Check out the new design

Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院 * - Mục lục các bản dịch


Ý nghĩa nội dung Chương: Al-Furqan   Câu:
إِذَا رَأَتۡهُم مِّن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ سَمِعُواْ لَهَا تَغَيُّظٗا وَزَفِيرٗا
12. ከሩቅ ስፍራ ባየቻቸው ጊዜ የእርሷን የቁጭት መገንፈልንና ማናፋትን ይሰማሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَإِذَآ أُلۡقُواْ مِنۡهَا مَكَانٗا ضَيِّقٗا مُّقَرَّنِينَ دَعَوۡاْ هُنَالِكَ ثُبُورٗا
13. ከጓደኞቻቸው ጋር (ከሰይጣኖቻቸው ጋር) በአንድ የታሰሩ ሆነዉም ከእርሷ በጠባብ ስፍራ በተጣሉ ጊዜ በዚያ ስፍራ ጥፋትን ይጠራሉ:: (ዋ ጥፋታችን! ይላሉ)።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَّا تَدۡعُواْ ٱلۡيَوۡمَ ثُبُورٗا وَٰحِدٗا وَٱدۡعُواْ ثُبُورٗا كَثِيرٗا
14. ዛሬማ አንድን ጥፋት ብቻ አትጥሩ:: ይልቁንም ብዙን ጥፋት ጥሩ ይባላሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ أَذَٰلِكَ خَيۡرٌ أَمۡ جَنَّةُ ٱلۡخُلۡدِ ٱلَّتِي وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۚ كَانَتۡ لَهُمۡ جَزَآءٗ وَمَصِيرٗا
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ይህ የተሻለ ነውን? ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጡት የዘልዓለሟ ገነት?» ገነት ለእነርሱ ምንዳና መመለሻ ሆነች።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَّهُمۡ فِيهَا مَا يَشَآءُونَ خَٰلِدِينَۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ وَعۡدٗا مَّسۡـُٔولٗا
16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ተስፋ ከጌታህ ሊለመን የሚገባው ተስፋ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ وَمَا يَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَقُولُ ءَأَنتُمۡ أَضۡلَلۡتُمۡ عِبَادِي هَٰٓؤُلَآءِ أَمۡ هُمۡ ضَلُّواْ ٱلسَّبِيلَ
17. እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን የሚሰበስብበትንና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን? ወይስ እነርሱው እራሳቸው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَالُواْ سُبۡحَٰنَكَ مَا كَانَ يَنۢبَغِي لَنَآ أَن نَّتَّخِذَ مِن دُونِكَ مِنۡ أَوۡلِيَآءَ وَلَٰكِن مَّتَّعۡتَهُمۡ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ نَسُواْ ٱلذِّكۡرَ وَكَانُواْ قَوۡمَۢا بُورٗا
18. (ተመላኪዎቹም): «አላህ ሆይ! ጥራት ይገባህ:: ከአንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ አይገባንም:: ግን እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን መገንዘብን እስከ ተውና ጠፊ ህዝቦችም እስከሚሆኑ ድረስ አጣቀምካቸው።» ይላሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَقَدۡ كَذَّبُوكُم بِمَا تَقُولُونَ فَمَا تَسۡتَطِيعُونَ صَرۡفٗا وَلَا نَصۡرٗاۚ وَمَن يَظۡلِم مِّنكُمۡ نُذِقۡهُ عَذَابٗا كَبِيرٗا
19. በምትሉትም አማልክቶቻችሁ አስዋሹዋችሁ:: ቅጣቴን መገፍተርንም ሆነ እራሳችሁን መርዳት አትችሉም:: ከናንተም የሚበድልን ሰው ታላቅን ቅጣት እናቀምሰዋለን:: (ይባላሉ።)
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا قَبۡلَكَ مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّآ إِنَّهُمۡ لَيَأۡكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَيَمۡشُونَ فِي ٱلۡأَسۡوَاقِۗ وَجَعَلۡنَا بَعۡضَكُمۡ لِبَعۡضٖ فِتۡنَةً أَتَصۡبِرُونَۗ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرٗا
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም ከመልዕክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚሄዱ ሆነው እንጂ አላክንም:: ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል:: ትታገሳላችሁን? ጌታህም ተመልካች ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Al-Furqan
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院 - Mục lục các bản dịch

穆罕默德·宰尼·泽海伦丁,由非洲学院发行

Đóng lại