Check out the new design

Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - Bản dịch tiếng Amharic - Học viện Châu Phi * - Mục lục các bản dịch

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Ý nghĩa nội dung Chương: Hud   Câu:
قَالَتۡ يَٰوَيۡلَتَىٰٓ ءَأَلِدُ وَأَنَا۠ عَجُوزٞ وَهَٰذَا بَعۡلِي شَيۡخًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عَجِيبٞ
72. እርሷም «ዋልኝ እኔ አሮጊት ይህም ባለቤቴ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው።» አለች።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُوٓاْ أَتَعۡجَبِينَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِۖ رَحۡمَتُ ٱللَّهِ وَبَرَكَٰتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ أَهۡلَ ٱلۡبَيۡتِۚ إِنَّهُۥ حَمِيدٞ مَّجِيدٞ
73. «በአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን? :: የአላህ እዝነትና በረከት በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን:: እሱ ምስጉንና ለጋሽ ነውና።» አሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَلَمَّا ذَهَبَ عَنۡ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلرَّوۡعُ وَجَآءَتۡهُ ٱلۡبُشۡرَىٰ يُجَٰدِلُنَا فِي قَوۡمِ لُوطٍ
74. ከኢብራሂም ፍራቻው በሄደለትና ብስራት በመጣችለት ጊዜ በሉጥ ህዝቦች ነገር ይከራከረን ጀመር::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّٰهٞ مُّنِيبٞ
75. ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ፤ አልቃሻ (እጅግ የሚማፀን) እና መላሳ ነውና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَآۖ إِنَّهُۥ قَدۡ جَآءَ أَمۡرُ رَبِّكَۖ وَإِنَّهُمۡ ءَاتِيهِمۡ عَذَابٌ غَيۡرُ مَرۡدُودٖ
76. (እነርሱም አሉት): «ኢብራሂም ሆይ! ይህን ክርክር ተው:: እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል:: እነርሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَمَّا جَآءَتۡ رُسُلُنَا لُوطٗا سِيٓءَ بِهِمۡ وَضَاقَ بِهِمۡ ذَرۡعٗا وَقَالَ هَٰذَا يَوۡمٌ عَصِيبٞ
77. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ:: ልቡም በእነርሱ ተጨነቀ:: «ይህ ብርቱ ቀን ነዉ።» አለም።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَجَآءَهُۥ قَوۡمُهُۥ يُهۡرَعُونَ إِلَيۡهِ وَمِن قَبۡلُ كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِي هُنَّ أَطۡهَرُ لَكُمۡۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُخۡزُونِ فِي ضَيۡفِيٓۖ أَلَيۡسَ مِنكُمۡ رَجُلٞ رَّشِيدٞ
78. ህዝቦቹም ወደ እርሱ እየተጣደፉ መጡና ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር:: «ህዝቦቼ ሆይ! እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው:: ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው:: አግቧቸው እናም አላህን ፍሩ:: በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ አንድ ቅን ሰው እንኳን የለምን?» አላቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا لَنَا فِي بَنَاتِكَ مِنۡ حَقّٖ وَإِنَّكَ لَتَعۡلَمُ مَا نُرِيدُ
79. «ከሴቶች ልጆችህ እኛ ምንም ጉዳይ የሌለን መሆኑን በትክክል ታውቃለህ:: አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ።» አሉት።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالَ لَوۡ أَنَّ لِي بِكُمۡ قُوَّةً أَوۡ ءَاوِيٓ إِلَىٰ رُكۡنٖ شَدِيدٖ
80. «በእናንተ ላይ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)።» አላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ يَٰلُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوٓاْ إِلَيۡكَۖ فَأَسۡرِ بِأَهۡلِكَ بِقِطۡعٖ مِّنَ ٱلَّيۡلِ وَلَا يَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدٌ إِلَّا ٱمۡرَأَتَكَۖ إِنَّهُۥ مُصِيبُهَا مَآ أَصَابَهُمۡۚ إِنَّ مَوۡعِدَهُمُ ٱلصُّبۡحُۚ أَلَيۡسَ ٱلصُّبۡحُ بِقَرِيبٖ
81. «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነን:: ህዝቦች ወደ አንተ በክፉ አይደርሱብህም:: ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሂድ:: ከናንተም አንድም ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እነሆ እርሷንማ እነርሱን የሚያገኛቸው ስቃይ ሁሉ ያገኛታልና:: ቀጠሯቸው ንጋቱ ላይ ነው:: ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» አሉት።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Hud
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - Bản dịch tiếng Amharic - Học viện Châu Phi - Mục lục các bản dịch

Người dịch Muhammad Zain Zuher Al-Din, do Học viện Châu Phi phát hành.

Đóng lại