Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - Bản dịch tiếng Amharic - Zain * - Mục lục các bản dịch


Ý nghĩa nội dung Chương: Chương Al-Zumar   Câu:

ሱረቱ አዝ ዙመር

تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ
1. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَٱعۡبُدِ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلۡخَالِصُۚ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ
3. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት ለአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት ሁሉ «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታምንና ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَّوۡ أَرَادَ ٱللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدٗا لَّٱصۡطَفَىٰ مِمَّا يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ سُبۡحَٰنَهُۥۖ هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ
4. አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር:: ጥራት ተገባው:: እርሱ አሸናፊውና ብቸኛው አንዱ አላህ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۖ يُكَوِّرُ ٱلَّيۡلَ عَلَى ٱلنَّهَارِ وَيُكَوِّرُ ٱلنَّهَارَ عَلَى ٱلَّيۡلِۖ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمًّىۗ أَلَا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفَّٰرُ
5. አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ሌሊቱንም በቀን ላይ ይጠቀልላል:: ቀኑንም በሌሊት ላይ እንዲሁ ይጠቀልላል:: ጸሐይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ አሸናፊዉና መሀሪው ነውና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
خَلَقَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ ثُمَّ جَعَلَ مِنۡهَا زَوۡجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ ثَمَٰنِيَةَ أَزۡوَٰجٖۚ يَخۡلُقُكُمۡ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡ خَلۡقٗا مِّنۢ بَعۡدِ خَلۡقٖ فِي ظُلُمَٰتٖ ثَلَٰثٖۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُصۡرَفُونَ
6. (ሰዎች ሆይ!) ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን ፈጠረ:: ለእናንተም ከግመልና ከዳልጋ ከብት፤ ከፍየልና ከበግ ስምንት አይነቶችን (ጥንዶችን) አወረደ:: በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሶስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ ይህን ያደረገው ጌታችሁ አላህ ነው:: ስልጣኑም የእርሱ ብቻ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِن تَكۡفُرُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمۡۖ وَلَا يَرۡضَىٰ لِعِبَادِهِ ٱلۡكُفۡرَۖ وَإِن تَشۡكُرُواْ يَرۡضَهُ لَكُمۡۗ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرۡجِعُكُمۡ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
7. በአላህ ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው:: ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም እርሱን ይወድላችኋል:: ማንኛይቱም ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያም የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ብቻ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ ይነግራችኋል:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ وَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ضُرّٞ دَعَا رَبَّهُۥ مُنِيبًا إِلَيۡهِ ثُمَّ إِذَا خَوَّلَهُۥ نِعۡمَةٗ مِّنۡهُ نَسِيَ مَا كَانَ يَدۡعُوٓاْ إِلَيۡهِ مِن قَبۡلُ وَجَعَلَ لِلَّهِ أَندَادٗا لِّيُضِلَّ عَن سَبِيلِهِۦۚ قُلۡ تَمَتَّعۡ بِكُفۡرِكَ قَلِيلًا إِنَّكَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلنَّارِ
8. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ ወደ እርሱ ተመላሽ ሆኖ ጌታወን ይጠራል:: ከዚያም ከእርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደ እርሱ ይጸልይበት የነበረውን መከራ ይረሳል:: ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል:: ለእንዲህ አይነቱ ሰው «በክህደት ጥቂትን ተጣቀም፤ አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ።» በለው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَمَّنۡ هُوَ قَٰنِتٌ ءَانَآءَ ٱلَّيۡلِ سَاجِدٗا وَقَآئِمٗا يَحۡذَرُ ٱلۡأٓخِرَةَ وَيَرۡجُواْ رَحۡمَةَ رَبِّهِۦۗ قُلۡ هَلۡ يَسۡتَوِي ٱلَّذِينَ يَعۡلَمُونَ وَٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶችም ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የሚገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሓዲ ነውን? በለው።) «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው:: የሚገሰፁት ባለ አእምሮዎች ብቻ ናቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ يَٰعِبَادِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ رَبَّكُمۡۚ لِلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٞۗ وَأَرۡضُ ٱللَّهِ وَٰسِعَةٌۗ إِنَّمَا يُوَفَّى ٱلصَّٰبِرُونَ أَجۡرَهُم بِغَيۡرِ حِسَابٖ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ إِنِّيٓ أُمِرۡتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እንድገዛው ታዘዝኩ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأُمِرۡتُ لِأَنۡ أَكُونَ أَوَّلَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
12. «የሙስሊሞች መጀመሪያ እንድሆን ታዘዝኩ» በል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلِ ٱللَّهَ أَعۡبُدُ مُخۡلِصٗا لَّهُۥ دِينِي
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «አላህን ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እገዛዋለሁ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَٱعۡبُدُواْ مَا شِئۡتُم مِّن دُونِهِۦۗ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَٰسِرِينَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِيهِمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ أَلَا ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِينُ
15. «ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ:: ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሳኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ሰዎች ሆይ! አስተዉሉ:: ግልጽ ከሳራ ማለት ይህ ነው።» በላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَهُم مِّن فَوۡقِهِمۡ ظُلَلٞ مِّنَ ٱلنَّارِ وَمِن تَحۡتِهِمۡ ظُلَلٞۚ ذَٰلِكَ يُخَوِّفُ ٱللَّهُ بِهِۦ عِبَادَهُۥۚ يَٰعِبَادِ فَٱتَّقُونِ
16. ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የሆኑ ድርብርብ ጥላዎች አሏቸው:: ከስራቸዉም እንዲሁ:: ይህ አላህ ባሮቹን እንዲጠነቀቁ በእርሱ ያስፈራራበታል:: ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱلَّذِينَ ٱجۡتَنَبُواْ ٱلطَّٰغُوتَ أَن يَعۡبُدُوهَا وَأَنَابُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ لَهُمُ ٱلۡبُشۡرَىٰۚ فَبَشِّرۡ عِبَادِ
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም ጣዖታትን ከመገዛት የራቁ እና ወደ አላህ የዞሩ ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ብስራት አላቸው። ስለዚህ ባሮቼን አብስር፡፡
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱلَّذِينَ يَسۡتَمِعُونَ ٱلۡقَوۡلَ فَيَتَّبِعُونَ أَحۡسَنَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ هَدَىٰهُمُ ٱللَّهُۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمۡ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
18. እነዚያን ንግግርን የሚያዳምጡትንና መልካምን የሚከተሉትን (ባሮቼን አብስር)፤ እነዚያ አላህ ወደ ቀናው መንገድ የመራቸው ናቸው። እነዚያም እነርሱ ባለ አእምሮዎቹ ናቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَفَمَنۡ حَقَّ عَلَيۡهِ كَلِمَةُ ٱلۡعَذَابِ أَفَأَنتَ تُنقِذُ مَن فِي ٱلنَّارِ
19. በእርሱ ላይ የቅጣት ቃል የተረጋገጠችበትን (ትመራዋለህን?) አንተ በእሳት ውስጥ ያለን ታድናለህን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ رَبَّهُمۡ لَهُمۡ غُرَفٞ مِّن فَوۡقِهَا غُرَفٞ مَّبۡنِيَّةٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ لَا يُخۡلِفُ ٱللَّهُ ٱلۡمِيعَادَ
20. ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ፤ ለእነርሱም ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ አሏቸው:: (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፤ አላህም ቃሉን አያፈርስም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَسَلَكَهُۥ يَنَٰبِيعَ فِي ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ يُخۡرِجُ بِهِۦ زَرۡعٗا مُّخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصۡفَرّٗا ثُمَّ يَجۡعَلُهُۥ حُطَٰمًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكۡرَىٰ لِأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድር ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ብዙ አይነቶች የሆኑ የተለያዩ አዝመራዎችን ያወጣበታል:: ከዚያም ይደርቃል:: ገርጥቶም ታየዋለህ:: ከዚያ ስብርብር ያደርገዋል፤ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሳፄ አለበት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٖ مِّن رَّبِّهِۦۚ فَوَيۡلٞ لِّلۡقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
22. አላህ ደረቱን ለእስልምና ያሰፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የሆነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸዉም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወየውላቸው፤ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱللَّهُ نَزَّلَ أَحۡسَنَ ٱلۡحَدِيثِ كِتَٰبٗا مُّتَشَٰبِهٗا مَّثَانِيَ تَقۡشَعِرُّ مِنۡهُ جُلُودُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمۡ وَقُلُوبُهُمۡ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهۡدِي بِهِۦ مَن يَشَآءُۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٍ
23. አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን ተመሳሳይ ተደጋጋሚ የሆነን መጽሐፍ (ቁርኣንን) አወረደ:: ከእርሱ ግሳፄ የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ:: ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ ተስፋ ማስታወስ ይለዝባሉ:: ይህ የአላህ መምሪያ ነው፤ በእርሱ የሚሻዉን ሰው ይመራበታል። አላህም የሚያጠመውን ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَفَمَن يَتَّقِي بِوَجۡهِهِۦ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَقِيلَ لِلظَّٰلِمِينَ ذُوقُواْ مَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ
24. በትንሳኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው (ከቅጣቱ እንደዳነው ነውን?) ለበዳዮችም «ትሰሩት የነበራችሁን ቅጣትን ቅመሱ» ይባላሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَأَتَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ:: ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَذَاقَهُمُ ٱللَّهُ ٱلۡخِزۡيَ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
26. አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ አያስተባብሉም ነበር::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ ضَرَبۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖ لَّعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
27. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُرۡءَانًا عَرَبِيًّا غَيۡرَ ذِي عِوَجٖ لَّعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ
28. መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን (አብራራነው):: ሊጠነቀቁ ይከጀላልና::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا رَّجُلٗا فِيهِ شُرَكَآءُ مُتَشَٰكِسُونَ وَرَجُلٗا سَلَمٗا لِّرَجُلٍ هَلۡ يَسۡتَوِيَانِ مَثَلًاۚ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
29. አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የሆኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹህ የሆነን ባሪያ ለሚያጋራና በአንድነት ለሚያምን ሰው ምሳሌ አደረገ። በምሳሌ ይስተካካላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّكَ مَيِّتٞ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عِندَ رَبِّكُمۡ تَخۡتَصِمُونَ
31 ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ቀን እጌታችሁ ዘንድ ትከራከራላችሁ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَذَبَ عَلَى ٱللَّهِ وَكَذَّبَ بِٱلصِّدۡقِ إِذۡ جَآءَهُۥٓۚ أَلَيۡسَ فِي جَهَنَّمَ مَثۡوٗى لِّلۡكَٰفِرِينَ
32. በአላህ ላይም ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲያን መኖሪያ የለምን? (አለ እንጂ)::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱلَّذِي جَآءَ بِٱلصِّدۡقِ وَصَدَّقَ بِهِۦٓ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُتَّقُونَ
33. ያም በእውነት የመጣውና በእርሱ ያመነዉም እነዚያ እነርሱ አላህን ፈሪዎቹ ናቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمۡۚ ذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
34. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚሹት (የሚፈልጉት) ሁሉ አላቸው:: ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لِيُكَفِّرَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ أَسۡوَأَ ٱلَّذِي عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ ٱلَّذِي كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
35. አላህ ያንን በስህተት የሰሩትን መጥፎ ስራ ከእነርሱ ሊሰርዝላቸውና በዚያም ይሰሩት በነበሩት መልካም ስራ ምንዳቸውን ሊመነዳቸው ይህንን አደረገ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِكَافٍ عَبۡدَهُۥۖ وَيُخَوِّفُونَكَ بِٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٖ
36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ ከእርሱ ሌላ በሆኑትም ጣኦታት ያስፈራሩሀል፤ አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን? አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّضِلٍّۗ أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِعَزِيزٖ ذِي ٱنتِقَامٖ
37. አላህ የሚያቀናውንም ለእርሱ ምንም አጥማሚ የለዉም:: አላህ አሸናፊውና የመበቀል ባለቤት አይደለምን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ قُلۡ أَفَرَءَيۡتُم مَّا تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ إِنۡ أَرَادَنِيَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ هَلۡ هُنَّ كَٰشِفَٰتُ ضُرِّهِۦٓ أَوۡ أَرَادَنِي بِرَحۡمَةٍ هَلۡ هُنَّ مُمۡسِكَٰتُ رَحۡمَتِهِۦۚ قُلۡ حَسۡبِيَ ٱللَّهُۖ عَلَيۡهِ يَتَوَكَّلُ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ
38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል:: «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ጣዖታት አያችሁን? እስቲ ንገሩኝ:: አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈልገኝ እነርሱም ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው:: «አላህ በቂዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ يَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَٰمِلٞۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ
39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሁናችሁ ስሩ:: እኔም ባለሁበት ሁኔታ ላይ ሁኜ ሰሪ ነኝና:: ወደ ፊትም ትክክለኛው የቱ እንደነበር ታውቃላችሁ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيۡهِ عَذَابٞ مُّقِيمٌ
40. «ያንን የሚያሳፍረው ቅጣት የሚመጣበትንና በእርሱ ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ታውቃላቸሁ።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
إِنَّآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ لِلنَّاسِ بِٱلۡحَقِّۖ فَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٍ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች ጥቅም በእውነት አወረድነው:: እናም በሱ የተመራ ሰው ሁሉ ፋይዳው ለነፍሱ ነው:: የጠመመም ሰው ጉዳቱ ለራሱ ነው የሚጠመው:: አንተም ታስገድዳቸው ዘንድ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አይደለህም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلۡأَنفُسَ حِينَ مَوۡتِهَا وَٱلَّتِي لَمۡ تَمُتۡ فِي مَنَامِهَاۖ فَيُمۡسِكُ ٱلَّتِي قَضَىٰ عَلَيۡهَا ٱلۡمَوۡتَ وَيُرۡسِلُ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّىۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
42. አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል:: ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፈ ጊዜ ይወስዳታል:: ከዚያም ያችን ሞትን የፈረደባትን ነፍስ ይይዛታል:: ሌላይቱን ደግሞ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቃታል:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉበት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُفَعَآءَۚ قُلۡ أَوَلَوۡ كَانُواْ لَا يَمۡلِكُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَعۡقِلُونَ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ቁረይሾች ከአላህ ሌላ አማላጆችን ያዙ። «እነርሱ ምንም የማይችሉና ምንም የማያውቁ ቢሆኑም ታመልኳቸዋላችሁን?» በላቸው።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُل لِّلَّهِ ٱلشَّفَٰعَةُ جَمِيعٗاۖ لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
44. «ምልጃ ሁሉም የአላህ ብቻ ነው:: የሰማያትና የምድር ስልጣንም የእርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ» በላቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَإِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَحۡدَهُ ٱشۡمَأَزَّتۡ قُلُوبُ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِۖ وَإِذَا ذُكِرَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦٓ إِذَا هُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ
45. አላህ ብቻዉን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸማቀቃሉ (ይደነብራሉ) እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሆኑት ጣዖታት በተወሱ ጊዜ ደግሞ እነርሱ ወዲያውኑ ይደሰታሉ።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلِ ٱللَّهُمَّ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ عَٰلِمَ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ أَنتَ تَحۡكُمُ بَيۡنَ عِبَادِكَ فِي مَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን የፈጠርክ ሩቁንም ቅርቡንም አዋቂ የሆንከው አላህ ሆይ! አንተ በባሮችህ መካከል በዚያም ይለያዩበት በነበሩት ነገር ትፈርዳለህ» በል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَوۡ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا وَمِثۡلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفۡتَدَوۡاْ بِهِۦ مِن سُوٓءِ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَبَدَا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مَا لَمۡ يَكُونُواْ يَحۡتَسِبُونَ
47. ለነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላዉም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሳኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር:: ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَبَدَا لَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
48. ለእነርሱም የሰሯቸው መጥፎዎቹ ይገልጹላቸዋል:: በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ضُرّٞ دَعَانَا ثُمَّ إِذَا خَوَّلۡنَٰهُ نِعۡمَةٗ مِّنَّا قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلۡمِۭۚ بَلۡ هِيَ فِتۡنَةٞ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
49. ሰውም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ይጠራናል:: ከዚያም ከእኛ የሆነውን ጸጋ በሰጠነው ጊዜ «እርሱን የተሰጠሁት በእውቀቴ ብቻ ነው።» ይላል:: ይልቁንም እርሷ (ጸጋይቱ) መፈተኛ ናት:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቁም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قَدۡ قَالَهَا ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَمَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
50. እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ይችኑ ቃል በእርግጥ ብለዋታል:: ይሰሩት የነበሩትም ነገር ከእነርሱ አልጠቀማቸዉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْۚ وَٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡ هَٰٓؤُلَآءِ سَيُصِيبُهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْ وَمَا هُم بِمُعۡجِزِينَ
51. የሰሯቸዉም መጥፎዎች ቅጣት አገኛቸው:: ከእነዚህም እነዚያ የበደሉት የሰሯቸውን መጥፎዎች ፍዳ በእርግጥ ይነካቸዋል:: እነርሱም አምላጮች አይደሉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَوَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
52. አላህ ሲሳዩን ለሚሻው ሰው የሚያሰፋ፤ ለሚሻው ሰው የሚያጠብም መሆኑን አያውቁምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑት ህዝቦች ሁሉ አያሌ ግሳጼዎች አሉበት::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
۞ قُلۡ يَٰعِبَادِيَ ٱلَّذِينَ أَسۡرَفُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُواْ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራልና:: እነሆ እርሱ መሀሪዉና አዛኙ ነውና።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَنِيبُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّكُمۡ وَأَسۡلِمُواْ لَهُۥ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَكُمُ ٱلۡعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ
54. (ሰዎች ሆይ!) ቅጣቱ ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትረዱ ከመሆናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ:: ለእርሱም ታዘዙ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَٱتَّبِعُوٓاْ أَحۡسَنَ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَكُمُ ٱلۡعَذَابُ بَغۡتَةٗ وَأَنتُمۡ لَا تَشۡعُرُونَ
55. እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን መልካሙን መጽሐፍ ተከተሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَن تَقُولَ نَفۡسٞ يَٰحَسۡرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِي جَنۢبِ ٱللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ ٱلسَّٰخِرِينَ
56. የካደች ነፍስ ሁሉ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስሆን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ! ጸጸቴ!» የምትል እንዳትሆን
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَوۡ تَقُولَ لَوۡ أَنَّ ٱللَّهَ هَدَىٰنِي لَكُنتُ مِنَ ٱلۡمُتَّقِينَ
57. ወይም «አላህ በመራኝ ኖሮ ከሚጠነቀቁት ሰዎች እሆን ነበር።» የምትል እንዳትሆን
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
أَوۡ تَقُولَ حِينَ تَرَى ٱلۡعَذَابَ لَوۡ أَنَّ لِي كَرَّةٗ فَأَكُونَ مِنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
58. ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ አለም አንድ ጊዜ የመመለስ ዕድል በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎች በሆንኩ።» የምትል ከመሆኗ በፊት መልካሙን ተከተሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
بَلَىٰ قَدۡ جَآءَتۡكَ ءَايَٰتِي فَكَذَّبۡتَ بِهَا وَٱسۡتَكۡبَرۡتَ وَكُنتَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
59. የለም ተመርተሃል:: አንቀፆቼ በእርግጥ መጥተውሃል:: በእነርሱም አስተባብለሃል፤ ኮርተሃልም:: ከከሓዲያንም ሆነሃል (ይባላል)::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تَرَى ٱلَّذِينَ كَذَبُواْ عَلَى ٱللَّهِ وُجُوهُهُم مُّسۡوَدَّةٌۚ أَلَيۡسَ فِي جَهَنَّمَ مَثۡوٗى لِّلۡمُتَكَبِّرِينَ
60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በትንሳኤ ቀንም እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን ፊቶቻቸው የጠቆሩ ሆነው ታያቸዋለህ:: በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَيُنَجِّي ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ بِمَفَازَتِهِمۡ لَا يَمَسُّهُمُ ٱلسُّوٓءُ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
61. እነዚያም የተጠነቀቁትን በማግኛቸው ስፍራ ሆነው አላህ ያድናቸዋል፤ ክፉ ነገር አይነካቸዉም:: እነርሱም አያዝኑም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ
62. አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
لَّهُۥ مَقَالِيدُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
63. የሰማያትና የምድር (ድልብ) መከፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: እነዚያም በአላህ አናቅጽ የካዱት እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قُلۡ أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَأۡمُرُوٓنِّيٓ أَعۡبُدُ أَيُّهَا ٱلۡجَٰهِلُونَ
64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድንገዛ ታዙኛላቸሁን?» በላቸው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَلَقَدۡ أُوحِيَ إِلَيۡكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكَ لَئِنۡ أَشۡرَكۡتَ لَيَحۡبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል:: በእርግጥም ከከሓዲያን ትሆናለህ በማለት ወደ አንተና እነዚያ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሰዎች በእርግጥ ተወርዷል::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
بَلِ ٱللَّهَ فَٱعۡبُدۡ وَكُن مِّنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም:: ከአመስጋኞችም ሁን::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَمَا قَدَرُواْ ٱللَّهَ حَقَّ قَدۡرِهِۦ وَٱلۡأَرۡضُ جَمِيعٗا قَبۡضَتُهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَٱلسَّمَٰوَٰتُ مَطۡوِيَّٰتُۢ بِيَمِينِهِۦۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
67. አላህንም በትንሳኤው ቀን ምድርን በመላ ጭብጡ ስትሆንና ሰማያትም በቀኝ እጁ የሚጠቀለሉ ሲሆኑ ከእርሱ ጋር ሌላን በማጋራታቸው ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ። ላቀም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا مَن شَآءَ ٱللَّهُۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخۡرَىٰ فَإِذَا هُمۡ قِيَامٞ يَنظُرُونَ
68. በቀንዱም ይነፋል:: በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡርና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል:: ከዚያም በእርሱ ሌላ መነፋት ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ የሚሰራባቸውን የሚጠባበቁ ሆነው ቋሚዎች ይሆናሉ::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَأَشۡرَقَتِ ٱلۡأَرۡضُ بِنُورِ رَبِّهَا وَوُضِعَ ٱلۡكِتَٰبُ وَجِاْيٓءَ بِٱلنَّبِيِّـۧنَ وَٱلشُّهَدَآءِ وَقُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
69. ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፤ መጽሐፉም ይቀርባል:: ነብያትና ምስክሮችም ይመጣሉ:: በመካከላቸዉም በእውነት ይፈረዳል:: እነርሱም አይበደሉም::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَوُفِّيَتۡ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا عَمِلَتۡ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَا يَفۡعَلُونَ
70. ነፍስም ሁሉ የሰራቸውን ስራ ትሞላለች (ትሰፍራለች):: እርሱም የሚሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتۡ أَبۡوَٰبُهَا وَقَالَ لَهُمۡ خَزَنَتُهَآ أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ رُسُلٞ مِّنكُمۡ يَتۡلُونَ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِ رَبِّكُمۡ وَيُنذِرُونَكُمۡ لِقَآءَ يَوۡمِكُمۡ هَٰذَاۚ قَالُواْ بَلَىٰ وَلَٰكِنۡ حَقَّتۡ كَلِمَةُ ٱلۡعَذَابِ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ
71. እነዚያ በአላህ የካዱትም የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ በሮቿ ይከፈታሉ:: ወደሷ በመጡም ጊዜ ዘበኞቿ «ከእናንተ የሆኑ የጌታችሁን አናቅጽ በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ መልዕክተኞች አልመጧችሁምን ነበርን?» ይሏቸዋል፤ «የለም መጥተውልናል። ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሓዲያን ላይ ተረጋገጠች።» (ይላሉ።)
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
قِيلَ ٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ
72. «የገሀነምን በሮች በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ የትዕቢተኞችም መኖሪያ ምን ትከፋ!» ይባላል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَسِيقَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ رَبَّهُمۡ إِلَى ٱلۡجَنَّةِ زُمَرًاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا وَفُتِحَتۡ أَبۡوَٰبُهَا وَقَالَ لَهُمۡ خَزَنَتُهَا سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمۡ طِبۡتُمۡ فَٱدۡخُلُوهَا خَٰلِدِينَ
73. እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገነት ይነዳሉ:: በመጧትም ጊዜ ደጃፎቿ የተከፈቱ ሲሆኑ ዘበኞቿም ለእነርሱ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ተዋባችሁ፤ ዘወታሪዎች ሆናችሁ ግቧት።» ይሏቸዋል።
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي صَدَقَنَا وَعۡدَهُۥ وَأَوۡرَثَنَا ٱلۡأَرۡضَ نَتَبَوَّأُ مِنَ ٱلۡجَنَّةِ حَيۡثُ نَشَآءُۖ فَنِعۡمَ أَجۡرُ ٱلۡعَٰمِلِينَ
74. «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ለዚያ የተስፋ ቃሉን ለሞላልን፤ የገነትንም ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንሆን ላወረሰን ይገባው።» ይላሉ። የሰሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
وَتَرَى ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ حَآفِّينَ مِنۡ حَوۡلِ ٱلۡعَرۡشِ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡۚ وَقُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡحَقِّۚ وَقِيلَ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲሆኑ በአርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ሆነው ታያለህ፡፡ በመካከላቸውም እውነት ይፈረዳል። ይባላልም፤ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።»
Các Tafsir tiếng Ả-rập:
 
Ý nghĩa nội dung Chương: Chương Al-Zumar
Mục lục các chương Kinh Số trang
 
Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - Bản dịch tiếng Amharic - Zain - Mục lục các bản dịch

Bản dịch tiếng Amharic

Đóng lại