ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።
عربی تفاسیر:
وَأَنَّ ٱلسَّاعَةَ ءَاتِيَةٞ لَّا رَيۡبَ فِيهَا وَأَنَّ ٱللَّهَ يَبۡعَثُ مَن فِي ٱلۡقُبُورِ
7. የሰዓቲቱም መከሰት ፈጽሞ ጥርጣሬ የሌለበት በመሆኑና አላህ በመቃብሮች ውስጥ ያለን ሁሉ የሚቀሰቅስ በመሆኑም ነው።
عربی تفاسیر:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِي ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَلَا هُدٗى وَلَا كِتَٰبٖ مُّنِيرٖ
8. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት ያለ አንዳች ማስረጃም ያለ አብራሪ መጽሐፍም ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ::
عربی تفاسیر:
ثَانِيَ عِطۡفِهِۦ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۖ لَهُۥ فِي ٱلدُّنۡيَا خِزۡيٞۖ وَنُذِيقُهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ
9. ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት (ይከራከራል)። በቅርቢቱ ዓለም ለርሱ ውርደት አለው:: በትንሳኤ ቀንም አቃጣይን (የእሳት) ቅጣት እናቀምሰዋለን::
عربی تفاسیر:
ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ يَدَاكَ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ
10. «ይህ እጆችህ ባስቀደሙት ኃጢአት ነው፣ አላህም ለባሮቹ ፈጽሞ በዳይ አይደለም።» (ይባላል።)
عربی تفاسیر:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَعۡبُدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ حَرۡفٖۖ فَإِنۡ أَصَابَهُۥ خَيۡرٌ ٱطۡمَأَنَّ بِهِۦۖ وَإِنۡ أَصَابَتۡهُ فِتۡنَةٌ ٱنقَلَبَ عَلَىٰ وَجۡهِهِۦ خَسِرَ ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةَۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِينُ
11. ከሰዎችም መካከል በሃይማኖት ጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አለ:: እናም መልካም ነገር ካገኘው በእምነቱ ላይ ይረጋል:: መከራ ካገኘው ግን በፊቱ ላይ ይገለበጣል (ይክዳል):: ይህ አይነቱ ሰው የቅርቢቱን ዓለምም ሆነ የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ:: ይህ ነው ግልጽ ኪሳራ ማለት።
عربی تفاسیر:
يَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُۥ وَمَا لَا يَنفَعُهُۥۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلضَّلَٰلُ ٱلۡبَعِيدُ
12. ከአላህ ሌላ የማይጎዳውንና የማይጠቅመውን ይገዛል:: ይህ እርሱ ከእውነት የራቀ ስህተት ነው::
عربی تفاسیر:
يَدۡعُواْ لَمَن ضَرُّهُۥٓ أَقۡرَبُ مِن نَّفۡعِهِۦۚ لَبِئۡسَ ٱلۡمَوۡلَىٰ وَلَبِئۡسَ ٱلۡعَشِيرُ
13. ያንን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ወደ እሱ የሚቀርብን ይገዛል:: ረዳቱ ምንኛ ከፋ! ወዳጁም ምንኛ ከፋ!
عربی تفاسیر:
إِنَّ ٱللَّهَ يُدۡخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَفۡعَلُ مَا يُرِيدُ
14. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባቸዋል:: አላህም የሚሻውን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይሰራልና።
عربی تفاسیر:
مَن كَانَ يَظُنُّ أَن لَّن يَنصُرَهُ ٱللَّهُ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ فَلۡيَمۡدُدۡ بِسَبَبٍ إِلَى ٱلسَّمَآءِ ثُمَّ لۡيَقۡطَعۡ فَلۡيَنظُرۡ هَلۡ يُذۡهِبَنَّ كَيۡدُهُۥ مَا يَغِيظُ
15. አላህ (መልዕክተኛውን) ሙሐመድን በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አይረዳዉም ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ገመድን ወደ ሰማይ ይዘርጋና ከዚያ (ትንፋሹ እስኪቆረጥ) ይታነቅ:: ይህ ተግባሩ ተንኮሉ የሚያስቆጨውን ነገር ያስወግደለት እንደሆነም ይመልከት።
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: حج
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں