Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

معانی کا ترجمہ سورت: حج   آیت:
وَيَسۡتَعۡجِلُونَكَ بِٱلۡعَذَابِ وَلَن يُخۡلِفَ ٱللَّهُ وَعۡدَهُۥۚ وَإِنَّ يَوۡمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلۡفِ سَنَةٖ مِّمَّا تَعُدُّونَ
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን ቅጣትን እንድታመጣ ያቻኩሉሃል (ያጣድፉሃል):: በጌታህ ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት የሚመጥን ነው::
عربی تفاسیر:
وَكَأَيِّن مِّن قَرۡيَةٍ أَمۡلَيۡتُ لَهَا وَهِيَ ظَالِمَةٞ ثُمَّ أَخَذۡتُهَا وَإِلَيَّ ٱلۡمَصِيرُ
48. ከከተማ በዳይ ሆና ጊዜ የሰጠኋትና ከዚያ የያዝኳት የቀጣኋት ብዙ ናት:: የመጨረሻው መመለሻም ወደ እኔ ብቻ ነው::
عربی تفاسیر:
قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَآ أَنَا۠ لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٞ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው።
عربی تفاسیر:
فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ
50. እነዚያም በትክክል ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ለእነርሱ ምህረትና ያማረ ሲሳይ አላቸው::
عربی تفاسیر:
وَٱلَّذِينَ سَعَوۡاْ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَحِيمِ
51. እነዚያ ከአላህ የሚያመልጡ መስሏቸው ተዓምራታችንን በመንቀፍ የተጉ ሁሉ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።
عربی تفاسیر:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رَّسُولٖ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلۡقَى ٱلشَّيۡطَٰنُ فِيٓ أُمۡنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلۡقِي ٱلشَّيۡطَٰنُ ثُمَّ يُحۡكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት አንድንም መልዕክተኛ ወይም ነብይ አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ የማጥመሚያን ሀሳብ የሚጥል ቢሆን እንጂ:: ወዲያዉም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ማጥመሚያ ቃል ያስወግዳል:: ከዚያም አላህ አናቅጽን ያጠነክራል (ያጸናል):: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
عربی تفاسیر:
لِّيَجۡعَلَ مَا يُلۡقِي ٱلشَّيۡطَٰنُ فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمۡۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَفِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ
53. ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸውና ልቦቻቸው ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል:: በዳዮችም ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ (ውዝግብ) ውስጥ ናቸው::
عربی تفاسیر:
وَلِيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَيُؤۡمِنُواْ بِهِۦ فَتُخۡبِتَ لَهُۥ قُلُوبُهُمۡۗ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهَادِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
54. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት እርሱ (ቁርኣን) ከጌታህ የሆነ እውነት መሆኑን እንዲያውቁና በእርሱ እንዲያምኑ ልቦቻቸዉም በእርሱ እንዲረኩ (ያጠነክራል):: አላህም እነዚያን በትክክል ያመኑትን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው::
عربی تفاسیر:
وَلَا يَزَالُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي مِرۡيَةٖ مِّنۡهُ حَتَّىٰ تَأۡتِيَهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغۡتَةً أَوۡ يَأۡتِيَهُمۡ عَذَابُ يَوۡمٍ عَقِيمٍ
55. እነዚያ የካዱት ሰዎች ሰዓቲቱ በድንገት እስከምትመጣባቸው ወይም ከደግ ነገር መካን የሆነው ቀን ቅጣት እስከሚመጣባቸው ድረስ በቁርኣን ጉዳይ ከመጠራጠር አያቆሙም::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: حج
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں