Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: فُصّلت   آیت:

ፉሲለት

حمٓ
1. ሓ፤ ሚይም፤
عربی تفاسیر:
تَنزِيلٞ مِّنَ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
2. ይህ ቁርኣን እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ከሆነው ጌታ ከአላህ የተወረደ ነው::
عربی تفاسیر:
كِتَٰبٞ فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥ قُرۡءَانًا عَرَبِيّٗا لِّقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
3. አናቅጾቹ የተብራሩ የሆነ መጽሐፍ ነው:: ዐረበኛ ቁርኣን ሲሆን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው::
عربی تفاسیر:
بَشِيرٗا وَنَذِيرٗا فَأَعۡرَضَ أَكۡثَرُهُمۡ فَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ
4. አብሳሪና አስፈራሪ ሲሆን ተወረደ። አብዛኞቻቸዉም ተውት:: እነርሱም አይሰሙም::
عربی تفاسیر:
وَقَالُواْ قُلُوبُنَا فِيٓ أَكِنَّةٖ مِّمَّا تَدۡعُونَآ إِلَيۡهِ وَفِيٓ ءَاذَانِنَا وَقۡرٞ وَمِنۢ بَيۡنِنَا وَبَيۡنِكَ حِجَابٞ فَٱعۡمَلۡ إِنَّنَا عَٰمِلُونَ
5. አሉም፡- «ልቦቻችን ከዚያ ወደርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው:: በጆሮቻችንም ላይ ድንቁርና አለ:: በእኛና በአንተ መካከል ግርዶሽ አለ:: በሃይማኖትህ ስራ እኛም ሰሪዎች ነንና::»
عربی تفاسیر:
قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ فَٱسۡتَقِيمُوٓاْ إِلَيۡهِ وَٱسۡتَغۡفِرُوهُۗ وَوَيۡلٞ لِّلۡمُشۡرِكِينَ
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ቀጥ በሉ:: ምህረትንም ለምኑት በማለት ወደ እኔ ይወርድልኛል እንጂ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ።» ለአጋሪዎችም ወዮላቸው።
عربی تفاسیر:
ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ كَٰفِرُونَ
7. ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲያን ለሆኑት (ወዮላቸው)::
عربی تفاسیر:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونٖ
8. እነዚያ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው::
عربی تفاسیر:
۞ قُلۡ أَئِنَّكُمۡ لَتَكۡفُرُونَ بِٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَرۡضَ فِي يَوۡمَيۡنِ وَتَجۡعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادٗاۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !) «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባላንጣዎች ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሰራው) የዓለማቱ ጌታ ነው።» በላቸው::
عربی تفاسیر:
وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِيَ مِن فَوۡقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقۡوَٰتَهَا فِيٓ أَرۡبَعَةِ أَيَّامٖ سَوَآءٗ لِّلسَّآئِلِينَ
10. በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ:: በእርሷም በረከትን አደረገ:: በውስጧም ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆን ወሰነ::
عربی تفاسیر:
ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِيَ دُخَانٞ فَقَالَ لَهَا وَلِلۡأَرۡضِ ٱئۡتِيَا طَوۡعًا أَوۡ كَرۡهٗا قَالَتَآ أَتَيۡنَا طَآئِعِينَ
11. ከዚያም እርሷ ጭስ ሆና ሳለች ወደ ሰማይ አሰበ:: ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ኑ» አላቸው:: «ታዛዦች ሆነን መጣን» አሉ::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: فُصّلت
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں