Check out the new design

Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院 * - Mục lục các bản dịch


Ý nghĩa nội dung Chương: Al-Baqarah   Câu:
۞ مَا نَنسَخۡ مِنۡ ءَايَةٍ أَوۡ نُنسِهَا نَأۡتِ بِخَيۡرٖ مِّنۡهَآ أَوۡ مِثۡلِهَآۗ أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አናቅጽ መካከል አንዱን እንኳን ብንሽር ወይም እርሱን ብናስረሳህ ከእርሱ የሚበልጥ ወይም ተመሳሳዩን እናመጣለን:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑን አላወቅክምን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٍ
107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ መሆኑን እና ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት እንደሌላችሁ አላወቅክምን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَمۡ تُرِيدُونَ أَن تَسۡـَٔلُواْ رَسُولَكُمۡ كَمَا سُئِلَ مُوسَىٰ مِن قَبۡلُۗ وَمَن يَتَبَدَّلِ ٱلۡكُفۡرَ بِٱلۡإِيمَٰنِ فَقَدۡ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ
108. (ሰዎች ሆይ!) ከአሁን በፊት (ነብዩ) ሙሳ እንደተጠየቀው ዓይነት መልዕክተኛችሁን (ሙሐመድን) ልትጠይቁ ትፈልጋላችሁን? በእምነት ክህደትን የሚለውጥ ሁሉ በእርግጥ ትክክለኛውን መንገድ ስቷል፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَدَّ كَثِيرٞ مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَوۡ يَرُدُّونَكُم مِّنۢ بَعۡدِ إِيمَٰنِكُمۡ كُفَّارًا حَسَدٗا مِّنۡ عِندِ أَنفُسِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلۡحَقُّۖ فَٱعۡفُواْ وَٱصۡفَحُواْ حَتَّىٰ يَأۡتِيَ ٱللَّهُ بِأَمۡرِهِۦٓۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
109. ከመጽሐፍ ባለቤቶች መካከል ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነው ምቀኝነት በመገፋፋት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲያን ሊያደርጓችሁ ተመኙ:: እናም አላህ ትዕዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ይቅርታ አድርጉ:: እለፏቸዉም:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَۚ وَمَا تُقَدِّمُواْ لِأَنفُسِكُم مِّنۡ خَيۡرٖ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
110. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢዎች ስጡ:: ለነፍሶቻችሁም የምታስቀድሙትን በጎ ስራ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَقَالُواْ لَن يَدۡخُلَ ٱلۡجَنَّةَ إِلَّا مَن كَانَ هُودًا أَوۡ نَصَٰرَىٰۗ تِلۡكَ أَمَانِيُّهُمۡۗ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
111. «ገነትን አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች የሆነ እንጂ ሌላ አይገባትም።» አሉ:: «ይህች ከንቱ ምኞታቸው ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ማስረጃችሁን አምጡ።» በላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
بَلَىٰۚ مَنۡ أَسۡلَمَ وَجۡهَهُۥ لِلَّهِ وَهُوَ مُحۡسِنٞ فَلَهُۥٓ أَجۡرُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦ وَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
112. ጉዳዩ እንደመሰላቸው አይደለም:: ይልቁንም በጎ ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ የሰጠ ሁሉ ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው:: በእነርሱ ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Al-Baqarah
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院 - Mục lục các bản dịch

穆罕默德·宰尼·泽海伦丁,由非洲学院发行

Đóng lại