Check out the new design

Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格 * - Mục lục các bản dịch

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Ý nghĩa nội dung Chương: Al-Nur   Câu:
وَأَنكِحُواْ ٱلۡأَيَٰمَىٰ مِنكُمۡ وَٱلصَّٰلِحِينَ مِنۡ عِبَادِكُمۡ وَإِمَآئِكُمۡۚ إِن يَكُونُواْ فُقَرَآءَ يُغۡنِهِمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦۗ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٞ
ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلۡيَسۡتَعۡفِفِ ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ نِكَاحًا حَتَّىٰ يُغۡنِيَهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦۗ وَٱلَّذِينَ يَبۡتَغُونَ ٱلۡكِتَٰبَ مِمَّا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡ فَكَاتِبُوهُمۡ إِنۡ عَلِمۡتُمۡ فِيهِمۡ خَيۡرٗاۖ وَءَاتُوهُم مِّن مَّالِ ٱللَّهِ ٱلَّذِيٓ ءَاتَىٰكُمۡۚ وَلَا تُكۡرِهُواْ فَتَيَٰتِكُمۡ عَلَى ٱلۡبِغَآءِ إِنۡ أَرَدۡنَ تَحَصُّنٗا لِّتَبۡتَغُواْ عَرَضَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَمَن يُكۡرِههُّنَّ فَإِنَّ ٱللَّهَ مِنۢ بَعۡدِ إِكۡرَٰهِهِنَّ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠበቁ፡፡ እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች (ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት) መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነሱ መልካምን ነገር ብታውቁ ተጻጻፉዋቸው፡፡ ከአላህም ገንዘብ ከዚያ ከሰጣችሁ ስጧቸው፡፡ ሴቶች ባሮቻችሁንም መጥጠበቅን ቢፈልጉ የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ላይ አታስገድዱዋቸው፡፡ የሚያስገድዳቸውም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ (ለተገደዱት) መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكُمۡ ءَايَٰتٖ مُّبَيِّنَٰتٖ وَمَثَلٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلِكُمۡ وَمَوۡعِظَةٗ لِّلۡمُتَّقِينَ
ወደእናንተ አብራሪ የኾኑን አንቀጾች ከእነዚያ ከበፊታችሁ ካለፉትም (ምሳሌዎች ዓይነት) ምሳሌን ለጥንቁቆቹ መገሰጫንም በእርግጥ አወረድን፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ ٱللَّهُ نُورُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ مَثَلُ نُورِهِۦ كَمِشۡكَوٰةٖ فِيهَا مِصۡبَاحٌۖ ٱلۡمِصۡبَاحُ فِي زُجَاجَةٍۖ ٱلزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوۡكَبٞ دُرِّيّٞ يُوقَدُ مِن شَجَرَةٖ مُّبَٰرَكَةٖ زَيۡتُونَةٖ لَّا شَرۡقِيَّةٖ وَلَا غَرۡبِيَّةٖ يَكَادُ زَيۡتُهَا يُضِيٓءُ وَلَوۡ لَمۡ تَمۡسَسۡهُ نَارٞۚ نُّورٌ عَلَىٰ نُورٖۚ يَهۡدِي ٱللَّهُ لِنُورِهِۦ مَن يَشَآءُۚ وَيَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَٰلَ لِلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ
አላህ የሰማያትና የምድር ብርሃን (አብሪ) ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት (ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች፤ ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው፡፡ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فِي بُيُوتٍ أَذِنَ ٱللَّهُ أَن تُرۡفَعَ وَيُذۡكَرَ فِيهَا ٱسۡمُهُۥ يُسَبِّحُ لَهُۥ فِيهَا بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡأٓصَالِ
አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)፡፡ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Al-Nur
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格 - Mục lục các bản dịch

谢赫·穆罕默德·萨迪格和穆罕默德二·哈比布翻译,在由先锋翻译中心的监督下完成,并可查阅原始译文,以便提出意见、评估和持续改进。

Đóng lại