Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: فُصّلت   آیت:
فَقَضَىٰهُنَّ سَبۡعَ سَمَٰوَاتٖ فِي يَوۡمَيۡنِ وَأَوۡحَىٰ فِي كُلِّ سَمَآءٍ أَمۡرَهَاۚ وَزَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِمَصَٰبِيحَ وَحِفۡظٗاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ
12. በሁለት ቀናትም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: በሰማያትም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ:: ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን:: ከሰይጣናት መጠበቅንም ጠበቅናት:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው ጌታ ውሳኔ ነው::
عربی تفاسیر:
فَإِنۡ أَعۡرَضُواْ فَقُلۡ أَنذَرۡتُكُمۡ صَٰعِقَةٗ مِّثۡلَ صَٰعِقَةِ عَادٖ وَثَمُودَ
13. ከእምነት እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የሆነን መቅሰፍት አስጠነቅቄያችኋለሁ።»
عربی تفاسیر:
إِذۡ جَآءَتۡهُمُ ٱلرُّسُلُ مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ قَالُواْ لَوۡ شَآءَ رَبُّنَا لَأَنزَلَ مَلَٰٓئِكَةٗ فَإِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ
14. መልዕክተኞቹ «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ» በማለት ከስተፊታቸዉም ከበስተኋላቸዉም በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላዕክትን ባወረደ ነበር:: ስለዚህ እኛ በዚህ በእርሱ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» አሉ።
عربی تفاسیر:
فَأَمَّا عَادٞ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَقَالُواْ مَنۡ أَشَدُّ مِنَّا قُوَّةًۖ أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَهُمۡ هُوَ أَشَدُّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗۖ وَكَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَجۡحَدُونَ
15. የዓድም ነገዶችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፤ ከእኛ ይበልጥ በኃይል ብርቱ ማን ነው ? አሉም ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኃይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መሆኑን አያምኑምን? በታዐምራታችንም ይክዱ ነበሩ::
عربی تفاسیر:
فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا صَرۡصَرٗا فِيٓ أَيَّامٖ نَّحِسَاتٖ لِّنُذِيقَهُمۡ عَذَابَ ٱلۡخِزۡيِ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَخۡزَىٰۖ وَهُمۡ لَا يُنصَرُونَ
16. በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸዉም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻ ብርቱ ነፋስ መናጢዎች በሆኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው:: እነርሱም አይረዱም::
عربی تفاسیر:
وَأَمَّا ثَمُودُ فَهَدَيۡنَٰهُمۡ فَٱسۡتَحَبُّواْ ٱلۡعَمَىٰ عَلَى ٱلۡهُدَىٰ فَأَخَذَتۡهُمۡ صَٰعِقَةُ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡهُونِ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
17. ሰሙዶችማ ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: እነርሱ ግን እውርነትን ከቅንነት ይልቅ መረጡ:: ይሰሩትም በነበሩት ኃጢአት አዋራጅ የሆነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው::
عربی تفاسیر:
وَنَجَّيۡنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ
18. እነዚያንም ያመኑትንና ይጠነቀቁ የነበሩትንም አዳንናቸው::
عربی تفاسیر:
وَيَوۡمَ يُحۡشَرُ أَعۡدَآءُ ٱللَّهِ إِلَى ٱلنَّارِ فَهُمۡ يُوزَعُونَ
19. የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውሱ:: የሚከመከሙ ሆነውም ይነዳሉ።
عربی تفاسیر:
حَتَّىٰٓ إِذَا مَا جَآءُوهَا شَهِدَ عَلَيۡهِمۡ سَمۡعُهُمۡ وَأَبۡصَٰرُهُمۡ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
20. በመጧትም ጊዜ ጀሮዎቻቸው፤ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸዉም ይሰሩት በነበረ ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: فُصّلت
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں